አብሮ የኖሩ፣ ክፉ ደግ ያሳለፉ ዜጎች በድንጋይ እየተወገሩ፣ በበትር እየተቀጠቀጡ መሞታቸውን መረጃዎች አመልክተዋል፡፡

Source: https://mereja.com/amharic/v2/165945

Sheger FM : ትዕግስትና ሆደ ሰፊነት ከማያባራ የጭካኔ ድርጊት ጋር እንዴት ይታረቃል? ኢትዮጵያውያን የአብሮ መኖር ልኬታቸውን ረጅም ዘመን ይቆጥሩበታል ግድያና ክፉ ስራዎችን አጥብቀው በሚከለክሉ እምነቶች ተከታዮች መሆናቸውም ለረጅም ጊዜ ይጠቀሳል፡፡ግን አሁን የሚታየውና የሚሰማው ይፈፀማል ተብሎ የማይታሰብ የማይገመትም ነበር አብሮ የኖሩ፣ ክፉ ደግ ያሳለፉ ዜጎች በድንጋይ እየተወገሩ፣ በበትር እየተቀጠቀጡ መሞታቸውን መረጃዎች አመልክተዋል፡፡ግጭቶች ከመፈጠራቸው ይባስ አፈፃፀማቸው አስደንጋጭ ሆኗል፡፡ ይኽን መሰል አሰቃቂ ድርጊት ሲፈፀም ሃይ የሚል አካል ቶሎ አለመድረሱ የወደፊቱንም ጊዜ አስጊ አድርጎታል፡፡ ስለዚህ ህዝቡ መንግስትንም እየጠየቀ ነው፡፡

 

Share this post

One thought on “አብሮ የኖሩ፣ ክፉ ደግ ያሳለፉ ዜጎች በድንጋይ እየተወገሩ፣ በበትር እየተቀጠቀጡ መሞታቸውን መረጃዎች አመልክተዋል፡፡

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.