አገር የሆነች ቤተ ክርስቲያንን መጠበቅ የመንግሥት ግዴታ መሆኑን ማኅበረ ቅዱሳን አሳሰበ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/170947

አገር የሆነች ቤተ ክርስቲያንን መጠበቅ የመንግሥት ግዴታ መሆኑን ማኅበረ ቅዱሳን አሳሰበ
አገር የሆነችን እና አንድነትን ከነ ጥብዓቱ ጠብቃ ለትውልድ ያስረከበችን ቤተ ክርስቲያን መጠበቅ የመንግሥት ግዴታ በመሆኑ የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚንስትር ክቡር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በቤተ ክርስቲያን እና በምእመናን ላይ እየተፈጸመ ያለውን ጥቃት እንዲያስቆሙ ማኅበረ ቅዱሳን በደብዳቤ ጠየቀ።
በቍጥር ማቅሥአመ/41/05/ሀ/12፤ በቀን 05-03-2012 ዓ.ም ለጠቅላይ ሚንስትሩ የተጻፈው ደብዳቤ ጠቅላይ ሚንስትሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአገር ግንባታ የነበራትን ታላቅ ሚና ተገንዝበው ለቤተ ክርስቲያን አንድነት እና ሰላም ላደረጉት አስተዋጽዖ ዕውቅና ሰጥቶ በአሁኑ ጊዜ ግን ወርቅ ላበደረ ጠጠር እየተከፈላት መሆኑን በመግለጥ በክርስቲያኖች ላይ እየደረሰ ያለውን መጠነ ሰፊ ጥቃት መንግሥት እንዲያስቆም ጠይቋል።
በአገራችን በየጊዜው ድንገት በሚፈጠሩ ሁከቶች እና ብጥብጦች ምክንያት እየተፈለገ አገልጋይ ካህናት እና ምእመናን እየተገደሉ፣ አብያተ ክርስቲያን እየተቃጠሉ መሆናቸውን የሚያስገነዝበው ደብዳቤው እየደረሰ ላለው ችግር መንግሥት አፋጣኝ መፍትሔ ሊሰጠው እንደሚገባ አሳስቧል።
Ø ጠቅላይ ሚንስትሩ ቤተ ክርስቲያኗን የአገር ባለውለታ ከማለት ይልቅ ራሷን አገር አድርጎ መግለጥ የውለታዋን ታላቅነት በተሻለ ሁኔታ ይገልጣል ብለው እንደነበር ደብዳቤው ያስታውሳል።
Ø ቤተ ክርስቲያን እንደ አገር ስለምታስብ ለአገር ልማት እና ዕድገት ትኩረት ሰጥታ ስትሠራ ኖራለች።
Ø ወርቅ ላበደረ ጠጠር እንዲሉ እየተፈጸመባት ያለው ግፍ ለበጎነቷ ተቃራኒ የሆነ መልስ ነው።
Ø ጽንፍ የረገጠው የዘውግ ፖለቲካ ርእዮተ ዓለም ኢትዮጵያን በጠላትነት የፈረጁ የውጭ አካላትን ሽፋን ያደረገ ቤተ ክርስቲያንን የማጥፋት እና ለአገር አንድነት እና ነፃነት ያላትን ሚና ለመቀነስ የሚፈጸም

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.