አትሌት ደራርቱ ቱሉ የአድዋን ድል ለመዘከር በባዶ እግሯ 500 ሜትር ልትሮጥ ነው

Source: https://fanabc.com/2019/01/%E1%8A%A0%E1%89%B5%E1%88%8C%E1%89%B5-%E1%8B%B0%E1%88%AB%E1%88%AD%E1%89%B1-%E1%89%B1%E1%88%89-%E1%8B%A8%E1%8A%A0%E1%8B%B5%E1%8B%8B%E1%8A%95-%E1%8B%B5%E1%88%8D-%E1%88%88%E1%88%98%E1%8B%98%E1%8A%A8/

አዲስ አበባ፣ጥር 09፣2011)ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ደራርቱ ቱሉ የአድዋ ድልን ለመዘከር በሚካሄደው የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ  ላይ  የመጨረሻዎቹን 500 ሜትሮች በባዶ እግሯ ለመሮጥ ቃል ገብታለች፡፡

የአድዋ ድልን የሚዘክር የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ በአዲስ አበባ የካቲት 24 ቀን 2011 ዓ.ም ይካሄዳል ።

በዚህ ውድድር የክብር አምባሳደር የሆነችው አትሌት ደራርቱ ቱሉ በጎዳና ሩጫው ላይ በመሳተፍ 9 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትሩን በጫማ የተቀረውን 500 ሜትር  ደግሞ በባዶ እግሯ ለመሮጥ ቃል ገብታለች።

የውድድሩ አምባሳደር ሆና በመመረጧም ከፍተኛ ኩራትና ክብር እንዲሁም እድለኝነት እንደሚሰማት ተናግራለች።

ደራርቱ ለመጨረሻ ጊዜ በውድድር የተሳተፈችው ከ8 ዓመታት በፊት እንደሆነ የገለፀች ሲሆን ፥በህዳሴው ግድብ ሩጫ ላይ ከ2 ዓመት በፊት ተሳትፎ እንደነበራትም አስታውሳለች፡፡

በአድዋ ድል እናቶችና አባቶቻችን ደማቸውን አፍሰው ያቆዩትን ታሪክና ጀግንነት ሁሉም በተሰማራበት መስክ መድገም እንዳለበትም አትሌት ደራርቱ አሳስባለች።

 

ምንጭ ፦ኢዜአ

Share this post

One thought on “አትሌት ደራርቱ ቱሉ የአድዋን ድል ለመዘከር በባዶ እግሯ 500 ሜትር ልትሮጥ ነው

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.