አክሱም ጽዮንና የኢትዮጵያ ማኅጸን

Source: https://mesfinwoldemariam.wordpress.com/2020/05/29/%E1%8A%A0%E1%8A%AD%E1%88%B1%E1%88%9D-%E1%8C%BD%E1%8B%AE%E1%8A%95%E1%8A%93-%E1%8B%A8%E1%8A%A2%E1%89%B5%E1%8B%AE%E1%8C%B5%E1%8B%AB-%E1%88%9B%E1%8A%85%E1%8C%B8%E1%8A%95/
https://2.gravatar.com/avatar/e16ba1b5076af05a353317291dcf50ae?s=96&d=identicon&r=G
መስፍን ወልደ ማርያም
ግንቦት 2012
የኢትዮጵያ ማኅጸን የሆነው ትግራይ ከዚህ በላይ ቆሻሻ ለመሸከም ትእግስት እንደሌለው እየገለጸ ነው፤ ለእኔ እንደሚመስለኝ የኢትዮጵያ ትንሣኤ ዋዜማ ነው፤ አክሱም ጽዮንም ለኢትዮጵያ አደራ አለባት፤ አክሱም ጽዮን የወንጀለኞች ምሽግ አትሆንም፤ የኢትዮጵያ ማኅጸን የሆነው ትግራይ የወንጀለኖች አለኝታና መከታ ሆኖ አይኖርም፤ የኢትዮጵያ ማኅጸን የሆነው ትግራይ በጎሠኞች ጎራ ገብቶ ኢትዮጵያን ለማናጋት አይሰለፍም፡፡
በቃ! ኢትዮጵያ ታበጽሕ ዕደዊሃ ኀበ እግዚአብሔር!
በበሩ አደባባይ የሚገሥጸውን ጠሉ፤እውነትን የሚናገረውን ተጸየፉ፤ድሀውንም ደብድባችኋልና የስንዴውንም ቀረጥ ከእርሱ ወስዳችኋልና፣ ከተጠረበ ድንጋይቤቶችን ሠርታችኋል፤ ነገር ግን አትቀመጡበቸውም … ጻድቁን የምታስጨንቁ፣ ጉቦንም የምትቀበሉ፣ በበሩም አደባባይ የችጋረኛውን ፍርድ የምታጣምሙ፤ እናንተ ሆይ በደላችሁ እንዴት እንደበዛ፣ ኃጢአታችሁም እንዴት እንደጸና እኔ አውቃለሁና፤ ስለዚህ ክፉ ዘመን ነውና …አሞጽ 5/10-13

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.