አቶ ዳውድ ኢብሳ በድጋሚ በጸጥታ ኃይሎች ወደ ቤታቸው መወሰዳቸውን ግንባሩ አስታወቀ

Source: https://www.zehabesha.com/amharic/archives/109014

ከቀናት ቆይታ በኋላ ወደ ጽህፈት ቤታቸው ተመልሰው የነበሩት የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ በድጋሚ በጸጥታ ኃይሎች ወደ ቤታቸው መወሰዳቸውን ግንባሩ አስታወቀ። አቶ ዳውድ በጸጥታ ኃይሎች ተገደው ወደ ቤት እንዲመለሱ የተደረጉት «ለደህንነታቸው ሲባል ነው» የሚል ምላሽ ማግኘታቸውን የግንባሩ ቃል አቃባይ ቀጄላ መርዳሳ ለዶይቸ ቬለ ተናግረዋል። የግንባሩ ሊቀመንበር በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች ጥብቅ ቁጥጥር ስር መሆናቸው በዕለት ተዕለት ስራቸው ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳደሩንም አቶ ቀጄላ ተናግረዋል።«ባለፈው ጊዜም እንደተነገረው ከእርሳቸውም አንደበትም የሰማነው ለደህንነታቸው ተብሎ ነው ። ነገር ግን ይሄ ጉዳይ በስራቸው ላይ ቢሮአቸው ለመሄድ ተጽዕኖ አለው»ቀደም ሲል የግንባሩ ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ባልተገኙበት በተወሰኑ የስራ አስፈጻሚ እና የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት አማካኝነት ተከናውኖ

The post አቶ ዳውድ ኢብሳ በድጋሚ በጸጥታ ኃይሎች ወደ ቤታቸው መወሰዳቸውን ግንባሩ አስታወቀ appeared first on ዘ-ሐበሻ (ZeHabesha) Latest Ethiopian News Provider 24/7.

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.