አቶ ለማና አቶ ገዱ ሲወዳደሩ #ግርማ_ካሳ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/68944


ሕወሃት ሳትከረበት በፊት ትልቅ ትግል የነበረባቸው አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ነበሩ። ከአቶ ለማ መገርሳ ጋር ሲነጻጸሩ።
አቶ ለማ በኦህዴድ ውስጥ ያሉ የሕወሃት አገልጋዮችን በአጭር ጊዜ ውስጥ አጥርተው( ብዙም ስላልነበሩ) ኦህዴድ ከሕወሃት ገለልተኛ እንዲሆን በቀላሉ ነበር ማድረግ የቻሉት። አቶ ገዱ ግን ብአዴን ውስጥ ከአንድ ሶስተኛ በላይ ህወሃትና አፍቃሪ ህወሃት ስለነበሩ እንቅስቃሴያቸው በገመድ ላይ እንደመራመድ ነበር። እንደውም አንድ ወቅት የስራ አስፈጻሚ ውስጥ የሞሉት አፍቃሪ ህወሃት የብአዴን አመራሮች፣ አቶ ገዱን እስከማንሳትና ራሺያ አምባሳደር አድርጎ እስከመሸኘት የወሰኑበትም ጊዜ ነበር። ያኔ ለአቶ ገዱ በጣም ከባድ ነበር።

አሁን ደግሞ የተገላቢጦሽ ሆኗል። በአማራ ክልል ትልቅ መረጋጋት አለ። ለተወሰኑ ቀናት በመተማ አካባቢ ሕወሃት አስርጎ ባስገባቸው አንዳንድ ቡድኖች ⶭግር ተፈጥሮ ነበር። ከዚያ ውጭ ግን በአሁኑ ወቅት መረጋጋት የት ነው ያለው ቢባል በአማራ ክልል ነው። የፖለቲካ ፓርቲዎች ፣ አብን፣ ግንቦት ስባት፣ ሰማያዊ…በነጻነት ይንቀሳቀሳሉ። የአማራ ቴሌቪዥን በአሰደናቂ ሁኔታ ገለልተኛ ነው።
አቶ ለማ መገርሳ ግን በጣም እየተንገዳገዱ ያሉበት ሁኔታ ነው ያለው። በኦሮሞ ክልል በፍጹም መረጋጋት ብሎ ነገር የለም። ሕግና ስርዓትን ማስጠበቅ አልቻሉም። የቀበሌ፣ ወረዳ፣ ዞን የኦህዴድ አመራሮች እነ አቶ ለማን  አይሰሙም፤ የሚሰሙት እነ ጃዋርን ነው። አቶ ለማ ወለጋንና ሃረርጌ ማስተዳደር ትልቅ ፈተና ሆኖባቸዋል። እነ ጃዋርና ኦነጎች ከፍተኛ አጣብቂኝ ውስጥ ነው የከተቷቸው። አቶ ለማ የሚሰሩትን እያፈረሱባቸው። የኦሮሞ ማህበረሰብ ከሌላው ማህበረሰብ ጋር በማቀራረብ በንግድ፣ በቱሪዝም፣ በኢንቨስትመንት በስራ እድል የበለጠ ተጠቃሚ እንዲሆን ለማድረግ አቶ ለማ ሲደክሙ

Share this post

2 thoughts on “አቶ ለማና አቶ ገዱ ሲወዳደሩ #ግርማ_ካሳ

  1. Ato Grma Kass tew eskahun mintsfewn betam anebewalehu ,endezih ejg betam tesasteh alayehum …..ahunm atsasat Ato Gedu belakachew Liyu Hail bemimalu seytanoch yehzbn hiwot slatefu ,habt slzerfu ena slakatelu new endezih ymiwodesew ..Abdi Ilie (Somali President ) kezih belay min aderege….?
    ebakachuh lehlinachuh nuru ! sttsfu bizu mizan yaldefa yhun . Tarik yferfdal ahun ante kuch bleh egele minamn eyalk wushet btawora ewnetu megaletu aykerm .
    Ethiopia Lezelalem tnur

    Reply
  2. Ato Gedu ena Ato Lemma yesemay ena yemdr yahl new mirarakut —-Lemma Malet Tibeb yetemolabet besal amerar mehonun atrsa Gedumalet degmo kemigebaw bely newtegna aygltsewm …zero chinklat new bil maganen ayhonmbgnm. 4 netb !!!

    Reply

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.