አቶ ለማ መገርሳ በፓርቲዎች ውህደት ላይ ተቃውሞ እንዳላቸው አስታወቁ።

Source: https://mereja.com/amharic/v2/177208

አቶ ለማ መገርሳ በፓርቲዎች ውህደት ላይ ተቃውሞ እንዳላቸው አስታወቁ።

” መዋሀዱን አልደግፍም : ከመጀመሪያ ጀምሬ ተቃውሜያለሁ ። በስብሰባው ብገኝም ፈፅሞ አልደገፍኩም! መደመር የሚባል ፍልስፍናም አይገባኝም! ” አቶ ለማ መገርሣ ለVOA ከተናገሩት

የኢፌዲሪ መከላከያ ሚንስትር እና የኦዲፒ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ለማ መገርሳ መደመርን በሚለው መርህ እንደማይስማሙ እና በፓርቲዎች ውህደት ላይ ተቃውሞ እንዳላቸው አስታወቁ።

አቶ ለማ ለአሜሪካ ድምጽ እንደተናገሩት በፓርቲዎች ውህደት ላይ ያላቸውን ቅሬታ ለኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ማስታወቃቸውን ገልፀው ውህደትም መሆን ካለበት እንዲህ በችኮላ መሆን እንደሌለበት ግልጽ አድርገው ተናግረዋል። #MinilikSalsawi

Gepostet von VOA Amharic am Freitag, 29. November 2019

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.