አትሌት ደራርቱ ቱሉ የምሥራቅ አፍሪካ አትሌቲክስ ሪጅን ምክትል ፕሬዚዳንት ሆና በሙሉ ድምፅ ተመረጠች

Source: https://mereja.com/amharic/v2/83698

ደራርቱ ቱሉ የምሥራቅ አፍሪካ አትሌቲክስ ሪጅን ምክትል ፕሬዚዳንት ሆና ተመረጠች
ኮሎኔል አትሌት ደራርቱ ቱሉ የምሥራቅ አፍሪካ አትሌቲክስ ሪጅን ምክትል ፕሬዚዳንት ሆና በሙሉ ድምፅ ተመርጣለች።

ከዚህ በተጨማሪም ኮሎኔል አትሌት ደራርቱ ቱሉ በአፍሪካ አትሌቲክስ ኮንፌዴሬሽን /CAA/ ውስጥ ሪጅኑን በመወከል የቦርድ አባል ሆና ተመርጣለች።
የምሥራቅ አፍሪካ አትሌቲክስ ሪጅን ኮንግረስ ስብሰባ በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ከተማ ተካሂዷል።
ኮሎኔል አትሌት ደራርቱ ቱሉ በዛሬው እለት በተካሄደው ስብሰባ ላይ ነው የምሥራቅ አፍሪካ አትሌቲክስ ሪጅን ምክትል ፕሬዚዳንት እና የአፍሪካ አትሌቲክስ ኮንፌዴሬሽን የቦርድ አባል ሆና የተመረጠችው።
በስብሰባው ላይ ኬኒያዊው ጃክሰን ቱዌዪ የምሥራቅ አፍሪካ አትሌቲክስ ሪጅን ፕሬዚዳንት ሆነው ሲመረጡ፥ ኡጋንዳዊው ዶሜኒክ አቱሴት ተቀዳሞ ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው ተመርጠዋል።
ኤፍ ቢ ሲ እንደዘገበው ሱዳናዊው ኢንጂነር ሳዲቅ ኢብራሂም የምሥራቅ አፍሪካ አትሌቲክስ ሪጅን ዋና ጸሃፊ ተደርገው ተመርጠዋል።

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.