አቶ በረከት ስምዖን በሰብዓዊ መብት ኮሚሽነር ስራ ውስጥ ጣልቃ በመግባት ያስፈራሩ ነበር ተባለ።

Source: https://mereja.com/amharic/v2/138240

“በኮሚሽነርነት ተመድቤ እንደመጣሁ ብዙም ሳልቆይ ተጣለሁ፡፡ ‘ይህን ትሰራለህ፤ ያንን አትሰራም’ በሚል ማለት ነው። ከወደቁ በኋላ ስም መጥቀስ እንዳይሆን እንጂ ከእነ አቶ በረከት ጋር ነው የተጣላሁት። የቅራኔው መንስዔ ደግሞ ምርጫ 2002ን መከታተልና ሪፖርት ማቅረቤ ላይ ነው።” አምባሳደር ጥሩነህ ዜና የቀድሞው የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር
‹‹በአፌ ያስቀመጡትን ሳላኝክ ዝም ብዬ የምውጥ ሰው አይደለሁም›› -የቀድሞው የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ጥሩነህ ዜና

የተወለዱት በቀድሞው ካፋ ጠቅላይ ግዛት ኮንታ ወረዳ ውስጥ ሲሆን፣ የአንደኛ ደረጃና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን የተማሩት ካሉበት አካባቢ 110 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው በጅማ ከተማ ነው:: በወቅቱ ለአካባቢው አንድ ለእናቱ በሆነው ቀዳማዊ ኃይለስላሴ ዩኒቨርሲቲ በኢኮኖሚክስና ፖለቲካል ሳይንስ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል፡፡ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን በአሜሪካ አገር በኢንተርናሽናል ፋይናንስ ሰርተዋል፤አምባሳደር ጥሩነህ ዜና፡፡
እኚህ የ72 ዓመት አዛውንት በውጭ ጉዳይ ከሶስት አስርት ዓመታት በላይ ያገለገሉ ሲሆን፣ በኒዮርክ በኢትዮጵያ አምባሳደርነት ለአራት ዓመት አገልግለዋል፡፡ ከጥቂት ዓመታት በፊት ደግሞ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር በመሆንም ሰርተዋል፡፡ አዲስ ዘመን ከአምባሳደሩ ጋር ባደረገው ቆይታ በሀገሪቱ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ላይና በዲፕሎማትነታቸው ወቅት ስለሰሯቸው እንዲሁም ስለሌሎችም ጉዳዮች በማንሳት ያደረገውን ቃለ ምልልስ እንደሚከተለው አቅርቦታል፡፡ መልካም ንባብ ይሁንልዎ፡፡
አዲስ ዘመን፡– ወደ ኮሚሽነርነት ከመምጣትዎ በፊት ስለሰሯቸው ቢገልጹልን?
አምባሳደር ጥሩነህ፡– በኮሚሽነርነት የሰራሁት ለአምስት ዓመት ያህል ብቻ ነው፡፡ ህይወቴን በሙሉ ያሳለፍኩት በዲፕሎማሲው ላይ ነው፡፡ በመጀመሪያ ውጭ ጉዳይ እንደገባሁ የሰራሁት በዓለም አቀፍ ግንኙነት ላይ ነው፡፡ ይህም ኢኮኖሚ መምሪያና ዓለም

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.