አዲስ አበባ የመወዛገቢያ ርዕስ ሳትሆን ኢትዮጵያዊያን በጋራ የምንኖርባትና የምናሳድጋት ልትሆን ይገባል – ም/ከንቲባ ታከለ ኡማ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/132842

BBC Amharic : አዲስ አበባ ለሁሉም ኢትዮጵያዊያን የምትሆን ከተማ በመሆኗ ለውዝግብና አለመግባባት ምክንያት መሆን እንደሌለባትና የተለያዩ ሃሳቦችን በማቅረብ ልናሳድጋት እንደሚገባ ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) ለቢቢሲ ተናገሩ።
አዲስ አበባ የሃገሪቱ እምብርት መሆኗን የሚጠቅሱት ምክትል ከንቲባው የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት መቀመጫም መሆኗን ጠቅሰው “አዲስ አበባ ሁሉንም የምታቅፍ የሁሉም ከተማ ናት። ከተማዋ የመወዛገቢያ ርዕስ ሳትሆን ኢትዮጵያዊያን በጋራ የምንኖርባትና የምናሳድጋት ልትሆን ይገባል” ብለዋል።
አስተዳደራቸው የከተማዋን ነዋሪ ችግሮች ለመቅረፍ የተለያዩ እቅዶች እንዳሉት የተናገሩት ምክትል ከንቲባው፤ በአዲስ አበባ ውሰጥ ያለው የቤት ችግር በከተማዋ ካሉ ዋነኛ ጉዳዮች መካከል አንዱ መሆኑን ይናገራሉ።
የኢትዮጵያ መንግሥት በተለይ ደግሞ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለችግረኞችና ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የከተማዋ ነዋሪዎችን ችግር ለመቅረፍ በቤቶች ልማት በኩል ትልቅ የሚባል ተግባር አከናውኗል የሚሉት ምክትል ከንቲባው፤ የቤቶች ልማት ፕሮጀክትን በተመለከተ እስካሁን የነበረውን አሰራር በመለወጥ፣ በመንግሥት ሲከናወን የነበረውን የቤቶች ግንባታ የሪል እስቴት አልሚዎች እንዲገቡበት ይደረጋል ብለዋል።
ለዚህም “የከተማዋ አስተዳደር ከአንድ ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በማዘጋጀት የተለያዩ የገንዘብ ተቋማት እንዲሳተፉና በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የከተማዋ ነዋሪዎች ተጠቃሚ የሚሆኑበትን ሥርዓት ተግባራዊ ያደርጋል” ብለዋል።
በመጪው አዲስ ዓመትም በተለይ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸውና ለመንግሥት ሰራተኞች በርካታ ቁጥር ያላቸው የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ ይጀመራል ያሉት ከንቲባው፤ ግንባታው የሚካሄደው እንደከዚህ ቀደሙ በመንግሥት ሳይሆን በግል ተቋማት ይሆንና መንግሥት የመቆጣጠርና የማስተባበር ኃላፊነቱን እንደሚወስድ ተናግረዋል።
በከተማዋ ውስጥ የልማት ሥራዎች ሲከናወኑ አሳሳቢ ከሆኑት ነገሮች መካከል የሰዎች ከመኖሪያቸው መፈናቀል

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.