አቶ ካሳ ተክለብርሃን እዚያው ጓዶቻቸው ጋር ያልቅሱ!

Source: http://welkait.com/?p=8803
Print Friendly

(ግርማ ካሳ)

ካሳ ተ/ብርሃን / ካሳ ሸሪፎ

“በትግራይ እና በአማራው ክልል የሚኖሩ፣ ማን እንደወከላቸው የማይታወቁ ሰዎች፣ የአገር ሽማግሌዎች ነን በሚል፣ የሁለቱም ክልሎች ፕሬዘዳንቶች፣ አቶ ገድ አንዳርጋቸውና አቶ አባይ ወልዱ፣ እንዲሁም ሌሎች በርካታ የሕወሃትና የብአዴን አመራሮች በተገኙበት አንድ ጉብዬ በመቀሌ አድርገዋል። ህዝብን ከሕዝብ ለማቀራረብ በሚል። በዚህ ስብሰባ አቶ ገዱ አንዳርጋቸውና አቶ ካሳ ተክለብርሃን ተናገሩት የተባለው፣ በአንዳንድ ማእዘናት ውይይቶችን ጭሯል። በመርህ ደረጃ ህዝብን ሊያቀራረብ የሚችል ማናቸውም አይነት ድርጊት ሆነ ስብሰባ የሚደገፍና ሊበረታታ የሚገባ ቢሆንም፣ ይህ የመቀሌው ስብሰባ ግን እንኳን የተባለለትን አላማ ሊያሳክ ቀርቶ ጭራሹን በሕዝብ መሳቂያና የጥቂት ጊዜ ወሬ ነው የሆነው።

ከስብሰባው ጋር በተዛመደ የሚነሱ መሰረታዊ ጥያቄዎች አሉ፡-

አማራ በሚባለውና ትግሬ በሚባለው ማህበረሰብ መካከል ምን ችግር ተፈጠረና ነው አሁን የማቀራረብ እንቅስቃሴ በጎላ መልኩ የሚደረገው ? ችግር አለ ከተባለስ ችግሮቹ ምንድን ናቸው ? የችግሮቹ መንስኤ ወይም ዋናው ነቀርሳው ላይ ሳይተኮር ላይ ላዩን ማውራት ችግሩን ይፈታል ወይ ? ላለፉት 25 አመታት በኦሮሚያ በኦህዴድና በኦነግ ፣ በደቡብ ክልል በነ አቶ መለስ ዜናዊ ትእዛዝና በነአቶ ሽፈራው ሽጉጤ ተላላኪነት፣ እጅግ በጣም በርካታ የሆኑ ኢትዮጵያዉን “አማራ ፣ ነፍጠኛ ..ናችሁ” በሚል በጅምላ ሲገደሉ፣ ከቅያቸው ሲፈናቀሉ፣ በባዶ እግራቸው ኪሎሜትሮች አቋርጠው እንዲሰደዱ ሲደረጉ፣ አገራችሁ አይደለም ተብለው ሲባረሩና ቤቶቻቸው ሲቃጠሉ፣ መቼ አይተን እናውቃለን የህዝብ ለሕዝብ መቀራረብ ጉባዬ ? መቼ ነው የኦሮሚያ ክልል ሽማግሌዎች በባህር ዳር መጥተው፣ በአማራ ክልል ካሉ ሽማግሌዎች ጋር እንዲነጋገሩ የተደረገው? የኦህዴድ ባለስልጣናትስ፣ እንኳን በአማራ ክልል ካለው ሕዝብ ጋር ሊነጋገሩ ቀርቶ፣ በኦሮሚያ አፋን ኦሮሞ ከማይናገሩ፣ በሚሊዮኖች ከሚቆጠሩ ወገኖች ጋር እንኳን መነጋገርና የነርሱን ጥያቄ ማስተናገድ የተሳናቸው አይደለም ወይ ?

እነዚህንና ተመሳሳይ ጥያቄዎች ስናነሳ በመቀሌ የተደረገው መቃወማችን አይደለም። ነገር ግን ከፈረሱ በፊት ጋሪው ከቀደመ ጉንጭ ከማልፋት ዉጭ አንድ እርምጃ ወደፊት መሄድ እንደማንችል ለማሳየት እንጅ።

የሕወሃት ባለስልጣናት ችግር መኖሩን መረዳታቸው ተገቢ ነው። መፍትሄ የሚፈለገው ችግር እንዳለ መረዳት ሲጀመር ነው። አቶ ካሳ ተክለ ብርሃን በመቀሌው ስብሰባ እያለቀሱ መናገራቸውን ስምተናል። “አቶ ካሳ ተክለ ብርሃን በመቀሌው ጉባኤ ላይ አለቀሱ የሚል ነገር ሰማሁ፡፡አቶ ካሳ ለወደፊቱ ሽንኩርት እየከተፉ ስብሰባ ላይ አይሳተፉ” እያለ እንደቀለደው ጦማሪ ስዩም ተሾመ፣ ለእኝህ ባለስልጣን እምባ ቦታ የሚሰጥ ዜጋ ይኖራል ብዬ አላስብም። ለማስመሰል ይሁን ከልብ ከተናገሯቸው አባባሎች መካከል የተወሰኑቱን በጣም የምጋራው መሆኔን ግን ሳልገልጽ ማለፍ አልፈልግም። “አማራና ትግራይ በጎንደር ተጣልተው ሽምግልና ተቀመጡ ሲባል በእውነት ያማል። ጎንደር የአቢሲንያ ርእሰ ከተማ ነው። የጎንደር መነሻ አክሱም ነው። በአክሱምና ጎንደር መካከል ልዩነት መፈጠር የአቢሲንያ ጉድ ነው። ውድቀት ነው። እናም ያማል “ ነበር ያሉት፣ የጎንደርና የትግራይ ህዝብን ትስስር ሲገልጹ። ትክክል ናቸው። እንደ እውነቱ ከሆነ ጎንደሬ ሆኖ ትግሬነት የሌለበት ይኖራል ብዬ አላስብም። ይሄ ሰሜን ጎንደር የሚኖር በአማራነት ስም ጸረ-ትግሬ ጦማር የሚለቀልቀው ሁልአ ወረድ ሲል አያት ቅድመ አያቶቹን ቢመረመምምር፣ ጎይቶሞችንና ትብለጾች ያገኛል።

አቶ ካሳ እተፈጠረ ነገር መታመማቸው ማለፊያ ነው። ግን አንድ ነግር መረሳት የለበትም። አቶ ካሳ አሁን ነው ያመማቸው፤ እኛ ግን ላለፉት 25 አመታት ነበር ሲያመን የነበረው። ለስልጣን እንዲያመቸው አገሪቷን በዘር በመሸንሸን፣ “ይሄ መሬት የአማራ፣ ያ መሬት የኦሮሞ፣ እዚያ ማዶ የትግሬ” እያለ ፣ ዜጎች በሚያስተሳስራቸው ነገር ላይ ሳይሆን በሚከፋፍላቸው ጉዳዮች ላይ እንዲያተኮሩ፣ እርስ እርስ እንዳይተማመኑ፣ እንዲከፋፈሉ ሲያደርግ የነበረውና አሁንምም እያደረገ ያለው፣ እርሳቸው “ያማል” ላሉት ነገር ተጠያቂ የሆነው፣ እርሳቸው አመራር አባል የሆኑበት አገዛዝ አይደለም እንዴ ? በዚሁ በመቀሌ ስብሰባ “የጥላቻ ዘርን በመዝራት የፍቅር አዝመራን መሰብሰብ አይቻልም” እንዳሉት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ይህ አሁን የሚታየው ከዘር ጋር የተገናኘውን፣ የጥላቻና እና የዘረኝነትን ዘር እራሱ ሕወሃታ እነ አቶ ካሳ ያሉ አገልጋዮቹ ዘርተው አሁን እንዴት ፍቅር እንዲሰበሰብ ይጠብቃሉ ?

እስቲ የወልቃይት ጉዳይን እንመልከት። ወልቃይት ጠገዴ የሚኖረው ህዝብ አማራ፣ ትግሬ ሳይባባል ለዘመናት በጎንደር ጠቅላይ ግዛት ሥር እንደ ወልቃይቴ ሲኖር የነበረ ሕዝብ ነው። ትግሬው፣ ከአማራው ተዋልዶ፣ ተደባልቋል። አብዛኛው ሕዝብ አማርኛም ትግሪኛም ይናገራል። ሲያሻው ሽሬ፣ ሲያሻው ጎንደርና ደባርቅ ሄዶ ይነግዳል። ወልቃይት ጠገዴ የፍቅር፣ የትስስር ተምሳሌት ነበረች። ሆኖም አንድነት፣ ፍቅርን ከማጠናከር ይልቅ ሕወሃት የትግሬነት ማንነት በወልቃት ህዝብ ላይ ለመጫን ተሞክረ (የኦነግ ጠባብ ፖለቲክ ያሰከራቸው አክራሪዎች የኦሮሞ ማንነት የሚሉትን አዲስ አበባና ሌሎች የኦሮሚያ ትላልቅ ከተሞች በሚኖርው ህዝብ ላይ ለመጫን እንደሚሞክሩት)። በግድ ትግሬ ነህ ሲባል፣ ህዝቡ ተፈጥሯዊ ነውና ተቃወመ። ህወሃቶች የዘር ካርድ መዘው በዘር ጨዋታ ሲንቀሳቀሡ ሌላዉም ሳይወድ በግዱ የዘር ጨዋት ካርድ ለመምዘዝ ተገደደ። ከሁለተኛ አለም ጦርነት በኋላ የበርሊን ከተማ ለሁለት ተከፍላ ነበር። ያ የሆነበት ምክንያት በራሺያና በአሜሪካ መካከል የርዮት አለም ልዩነት ስለነበረ ነው። በራሺያ እነ ጎርባሾቭ ሲመጡ በበርሊን የነበረው ግንብ ፈረሰ። ከተማዋ እንደጋና አንድ ሆነች። አሁንም ህወሃት ያመጣው የዘር ፖለቲካ ለምሳሌ አንድ የነበረውን የጠገዴ ህዝብ፣ ለሁለት ከፍሎታል። ጠገዴና ጸገዴ በሚል። እንደ ሞያሌ፣ ዲላ ያሉ ከተሞችን ለሁለት ክፍሏል።

የበርሊን ግንብ እንደፈረሰው፣ በጠገዴ/ጸገዴ በሞያሌ፣ በዲላ … ያለውም የዘር መከፋፈል ግንብ ካልተደረመሰ አሥር ሺህ ጉብዬ ቢደረግ የሚለወጥ ነገር አይኖርም። የትግራይ ክልል መንግስት፣ ሕወሃት፣ በሃይልና በጉልበት፣ ያለ ሕዝቡ ፍላጎት፣ በዚያ የሚኖረውን ህዝብ አፈናቅሎና ለስደት ዳርጎ ፣በግድ ትግሬ ነህ እየተባለ፣ በአማርኛ እንዳይማርና በአማርኛ የመንግስት አገልግሎት እንዳያገኝ ተከልክሎ ፣ በወልቃይት ጉዳይ ህዝብ ወክሏቸው ሰላማዊ በሆነ መንገድ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ዜጎች በግፍና በጭካኔ እየተሰቃዩ፣ በሁሉም የአገሪቷ ክፍሎች የሕወሃት የበላይነት ገኖ፣ እንዴት ነው እርቅ ሊመጣ የሚችለው ? አቶ ካሳ መቀሌ ሄደው ከሚያለቅሱ ለምን በሚኒስትሮች ምክር ይሁን በአሕአዴግ ፖሊት ቢሮ ስብሰባ ላይ ወልቃይትን ጨምሮ፣ በጎንደር በጎጃም..የሚኖረው ሕዝብ የጠየቃቸውን መሰረታዊ ጥያቄዎቹ እንዲመለሱ ለምን አይተጉም? እዚያው ጓዶቻቸው መካከል ለምምን አያለቅሱም ?

ከፈሩሱ በፊት ጋሪው አይቀደም ያልኩት እንግዲህ ይሄንን ነው። እንደውም ጉባዬ፣ ስብሰባ አያስፈለግም። በሕዝብና በሕዝብ መካከል ችግር የለም፣ ኖሮም አያውቅም። ችግር ፈጣሪዎቹ ፖለቲከኞችና ስልጣን ላይ የተቀመጡት ናቸው። እነርሱ ባመጡት ጣጣና የዘር ፖለቲካ ነው አገር እየታመሰች ያለችው። ስለዚህ የዘር ጨዋታ ካርዶች ወደ ገደል እየተጣሉ አዲስ ፣ ጤናማ፣ ህዝብን የሚጠቅም፣ በሰብአዊነት ላይ ያተኮረ ጨዋታ መጀመር አለበት። እነ አቶ ካሳ በርግጥም እየተፈጠረ ባለው ነገር ሕመም ከተሰማቸው፣ ፍቱን መድሃኒት እንዲመጣ ማድረግ አለባቸው። እርሱም ከናካቴው ከዘር ፖለቲክ በመውጣት፣ ትግሬ፣ አማራ፣ ኦሮሞ መባባሉና ሁሉንም፣ ነገር በዘር ሂሳብ ማስላቱ ቆሞ፣ ዜጎች በሁሉም የአገሪቷ ግዛት፣ ባህላቸው፣ ቋንቋቸው ተከብሮ፣ ሁሉም የአገሪቷ ግዛት አገራቸው መሆኑን አምነውና ተረድተው፣ ያም በሕግ በማያሻማ መንገድ ተረጋግጦ፣ እንዲኖሩ መደረግ አለበት። አሁን ያለው ፌዴራል አወቃቀር ተሰርዞ ወይም ተሻሽሎ፣ አዲስ ዘመናዊ፣ በቋንቋ ላይ ብቻ ሳይሆን በባህል፣ በታሪክ፣ በሕዝብ አሰፋፈር በኢኮኖሚ፣ በጂዮግራፊ፣ በሕዝብ ፍላጎትና በአስተዳደር አመችነት ላይ የተመሰረተ የዘመኑን ትዉልድ የሚመጥን አወቃቀር ያስፈልገናል።

አንድ ሰው መጥበብ፣ ጎሰኛና መንደርተኛ መሆን ከፈለገ፣ ትግሬነትን፣ ኦሮሞነትን፣ አማራነትንን ..ማቀንቀን ይችላል። ያ መብት ነው። ሆኖም ግን በመንግስት ደረጃ አጼ ቴዎድሮስ “ሃይማኖት የግል አገር የጋራ” እንዳሉት፣ እኔም ዘርን ጨምሬ “ሃይማኖትና ዘር የግል አገር የጋራ” ይሁን እላለሁ። በዚህ ረገድ ገዢዎች መሰረታዊ የአካሄድ ለውጥ በቶሎ እንዲያደርጉ እመክራለሁ።

(ከዚህ በታች የምታይዋቸው በግፍና በጭካኔ ፣ “አማራ ናችሁ” ተብለው የተፈናቀሉ ናቸው። በጎንደር የነበሩ ጥቂት የትግራይ ተወላጆች፣ ጎንደር በነበረው እንቅስቃሴ ስለፈሩ በፍቃዳቸው ጎንደርን መልቀቅ በፈለጉ ጊዜ በቦይንግ ነው ወደ መቀሌ እንደሄት፣ እነዚህ ወገኖች ቦይንግ አይደለም የፈረሰ ጋሪ አልቀረበላቸውም። ሳይፈልጉ በግድ ነው፣ ኪሎሜትሮች በማቋረጥ በእግር የተፈናቀሉት። በተለይ በአርባ ጉጉና በበደኖ ብዙዎች በጭካኔ ተግድለዋል። ከመተማ አካባቢ ወደ ሱዳን ተሰደው ለነበሩ የትግራይ ተወላጆች መልሶ ማቋቋሚያ በሚል በአሥር ሚሊዮኖችች የሚቆጠር ገንዘብ በክልሉ መንግስትና እንደ ሶማሌ ክልል ባሉ ሌሎች የክልል መንግስታት ሲሰበሰብ፣ የመንግስት ሜዲያ የነዚህ የትግራይ ወንድሞቻችንን መፈናቀል በስፋት ሲዘግብ፣ እዚህ ፎቶ ላይ ያሉ ወገኖቻችን ግን ዞር ብሎ የተመለከታቸውም የለም። በነርሱምም ጉዳይ የተጠራ ጉባዬ የለም)

Share this post

One thought on “አቶ ካሳ ተክለብርሃን እዚያው ጓዶቻቸው ጋር ያልቅሱ!

 1. >» ሰሞኑን አንድ የሰሜን ሰው ወዳጄ….ህወአት እና ብአዴን እርቅ ለማድረግ ዘመዶችህ ብትሬን ጥምጣሜን ሳይሉ ፬፻ ሆነው አድዋ ተመሙ(ተርመሰመሱ)አልኩት…ሰውዬውም ዋዛ አደለም ምነው ምን ተገኘ? አለኝ…እንግዲህ ነጻ ሊወጡ እኛን ሊያስሩ ማኒፌስቶ ያወጡበት ቦታ ሄደው እንደገና ለ፶ ዓመት ተማማሉ መሰለኝ ብለው…”ለመሆኑ ሽምግልና ጥሩ ሀገራዊ እሴት ነው ታዲያ ፴..፵ አልፎም ፶ ሽማግሌ አይበቃም? አለኝ አይ ልማታዊ አማሮችን የአለቆቻቸውን የአፓርታይድ ሠፈር አሳይተው ለማስጎምጀት ይሆናል ብለው አይ ፬፻ ሰው ለጦርነት ሲሰለፍ እንጂ ለሽምግልና ሲጠራ አይቼም ሰመቼም አላውቅም”። አለኝ ጭራሽ ለቅሶም እንደነበር አቶ ካሳ ተከለብርሃንን አሳየሁትና ተማመንን…ጉድ ነሽ የአንኮበር ቅጠል!
  *****! እንደልማዳቸው የሚያስተምሩን አቶ ጌታቸው ረዳ ተርጉመው ከከተቡት እንዋስ…ድንቄም ሽምግልና!? *****
  “ፋሺሰትነት ለኢትዮጵያ አዲስ አይደለም። በታሪካችን በመልክ ይለያዩ እንጂ በብዙ ተግባር አንድ የሆኑ ‘ፋሺስታዊ’ ክስተቶች በሕዝባችን ላይ ተከናውኗል። ፋሺስትነት ሕዝባዊ/ጅምላዊ/ ጭፍጨፋ ነው። አሁን ያለው የወያኔ ትግሬዎች ፋሺዝም ለየት የሚያደርገው፤ጥንት ከታየው ‘ሃይሞኖታዊ ፋሺዝም’ (ግራኝ አህመድ.. ጉዲት..) ለየት ይላል። የእነግራኝ፤ የነ ጉዲትና የነሙሶሎኒ… በግለሰብ የተመራ ነበር። የትግሬ ፋሺዝም ከሌሎቹ ለየት ይላል። በግለሰብ እና በቡድን እየተፈራረቀ የሚጓዝ ነው። ሁሉም ፋሽቶች ‘አገር ወዳዶች ናቸው”። የትግሬ ፋሺዝም ግን “ጎሳ ወዳድ ነው”። ሌሎች ፋሺስቶች፤ አገራቸው በባዕድ እንዲረገጥ አይወዱም። ታሪክ ወይንም አገራዊ ክብር፤ ሰንደቃላማ፤ መሬት፤ ድምበር ፤ ወደብ፤ የሕዝብ ባሕል፤ ሃይማኖት ለጠላት አሳልፈው አይሰጡም (አገራቸው ከከብራቸው ጋር ስለሚያ ያ ይዙት እጅግ ውድ እሴት ነው ስለሚሉ)። እነ ሙሶሎኒ አስከፊ ቢሆኑም ሲበዛ በጣም አክራሪ አገር ወዳዶች (Aggressive nationalist) ናቸውና አገራቸውን እጅግ አንደ ብሌን ያያሉ። የትግሬው ፋሺስት ቡድን ግን የተቃራኒው ነው (ልዩ የሚያደርገውና የሚያስገርመው ደግሞ ይህ ባሕሪውና እርምጃው ነው)። “ትግራይ የመላ አካባቢያችን “ሲም ካርድ” (Sim Card) ነች። ስልክ ቁጥር፤ ምን፤ ምን ታሪክ የያዘች ነች። ትግራይ የታሪክ ቀፎ ነች። የአካባቢያችን ቀፎ ነች። ትልቁ የቴሌፎን ሞባይል ‘ያለ ደቃቃዋ/ትንሿ “ሲም ካርድ” ህይወት የላትም። ትግራይ ማለት ደግሞ እንዲሁ የሁሉም አካባቢያችን ክልሎች/አገሮች/ቦታዎች ሁሉ “ሲም ካርድ” ነች። ያለ ትግራይ ሁሉም አካባቢዎች ታሪክ የላቸውም። መነሻው እኛ ነን። ሁሉም የሚጀምረው ከትግራይ ነው፤ “ሃይማኖት፤ ፖለቲካ፤ ስልጣኔ…. መነሻዎች እኛ ነን። (ዶ/ር ሙሉወርቅ ኪዳነማርያም)
  ___፟ (አማራዎች) ወልቃይትን በሚመለከት አንድም የሚሟገቱበት መጽሐፍ እስካሁን ድረስ ያሳተሙት ነገር የለም። ዘፈን ግን አዎ! እንኳን ለነሱ ሰዎች፤ የነሱ ያልሆነውን ሁሉ፤ ዘፈን እየዘፈኑ “አስክስታ አስጨፍረውታል”። እንኳን የኑሰ የሆነ “የኛም ሰው” አስጨፍረውታል። (ዶ/ር ሙሉወርቅ ኪዳነማርያም)
  ****”አማራዎች በሙዚቃ ቃናቸው ትግሬዎችን ማስተማር፤ማስጨፈር የተካኑት ብቻ ሳይሆን በመጻፍም መጻፍ የጀመሩት ከትግሬዎች ቀድመው ነው።ትግርኛ የሚባል አክሱምን የወረሩ ‘የቤጃ ጦሮኞች እና ሰፋሪዎች’ በዛሬው ትግራይ ውስጥ ተበትነው ሲኖሩ ከግዕዝ፤ከቤጃና ከአማርኛ ደባልቀው የፈጠሩት ‘ትግርኛ’ አክሱም ውስጥ ተጽፎ የተተወ ማስረጃ የለም። ምከንያቱም ትግርኛ እራሱ የጽሑፍ ከመሆኑ በፊት መነጋገሪያ ብቻ ነበር። ትግርኛ መደመጥ የተጀመረው ወይንም ትግራይ/ትግሬ የሚለው ቃል ከወደ 7ኛ ክ/ዘመን መጨረሻ አካባቢ እንደሆነ ይነገራል። በደምብ የታወቀው ግን በጣም ቆይቶ ነው። አማራዎች ግን ጽሑፋቸው ትተውት የሄዱት አክሱም ውስጥ ነው። የዛሬ ትግሬዎች አማራዎች ታሪካችን፤ ጽሑፋችን ነጠቁን የሚሉት፤ አማራዎች ከዘፍን ውጭ የሚያወቅት ነገር የለም የሚለው “ድንቁርና” በሙሉወርቅ ቃላት ልጠቀም እና “ትግሬዎች አደብ ብንገዛ መልካም ነው”። ምክንያቱም አማራዎች አክሱም ውስጥ ነበሩ፤ ፁሑፋቸውም ይመስክራል፡ “ማኒኤል በራዳ” እንዲህ ይላል፡
  “…..inscription with letters on one side in `Amharic’ of an ancient style, and on the other letters which appeared to be Greek or Latin. The thrones are described, and also the `Tomb of Kaleb and Gabra Masqal’.”
  ይህስ ትግሬዎች ናቸው የጻፉት? ጽሑፉስ ‘ትግርኛ’ ነው ወይስ ‘አማርኛ’? ዘመኑስ? ቦታውስ? አክሱም ነው? ትግሬ ነው? ኤርትራ ወይስ የት ነው? ጹሑፉ አማርኛ ስላለው የትግሬ ፋሺስቶች ጎዳናዎች፤ ታሪካዊ ገጠሮች፤ ከተሞች፤ ተራሮች፤ ወንዞች፤ በወያኔ ታጋይ ስሞች እየተኩ ጥናት ለማካሄድ ወደ ስፍራው በሚመጡ የታሪክ ተማራማሪዎች ፍለጋ እንዲሰወሩ/እንዳይታወቁ/ እያደረገ አንዳለው ወንጀል፤ ይህ ማስረጃም ‘አማርኛ’ጽሑፍ ስለሆነ ሰባብረው ጥለውት ይሆናል ወይንም እንደማይነበብ ወቅረውት ይሆናል። አማራን የሚጠላ ቡደን አያደርግም አይባልም። ወደብን ለዓረብ የሰጠ ቡደን ይህ አያደርግም አንልም።”….(
  ___ አማራ ከ 13/14 ክፍለ ዘመን የተፈጠሩ ናቸው። ወልቃይት ከዚያ በፊት አለ።ወልቃይቶች ከ‘አክሱም’ በፊት የነበሩ ናቸው። ወልቃይቶች በዘመነ ጉዲትም ነበሩ። እነሱ የታሪክ ማስረጃ/ክርክር አያደርጉም። ክርክራቸው። የሰሊጥ አገር ‘ትግሬዎች’ወሰዱት’ ምንትስ ምንትስ ነው ክርክራቸው፡ ይኼው ነው ሙግታቸው። (ዶ/ር ሙሉወርቅ ኪዳነማርያም)
  ዶ/ር ሙሉወርቅ ንግግሩን ስመዝነው፤ የወልቃይት ምሁራን እና ሌሎች ኢትዮጵያዊያን እያሳተሙዋቸው ያሉት ጽሑፎች እና የታሪክ መጽሀፍቶች፤ የተከታተለ አይመስልም። የጥንት ስማቸው እንደያዙ የሚጓዙት የወልቃይት አማራዎች ትግሬዎች ‘ሰሊጥ የምንዘራበት ለም መሬታችን ዘረፉን” ብለው ቢሉ ሕጋዊ ጥያቄ ነው። ሰሊጥ የሚያመርት ወልቃያት ሑመራ ተወሰደብን ብሎ አይደለም እንዴ ‘ወያኔ’ ወደ ትግሬ ያጠቃለለው? ለነገሩ- ሰሊጥ ብቻ አይደለም ክሱ፤ የዘር ማጽዳት ክስም ነው!!!! ወልቃይቶች ትግሬዎችን እየከሰሱ ያሉት። አደብ አደብ፤ ወያኔዎች የትግራይን ሕዝብ ወዴት እየመሩት ነው? አምና የታየው “አማራዎች ያሳዩት የቁጣ ቁጭትና መዘዙ” ትግሬዎች መማር አልቻልንም? ደወሉ አይሰማንም ወይ? ትግሬዎች ወያኔዎችን በተሎ አስወግዱዋቸው። ወደ አደገኛ ጭለማ ውስጥ እየከተቱን ነው። ልብ እንግዛ!!!!!!!!
  ____የመሬት ጥያቄ እየጠየቁ ‘ወንድማማቾች ነን’ ቢሉን አንሰማቸውም። ወንድምህ ከጠላህ ወዳጅነት፤ ወንድምነት የሚባል የለም። በማለት የዓድዋው ሰው ‘ ሙሉወርቅ’ በምሳሌ እየመሰለ አድማጩን አስቋል።\(ዶ/ር ሙሉወርቅ ኪዳነማርያም)
  “የአማራ ብሔር/ሕዝብ” ቀንደኛ ጠላታችን ነው ፤ ስለሆነም ሰላምና ዕረፍት ማግኘት የለበትም፤ብሎ ከ 40 አመት በፊት በማኒፌስቶ ሕዝብን የቀሰቀሰ የናዚ ቡድን ‘ወንድማማቾች ነን” ብለው ለሚሉን አማራዎች የሚያዳምጥ ጀሮ ከየት ሊያመጣ ይችላል? ያልተፈጠረበት ጀሮ ከየት ይፈጥረዋል!
  ____ ትግራይ የኢትዮጵያ ‘ ሲም ካርድ’ ነች። እኛ ትግሬዎች ኢትዮጵያዊያን ሳይሆነ፤ ኢትዮጵያን ያደረግን የመሰረትን ነን። የእኛ ኢትዮጵያዊነት ‘ ምስክር’ አያስፈልገንም፤ ምስክር የምንሆንለት ካልሆነ በቀር። ብያምኑም ባያምኑም፤ ሃቁ ያ ነው። (ዶ/ር ሙሉወርቅ ኪዳነማርያም)
  ይህንን ፋሺስታዊ ትምክሕት ደጋግሞ ተናግሮታል። ትንሽ ነካክቼዋለሁ፤ የተቀረው ለናንተው ልተው።
  13) ትግራይ ውስጥ ያልተደረገ ታሪክ የለም። ሁሉም የኛ ነው። ጥልፍ መጥለፍ፤ የሴቶች ጸጉር አሰራር ዘፈን/ሙዚቃ፤ የፊደል ጽሁፍ ጥበብ ሁሉም የትግሬዎች ነው። እነዚህ ሁሉ ግን (አማራዎች)የኛ ነው እያሉ እየወሰዱት ነው። “አሰርቲቭ” መሆን አለብን። አስቀድሜ እንደገጽኩት አሞኝ ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ክሊኒክ ሄጄ፤ ጥዋት ነው፤ ተራ ይዤ እንዳለሁ፤ “ዛሬ ስንት ቀን ነው?” አለችኝ። “በኢትዮጵያ ነው ወይስ በፈረንጅ?” ስላት “በአማርኛ አለችኝ” “እኔ ደግሞ ‘በትግርኛ ነው የማውቀው” አለኳት። “አሰርቲቭ” ማለት ይኼ ነው። እኛ ነን መጀመሪያ የቀን መቁጠሪያውም ያወጣነው (“አመራ” አይደለም) ማለት አለብን። እንዲያ ካላደረግናቸው “አደብ” ጸባይ አያደርጉም። ደብተር ስንገዛም “የአማርኛ ደብተር” ብለን ከገዛን፤ “ለትግርኛ’ የማይሆን ደብተር ለምን እንገዛለን? አማራ አልሰሩትም። ደብተርን የሰሩ ፤ ለእንግሊዝኛ፤ ለማንኛ….ለማንኛውም የሚያገለግል ነው። ሳይሰሩ የኛ ነው፤ አማርኛ ደብተር እያልን መጥራት ስሕተት። ሳይሰሩ “በጨው ደንደስ በርበሬ ተወደስ” ነው። (ዶ/ር ሙሉወርቅ ኪዳነማርያም)
  ይህም ለናንተው ልተው።
  ____”እኛ ትግሬዎች ልባችን አንድ ነው፤ ስሜታችንም አንድ ነው።” (ዶ/ር ሙሉወርቅ ኪዳነማርያም)
  ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም ‘የትግሬዎች አስተሳሰብ እንደ ካንድ ፋብሪካ እንደወጣ ሳሙና ሁሉም አንድ አይነት አስተሳሰብ አለው” ብለው ፕሮፌሰር ወ/ማርያም ሰደቡን እያለ እራሱም ሆነ እነ ገብረኪዳን ደስታ እሪ እያሉ ፕሮፓጋንዳ ሰርተው መስፍን ወ/ማርያም ‘ጸረ ትግሬ ነው’ እያሉ ሲወራጩ እንዳልነበረ፤ ዛሬ ያንን ተረስቶ “ትግሬዎች ልባችን እና ስሜታችን አንድ ነው” ሲል ከመምህር ሙሉወርቅ ኪዳነማርያም መስማታችን፤ ፕሮፉሰሩ አልተሳሳቱም ነበር። ትግሬዎች ሲሉት ልክ የሚሆነው፤ ሌሎች ሲሉት ግን ልክ የማይሆነው እና በያዙኝ ልቀቁኝ የምንወራጭበት መብት እንዴት ሊከሰት ቻለ? ብየ ጽሑፌን የትግሬ ፋሺዝም ዓይኑ በሚያስፈራ ደራጃ አድጎ አገሪቷን ወደ መሃምቅ እየገፋት እንደሆነ፤ ማስረጃዎች አቅርቤላችኋል። የመቀበል፤ያለመቀበል የናንተው ነው። ጨርሻለሁ።
  አመሰግናለሁ ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ – ሰማይ አዘጋጅ)

  Reply

Post Comment