አትሌት ሌሊሳ ዴሲሳ እና ሩት ቼፔንጌቲች የ2019 ምርጥ የማራቶን ሩጫ ውድድር ተሸላሚ ሆኑ

Source: https://fanabc.com/2019/11/%E1%8A%A0%E1%89%B5%E1%88%8C%E1%89%B5-%E1%88%8C%E1%88%8A%E1%88%B3-%E1%8B%B4%E1%88%B2%E1%88%B3-%E1%8A%A5%E1%8A%93-%E1%88%A9%E1%89%B5-%E1%89%BC%E1%8D%94%E1%8A%95%E1%8C%8C%E1%89%B2%E1%89%BD-%E1%8B%A82019/

አዲስ አበባ፣ጥቅምት 29፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአለም ሻምፒዮኖቹ ኢትዮጵያዊው አትሌት ሌሊሳ ዴሲሳ እና ኬንያዊቷ አትሌት ሩት ቼፔንጌቲች የ2019 ምርጥ የማራቶን ሩጫ ተወዳዳሪ ተሸላሚ ሆነዋል።

የአለም አቀፉ የማራቶን እና ረጅም ርቀት ውድድሮች ማህበር (ኤ አይ ኤም ኤስ) የሚያዘጋጀው የዓመቱ ምርጥ የማራቶን ሩጫ ውድድር ሽልማት ስነ ስርዓት በትናንትናው ዕለት በግሪክ አቴንስ ከተማ ተካሂዷል።

ለሰባተኛ ጊዜ በተካሄደው በዚህ የዕውቅና መድረክም በወንዶች ኢትዮጵያዊው አትሌት ሌሊሳ ደሲሳ ተሸላሚ ሲሆን፥በሴቶች ደግሞ ኬንያዊቷ አትሌት ሩት ቼፔንጌቲች ተሸላሚ ሆናለች።

አትሌቶቹ ተሸላሚ የሆኑትም ባለፉት 12 ወራት በማራቶን ውድድር ሩጫ ዘርፍ ባስመዘገቧቸው ምርጥ ውጤቶች መሰረት መሆኑ ተመላክቷል።

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.