አስከመቼ?

Source: https://mesfinwoldemariam.wordpress.com/2020/06/04/%E1%8A%A0%E1%88%B5%E1%8A%A8%E1%88%98%E1%89%BC/
https://2.gravatar.com/avatar/e16ba1b5076af05a353317291dcf50ae?s=96&d=identicon&r=G

መስፍን ወልደ ማርያም
ግንቦት 2012

እስከ መቼ? ወይዘሮ ሀቢባ መሠረታዊ ጥያቄ ጠይቀሻል፤ ከሔዋን የጀመረ ጥያቄ አይደለም፤ በእኔ አስተያየት የመጀመሪያዋ አብዮታዊት ሔዋን ነች፤ ክፉና በጎን ለመለየት የሚያስችለውን በለስ በላችና፣ ባሏንም አበላችና ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የሰው ልጅን ኃጢአት፣ የሰው ልጅን ወንጀል ሸፋፍና አዝላ በወጥ ቤትና በመኝታ ቤት ተወሰናለች! አስከመቼ? እስክትነቃ! የሔዋንን አብዮት ከሞተበት አሥነስታ መመሪያዋ አስክታደርገው! እንደወንዶች ስሜቷንም ሀሳቧንም በአደባባይ መግለጽ አስክትችል፣ እቤትዋ ቁጭ ብላ በመጣልኝ እያለች ከመቅበጥበጥ ይልቅ ተነሥታ እጆቿን ዘርግታ የፈለገችውን፣ የወደደችውን እስክትይዝ! በሌላ አነጋገር ነጻ አስክትወጣ!
ሀቢባ አብዮቱን ጀምሪውና ምሪው! ያበርታሽ፡፡

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.