‹‹አዲስ አበባ ስለሰላም ተናግሬ ከዚያ ሌላ ብናገር ይጠይቀኛል፤ ሄጄ የምሠራውም ከዚህ እንደምናገረው ነው፡፡›› አቶ ገዱ አንዳርጋቸው

Source: https://mereja.com/amharic/v2/84698

‹‹አዲስ አበባ ስለሰላም ተናግሬ ከዚያ ሌላ ብናገር ይጠይቀኛል፤ ሄጄ የምሠራውም ከዚህ እንደምናገረው ነው፡፡›› የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው
‹‹ይህች መሬት ሄደች ለኛ አጀንዳ አይደለም፤ ሊያጋጨንም አይገባም፡፡ ሕዝቡም ግጭት አይፈልግም፤ የአማራ ሕዝብ ከግጭትም አትርፎናል እላለሁ፡፡›› የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል
(አብመድ)
የአማራና ትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳድሮች በአዲስ አበባ ሂልተን ሆቴል ከሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ጋር እየተወያዩ ነው፡፡ በመድረኩም ሁለቱ ርዕሰ መስተዳድሮች ንግግር አድርገዋል፡፡
የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ‹‹ስለሰላም ተጨንቃችሁና አስባችሁ ባሕር ዳርና በሌሎችም ክልሎች ተዘዋውራችሁ አስተምራችሁናል፤ መክራችሁናል፡፡ ይህ ደግሞ ከሃይማኖት አባቶች፣ ሽማግሌዎችና እናቶች የሚጠበቅ ነው፡፡ የሰላም አጀንዳ ይዛችሁ በዚህ ወቅት በመንቀሳቀሳችሁና እንድንገናኝ ጥረት ስላደረጋችሁ በአማራ ክልል ሕዝብ ስም አመሠግናለሁ›› ብለዋል፡፡

‹‹ኢትዮጵያ ሰላም እንድንትሆን የምንመኛው ስለሆነ አካል ብለን ሳይሆን ለሁሉም መሠረት ስለሆነ ነው፡፡ ትንሽ ጊዜ እንኳ ግጭቶች ሲኖሩ ምን ያህል ጉዳት እንደሚደርስ እያየነው ነው፡፡ የአማራ ሕዝብ ከወንድሞቹና ከጎረቤት ክልሎች፣ ከትግራይ ሕዝብ ጋር ሰላም መሆን ይፈልጋል፤ ለዚህ የሰላም አጀንዳችሁም አመሠግናለሁ፡፡ የምመራው ሕዝብም ሰላም ይፈልጋል፤ ለመሥራት፣ ለመኖር፣ ለመሻሻል… የሚፈልግ ነው፡፡ ይህንንም ስታወያዩት ነግሯችኋል፡፡ እኔም ዝግጁ ነኝ፡፡ ሰላምን የሚጠላው ሰይጣናዊ አስተሳሰብ የተጠናወተው ነው›› ነው ያሉት አቶ ገዱ፡፡
‹‹የአማራና ትግራይ ሕዝቦች ለሺህ ዘመናት የጋራ ሃይማኖት፣ ባሕልና እሴት ያላቸው አንዱ በአንዱ የሚሰጋ ሳይሆን የሚኮራ ሕዝቦች ናቸው፤ ይህ ግን ከጊዜ ጊዜ እየተሸረሸረ መጥቷል፡፡ ሕዝቡ ሰላማዊ ፍላጎቱ በሰላም እንዲፈታ እንጅ እንዲጋጭ

Share this post

2 thoughts on “‹‹አዲስ አበባ ስለሰላም ተናግሬ ከዚያ ሌላ ብናገር ይጠይቀኛል፤ ሄጄ የምሠራውም ከዚህ እንደምናገረው ነው፡፡›› አቶ ገዱ አንዳርጋቸው

  1. Melikt Lendenkorow Gedu OR Gindu : Ante Wushetam Ye aemro beshtegna mech new yetenagerkewn adrgeh mtawkew eski …ngeren bakh ..matreba worada , chnkilat yelehm enji ante ahun melkekia mtasgebabet gize neber eko ke ante Abdi ili Etf Etf adrgo yshalal . Gin aygebah min yderegal Denkoro !!!

    Reply

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.