አብይ እህመድ እስክንድር ነጋ ላይ “ግልጽ ወደ ሆነ ጦርነት ውስጥ እንገባለን” ያለው ዛቻ ሊተገብረው እንደሆነ ውስጥ አወቆች አጋለጡ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/124384

ህወሃት ጉያ ውስጥ የክፋትና የመሰሪነት ጡጦ ሲጠባ ያደገው አብይ አህመድ በህዝባዊ አመጽና ለረዥም ዓመታት በተደረገ ሰላማዊ ትግል የሥልጣን ማማ ላይ ከተፈናጠጠ በኋላ በአፈ ጮሌነትና በማጭበርበር በርካታ ቁጥር ያላቸውን ኢትዮጵያዊያንን እንዳደነዘዘና እንዳፈዘዘ ይታወቃል። ብዙ ሽህ ቁጥር ያለውን የፌዴራል መንግስትን ጦር ሰራዊት፣ ታንኩን፣ የጦሩን አውሮፕላኑና መድፉን በእጁ ቢያስገባም የህወሃትን ወንጀለኞች እንደ ጌታቸው አሰፋ አይነቶቹን ለፍርድ ለማቅረብ ወኔው የከዳውና የተልፈሰፈሰው አብይ አህመድ በሰላማዊ መንገድ የህዝብን ጥያቄ አንስቶ የተገፋውንና የተረገጠውን የአዲስ አባባ ህዝብ ብሶት በማሰማቱ ምክንያት ከአስኪሪቢቶና ወረቀት ሌላ ምንም የሌለውንና በሰላማዊ ትግልና በጋዜጠኛነቱ ዓለም የተመሰከረለትን እስክንድር ነጋን የወገንቡ ቅማል ሆኖበት አላስቀምጥ አላስቆም ብሎት እንደ አህያ እንዲያናፋ አስገድዶታል። እስክንድር ነጋ ለበርካታ ዓመታት ለዲሞክራሲ፣ ለእኩልነትና ለአንድነት መስፈን በህወሃት እስር ቤት ሲሰቃይ በነበረበት ጊዜ አብይ አህመድ የህወሃትን ሹመት ተቀብሎ የስለላ መስሪያ ቤት በመምራት ንጹሃንን እየሰለለ ለመከራ አሳልፎ ይሰጣቸው እንደነበር እራሱም ቢሆን የሚክደው ሃቅ አይደለም። በነዚያ የአፈናና የስቃይ ዓመታት እስክንድር ነጋ ህጻን ልጁንና ባለቤቱን ለመከራ አጋልጦ እሱ እስር ቤት ውስጥ እድሜውን አጋምሶታል። አብይ አህመድ ይሉኝታ የሌለውና በጭብጨባ ብዛት ናላውን የሳተ በመሆኑ ነው እንጅ እስክንድር ነጋ ላይ አፉን የሚከፍትበት የሞራልም ሆነ የግብረገብ ብቃት የለውም።
አብይ አህመድ ሰኔ 16, 2010 አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በደረሰበት የግድያ ሙከራ የህይወት መስዋዕትነት የከፈለለትንና አሁን ለመጣው ለውጥ ለብዙ ዓመታት  ምርጫ 97ን ጭምር ከፍተኛ የህይወት መስዋዕትነትን የከፈለውን የአዲስ አበባ ህዝብ ላይ ክህደት ፈጽሟል። የአዲስ

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.