አዲሷ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፕሬስ ሴክሬተሪ በዜግነት ካናዳዊት ናቸው

Source: http://www.goolgule.com/the-new-press-secretary-billene-is-canadian/

በዚህ ሳምንት የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፕሬስ ሴክሬታሪ ሆነው የተሾሙት ወ/ሪት ቢልለኔ ስዩም ወልደየስ በዜግነት ካናዳዊት መሆናቸው ጥያቄ አስነስቷል። ሹመታቸውም በሥራ ላይ ያለውን ሕግ የሚጻረር ነው ተብሏል። ወ/ሪት ቢልለኔ ለማስተርስ ዲግሪ ያቀረቡትን ጥናታዊ ጽሁፍ “Transformative Spaces: Enabling Authentic Female Leadership Through Self Transformation – the Association of Women in Business” ወደሚል መጽሐፍ ቀይረው ባሳተሙት ገጽ 16 ላይ […]

Share this post

One thought on “አዲሷ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፕሬስ ሴክሬተሪ በዜግነት ካናዳዊት ናቸው

 1. የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፕሬስ ሴክሬታሪ ሆነው የተሾሙት ወ/ሪት ቢልለኔ ስዩም ወልደየስ በዜግነት ካናዳዊት መሆናቸው ጥያቄ አስነስቷል።
  አዋጅ ቁጥር 270/1994፣ ‹‹የኢትዮጵያ ተወላጅ የሆኑ የውጭ ዜጎች በትውልድ አገራቸው የሚኖራቸውን መብት ተጠቃሚነት ለመወሰን በወጣው ሕግ መሠረት፣ ማንኛውም የውጭ ዜግነት ያለው ትውልደ ኢትዮጵያዊ በማናቸውም የአገር መከላከያ፣ የአገር ደኅንነት ወይም በውጭ ጉዳይና መሰል የፖለቲካ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በመደበኝነት ተቀጥሮ መሥራት እንደማይችል ተደንግጓል፤›› ይላል፡፡
  በዚህም አዋጅ መሠረት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤትም እንደ አንድ ወሳኝ የፖለቲካ የመንግሥት መሥሪያ ቤት የውጭ ዜግነት ያላቸው ትውልደ ኢትዮጵያዊያን መቀጠር እንደማይችሉ፣ ሪፖርተር ያነጋገራቸው የሕግ ባለሙያዎች ያስረዳሉ፡፡
  ‹‹ይህ ጉዳይ መንግሥት ትኩረት ሊሰጥበት የሚገባው ነው፡፡ ምክንያቱም ዜጎች ለየትኛው ፖስፖርት ነው ታማኝነታቸው የሚለውን ጥያቄ ያስነሳል፤›› ሲሉ አንድ የሕግ ባለሙያ ተናግረዋል፡፡
  **************
  የዚህ ጉዳይ አንሺዎችና(ጋዜጠኞች) ሕጉን ያብራራው ባለሙያ(ጠበቃ) የሕጉን ትክክለኛነትና ጉድለትን አይተቹም!?ልዩ ጥቅማጥቅም
  በመሠረቱ የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦችን ( አበበ አበባና አቦቦች) ማለትን አንድ ነው ብሎ የተቀበለ ይህንንም ሕገመንግስት የሚቃወም ይሁን ማሻሻል ወይንም አንድ ቃል ቢያወጣ አፈነዳለሁ! አፈርሳልሁ! እገነጥላለሁ! ለሚሉ ዲያስፐርስ ምንም አልተባሉም። አደለም እንዴ?
  የካናዳ የመከላከያ ሚኒስትር በነገድ(ትውልደ ሕንዳዊ) በዜግነቱ ካናዳዊ ነው፡ ብዙ ትውልደ ዓረብም ይሁን ትወልደ አፍሪካዊ የፓርላማ አባላት በካናዳና አሜሪካ አሉ ቁምነገሩ የተገነባውን ተቋም፤ ሕዝብና ሀገር አክብሮ የተሻለውን ሰርቶ የሕዝብን አድናቆትና ድጋፍ፡ አመኔታን፡ ማግኘት እንጂ ስንቱ ኢትዮጵያ ተወልዶ አድጎ፡ በድሃው ግብር ተምሮ ሀገር የሚመዝብር፡ወላጅ ወዳጅ ዘመድ የሚያሳርር፡ ተገልጋዩን ሕዝብ የሚያማርር፡ ትወልድ የሚያመክንና የሚያባክን ዜጋ ተብዬ አጭልግ እንደተወለደ ሟች ኢትዮጵያዊስ በሁሉም ዘርፍ ሞልቷት የለም እንዴ ? ዋሸሁ እንዴ?
  ታዲያ ይህ ጫጫታ ምንድነው?
  “ኢትዮጵያውያንና ትወልደ ኢትዮጵያውያን” ለነገሩ ክልላዊ ማንነት እንጂ ሀገራዊ ዜግነት ዋጋ እንዳለው ሕዝቡ አሁን እንዴት ገባው? ለዚያውም ለጠ/ሚ ወሬ ተንታኝ ለመሆን? ሀገሪቷ አዲስ ነገር አይታይበሽ ተበላ እንደተረገመች አቃቂረኛና አሽሙረኛው አፉን አሹሎ ሊሞጣሞጥ ብቅ ይላል።
  ለምሳሌ የቻይና ቲቪ ጋዜጠኛ ግሩም ጫላ ጥያቄ መጀመሪያ የሥራ ቋንቋዬ እንግሊዘኛ ስለሆነ ጥያቂዬን በእንግሊዘኛ ላቅርብ ይላል” …ኢትዮጵያዊ ሆኖ በሥራ ቅጥር ቻይናዊ ሆኗል ማለት ነው። በአሜሪካ እና ካናዳ ሌሎችም ሀገር ያሉ የውጭ ጋዜጠኞች ስፓንሹም ፈረንሳዩም ትንታኔ የሚጠይቁት በሀገሩ ብሔራዊ ቋንቋ እንጂ በመጡበት ሀገር ወይም በተቀጠሩበት ሀገር ቋንቋ አደለም። ግሩም ጫላ ለምን ለየት ለማለት ፈለገ? ቦታው ለእኛ በእኛ ብቻ ብሎ ይሆን?
  ወ/ሪት ቢልለኔ ስዩም ወልደየስ በዜግነት ካናዳዊት መሆናቸው ለማሳጣት ወይስ እንግሊዘኛ ብቃታቸውን ለመፈታተን? (መሰሪነት!)
  ሌላው ያነሳው ነጥብ ” ከእናንተ ይልቅ ጠ/ሚ ኮ/ል አብይ አህመድ በወር አንድ ግዜ ያናግረን ከፈረሱ አፍ መስማት እንፈለጋለን” ይላል ይህ ሁለተኛው ጠለፋ ነው።
  ** (ግሩም ጫላ.አዲስ አበባ. ኢትዮጵያ) ሲል በጣም ደስ የሚለኝ ኢትዮጵያዊ ጋዜጠኛ ነው።
  ጠ/ሚ ኮ/ል አብይ ለአዳራሽ የሚበቃ ጥሩ የንግግር ችሎታ ቢኖራቸውም (ጋዜጠኛው አፋጠጣቸው፡ ታሪክ ሰራ) የሚያስብል አልባሌ ጥያቄ በመጣል አድናቆትን የሚያነፈንፉ ጋዜጠኞች ) አስተሳሰብ ነው። ዓብይ አሁን አንዳንዱ ጨዋታም ገብቷቸዋል ማለት ነው፡ ወይ ፀጥ ለጥ አድራጊ አፈቀላጤ መቅጠር አለዚያም ይህንን ጥያቄ አልፈዋለሁ ማለት። በበኩሌ ጠ/ሚ ኮ/ል አብይ በአሽሙር ከመለሰው መልስ ይልቅ…በተለይ ሕግ ነክ ጥያቄዎችን ሳያጨማልቅ ጥያቄዎችን የዘለለበት ዘዴዎች በጣም ተስማምቶኛል..የመለስን ራዕይ ቢከተል እንዲሁ የቻይና ተረት፡ የጫት ላይ ቀልድ ፓርላማ እየቀለደ በውሸት ጭብጫቦ ይደነቁር ነበር።
  ሌላው ቱማታ “ዜጎች ለየትኛው ፖስፖርት ነው ታማኝነታቸው የሚለውን ጥያቄ ያስነሳል፤››
  ድንቄም! መጀመሪያ ግሎባላይዜሽን ሉዓላዊ ሀገርነትህን ገፎታል። የኢትዮጵያ ሕገመንግስትም ዳር ደንበር በክልሎቹ ይወሰናል ይላል እንጂ አዋሳኝ ሀገር ድንበር የለንም፡ጭራሽ አሁን አፍሪካን አንድ ማድረግ ሕልም በገዳ ሥርዓት ማስተሳሰር ሲባል አብረህ ታጨበጭባለህ ከፍተህ ምን ልትሰጥ፡ ምን ልትቀበል እንደሆን ይታያል!። ዛሬ የሚያበድሩንና የሚረዱን ሀገራት ፳፪ ቢሊየን ዶላር ዕዳ ሲቆሉሉብን የጋዜጠኛ ወሬን ሳይሆን ወርቅ፡ ነዳጅ፡ ቅርስ፡ ገንዘብ፡ብረትና ቡና የት እንዳለ ሥንት እንደሚያወጣ ከአየር ላይ እየተቆጣጠሩና እየመዘገቡ እንደሆነ ማወቅ ነው። ይህንን ለማድረግ ሳተላይት እንጂ ፓስፖርት(ዜግነት፡ቪዛ) አያስፈለጋቸውም ግድግዳ ላይ የተፃፈን ቆሞ ጋዜጠኛ ፊት ማውራት ምን ያህል የሀገር ድብቅ ሚስጠር ቢሆን ነው? ስንቱ የውጭ ዜግነት ይዞ ሚዲያ ከፍቶ ሁለተኛ መንግስት መስርቻለሁ ይል የለምን? የአንድን ደሃ ሀገር ዓመታዊ የትምህርት ፈተና ሰርቄ እኔነኝ መልስ የሰራሁትና መንግስትን ዕዳ የጨመርኩት የሚልን ጎረምሳ ቤተመንግስት አስገብቶ ያንፈላሰስ የለምን? ትውልደ ኢትዮጵያዊውን አደለም አንድ ዶላር ከቡና ቀንስ ሀገርህን ዕርዳ ተብሎ የሚለመነው? የትውልደ ኢትዮጵያዊው የቤተሰብ እርዳታ አደለም ከውጭ እርዳታ የሚበልጠው? ለመሆኑ ከነጭ እውቀት ከምንለምን የነጭ ዕውቀት ነጥቀው በሚመጡ ብንጠቀምበት ምንድነው ችግሩ? ለመሆኑ ጠ/ሚሩ በተለያዩ የውጭ ሀገራት ሲሄዱ ትምህርት፡ ጤና፡ መከላከያውን ለማጠናቀር እርዱኝ ብለው ሲለምኑ የሀገር ሚስጥር ሳይገለጥ ነው? እነኝህ ሰዎች ለመምከርና ለመርዳት ሲመጡ የክልል ዜግነትና ፓስፖርት ተሰጥቷቸው ነው? (ቂጥ ገልቦ ክንብንብ) አሉ
  **************
  ይህ ጉዳይ ኮ/ል አብይ አህመድ የአብዛኛውን ተቃዋሚ ተፎካካሪ ተደጋፊ ከበሮ ቀምቶ መደለቅ ሲጀምር ብዙው ሥራ ፈት ሆኗል። ከ፷፭ ፓርቲ ለምርጫ ውድድር የተመዘገበው እንኳ ፭ አልሆነም !? ሁሉንም ኢህአዴግ አድርጎ ደምሮታልና!!። ጋዜጠኛውንም..ሰበር ዜና፡ ሚስጥር፡ ሹክሹክታ፡ውስጥ አዋቂ የሚለውን በአንድ ቃል አቀባይ ለሁሉም ያወራዋል ስለዚህ ነገሮች ግልጽ እየሆኑ ይሄዳሉ የስሚ ስሚ የለም ቃል አቀባዮቹ ጠ/ሚስተሩንም ፓርቲውንም ይሞግቱለታል .. አሉ.. ተባለ አሉ.. መሰለኝ… ጠረጠርኩ የሚሉ እንቶፈንቶ ወሬ ይቀንሳል ይቀራልም። ስለዚህ ጅምሩን መተቸት፡ አለዚያም ማተራመስ ወይም መቀወጥ ስልታዊ መሸበርና ማሸበር ነው በለው!

  Reply

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.