አዲስ አበባ ዉስጥ ጫት ጠፍቷል – የሚገኘውም ዋጋው እጅግ ውድ ነው

Source: http://www.zehabesha.com/amharic/?p=81497

በአዲስ አበባ ዉስጥ ጫት በመጥፋቱ ሳቢያ የጫት ዋጋ በጣም መናሩን የጫት ተጠቃሚዎች ገለጹ። ቀደም ሲል 50 ብር እንገዛው የነበረው ጫት እስከ 150 ብር ደረሰብን የሚሉት ጫት ቃሚዎች ከእንግዲህ በኋላ ቃሚ ለመሆን ሐብታም መሆን ሳያሻ አይቀርም ሲሉ ቅሬታቸውን አሰምተዋል።


በኦሮምያ ዉስጥ የተከሰተውን ህዝባዊ እምቢተኝነት ተከትሎ የጫት ዝዉዉር መቀነሱን የሚያስረዱት የጫት ነጋዴዎች መደርደሪያዎቻቸው ባዶ መሆን ከጀመሩ ሰንበት ማለቱን አሳዉቀዋል።

ከፍተኛ የጫት ዝዉውር የሚደረግባትን የአወዳይ ከተማ ቀደም ሲል የህወሃት ኮንትሮባንድ የጫት ነጋዴዎች ተቆጣጥረዉት እንደ ነበር የኦሮሞ አክቲቪስቶች ያስረዳሉ። በመሆኑም የኦሮሞ ቄሮዎች ባደረጉት ተጋድሎ ወደ ጅቡቲና ሶማሊያ ይገባ የነበረው ጫት በጣም በመቀነሱ ጫት እንደ ዲፕሎማሲያዊ መሳሪያ ያገለገለበት ታሪካዊ ወቅት መሆኑ እየተነገረ ነው።

የጫት ንግድ ወ/ሮ አዜብ መስፍንን ጨምሮ የህወሃት ጀነራሎች ድረስ የተሳተፉበት የኮንትሮ ባንድ የንግድ መስመር መሆኑ በተደጋጋሚ ይነገራል። ህወሃት ወጣቱን ለማደንዘዝ ጫትን እንደ ፖለቲካዊ መሳሪያ ይጠቀምበታል የሚል ክስ ባለበት መልኩ ሰሞኑን በአዲስ አበባ ዉስጥ ጫት ስለተወደደና ስለጠፋ ቃሚው ወጣት በየጎዳናው ላይ ተኮልኩሎ መታየቱ ጫት አገሪቷ ልደርስበት የሚገባዉን የለውጥ ጉዞ ያሰናከለ መሆኑን አመላካች ነው የሚል አስተያየት አለ።
በርግጥ በየቀኑ በጫት ሐሳባዊ አለም (ምርቃና) ዉስጥ ሆኖ ጭቆና መኖሩ ዘንግቶ ዝምታ ዉስጥ የነበረው ወጣት እንደ ኦሮምያ ወጣቶች (ቄሮዎች) ይነሳ ይሆን ?በሒደት የሚታይ ይሆናል።

ጫት ኢትዮጵያ ወደ ውጪ ልካ ( export) የዉጭ ምንዛሪን የምታገኝበት ቢሆንም፥ በተለያዩ የመካከለኛው ምስራቅና የምእራብ አገራት ዉስጥ እንደ አደንዛዥ እጽ የሚቆጠር በመሆኑ ህገወጥ እንደሆነ ይታወቃል። (ቢቢኤን እንደዘገበው)

Share this post

Post Comment