አየር መንገዱ ከአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት ጋር የአጋርነት ስምምነት ተፈራረመ

አየር መንገዱ ከአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት ጋር የአጋርነት ስምምነት ተፈራረመ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ አየርመንገድ እና የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት (ዩ.ኤስ.ኤይድ) ጋር የአጋርነት ስምምነት ተፈራረሙ፡፡
 
የአጋርነት ስምምነቱ የግብርና ውጤቶችን በሃገር ውስጥ ካለው አርሶአደር ለማግኘት ያለመ ነው ተብሏል፡፡
 
አየር መንገዱን የግብርና ውጤቶችን ለደንበኞቹ ለማቅረብ እንደሚያስችለው አስታውቋል፡፡
 
ኢትዮጵያና አሜሪካ በአጋርነት ለ100 ዓመታት መስራታቸውን መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
 
ባለፈው ዓመት ኢትዮጵያውያን አርሶ አደሮችና አነስተኛ ንግድ አንቀሳቃሾች ከ1 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በላይ ማግኘታቸውን የአሜሪካ ኤምባሲ መረጃ ያሳያል፡፡

The post አየር መንገዱ ከአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት ጋር የአጋርነት ስምምነት ተፈራረመ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply