አገር በቀል ባለ ኢንዱስትሪዎች መብታችንን ተነፍገናል አሉ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/71431

(ሪፖርተር ኣማርኛ)
የገቢ ዕቃዎችን በአገር ውስጥ ምርት በመተካት ላይ የሚገኙ የፋብሪካ ባለቤቶች ኢትዮጵያዊ በመሆናቸው ብቻ መብታቸው በመነፈጉ፣ ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አቤቱታ አቀረቡ፡፡
ከውጭ ጥሬ ዕቃ በማስገባት ያለቀላቸው ገቢ ዕቃዎችን በአገር ውስጥ የሚያመርቱ አገር በቀል ፋብሪካዎች የዱቤ ሽያጭ አሠራር ለውጭ አገር ኢንቨስተሮች ተፈቅዶ፣ ለአገር ውስጥ ኢንቨስተሮች መከልከሉ በገዛ አገራቸው የባይተዋርነትና የሁለተኛ ዜግነት ስሜት እንዲሰማቸው ማድረጉን አመልክተዋል፡፡
ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀረበው አቤቱታ ማጠንጠኛ በአቶ ተክለ ወልድ አጥናፉ ይመራ የነበረው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባለፈው ዓመት ጥቅምት 2010 ዓ.ም. ያወጣው የውጭ አቅራቢዎች ዱቤ ሽያጭ መመርያ፣ አገር በቀል ኢንዱስትሪያሊስቶችን በማግለሉ ነው፡፡ ዋነኛ የኢንዱስትሪው ተዋናዮች ይህንን የብሔራዊ ባንክ መመርያ ‹‹የአፓርታይድ መመርያ›› እያሉ ይጠሩታል፡፡
ባለፈው አንድ ዓመት የውጭ ኢንቨስተሮች በመመርያው መሠረት በውጭ አቅራቢዎች ዱቤ ሽያጭ (ሰፕላየርስ ክሬዲት) ከብሔራዊ ባንክ ልዩ ደብዳቤ በማጻፍ ጥሬ ዕቃ ከውጭ በማስገባት ማምረት መቻላቸውን፣ አገር በቀል ፋብሪካዎች ግን መመርያው ስላልፈቀደላቸው ከማምረት መስተጓጎላቸውን ገልጸዋል፡፡ የውጭ አቅራቢዎች ዱቤ ሽያጭ አሠራር ለአገር ውስጥ ባለሀብቶች እንዲፈቀድ ካስፈለገ ኤክስፖርት አድርገው ምንዛሪውን ካመጡ ብቻ ሲሆን እንጂ፣ እንደ ውጭ ባለሀብቶች በአገሪቱ ግምጃ ቤት ምንዛሪ ስለማይፈቀድላቸው ከምርት እየወጡና የተበደሩትን መክፈል ባለመቻላቸው ያስያዙት ንብረት የመወረስ ሥጋት አንዣብቦበታል ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ሆነው በቅርቡ የተሾሙት ይናገር ደሴ (ዶ/ር) የአገር ውስጥ ኢንዱስትሪያሊስቶች በጥሬ ዕቃ ዕጦት ምክንያት ማምረት ባለመቻላቸው ለብድር ያስያዙት ንብረት እንዳይወረስ ለባንኮች ደብዳቤ የጻፉ ቢሆንም፣ አገር በቀል ፋብሪካዎች ከአቅማቸው በታች በማምረት በመገደዳቸው

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.