ኢህአዴግ አዲስ ከሚመረጠው ጠቅላይ ሚ/ር ምንም አዲስ ነገር አትጠብቁ አለ

Source: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/89113

(ዘ-ሐበሻ) አዲሱ የኢህአዴግ ሊቀመንበርና ጠቅላይ ሚ/ር የሚሆነው ሰው በዚህ ሳምንት የሚታወቅ ሲሆን አዲስ በሚመረጠው ሰው ላይ ገና ማንነቱን ሳያውቁ ተስፋ ለሚያደርጉ ሰዎች ድርጅቱ ምንም የተለየ ነገር አትጠብቁ ሲል መግለጫ ሰጠ:: የኢህአዴግ የአዲስ አበባ ፌስቡክ ገጽ ላይ ድርጅቱ አቋሙን እንደገለጸው “ከኢህአዴግ የተለየ ፕሮግራም የሚፈፅም ጠቅላይ ሚኒስቴር ሊመጣ የሚችለው ከኢህአዴግ ውጪ ብቻ ነው!” ሲል በግልጽ ለውጥ እንደማይኖር […]

Share this post

One thought on “ኢህአዴግ አዲስ ከሚመረጠው ጠቅላይ ሚ/ር ምንም አዲስ ነገር አትጠብቁ አለ

 1. “አዲሱ የኢህአዴግ ሊቀመንበርና ጠቅላይ ሚ/ር የሚሆነው ሰው በዚህ ሳምንት የሚታወቅ ሲሆን አዲስ በሚመረጠው ሰው ላይ ገና ማንነቱን ሳያውቁ ተስፋ ለሚያደርጉ ሰዎች ድርጅቱ ምንም የተለየ ነገር አትጠብቁ ሲል መግለጫ ሰጠ::”
  “በምርጫ አሸንፎ ይህችን ሃገር የመምራት ሃላፊነት የተረከበው ኢህአዴግ ነው፡፡ ተወዳድሮ ያሸነፈው የኢህአዴግ ፕሮግራም ነው፡፡ ስለሆነም ጠቅላይ ሚኒስቴር የሚሆነውም ኢህአዴግ ነው፡፡ ሰው በሰው ሊተካ ይችላል፡፡ ተተክቷልም! የሚቀጥለው ግን መስመሩና የድርጅቱ ፖሊሲና ስትራቴጂ ነው፡፡”
  “ከኢህአዴግ የተለየ ፕሮግራም የሚፈፅም ጠቅላይ ሚኒስቴር ሊመጣ የሚችለው ከኢህአዴግ ውጪ ብቻ ነው!” ሲል በግልጽ ለውጥ እንደማይኖር አስታውቋል::
  ******************
  » ይህ ያልገባው ግራ የተጋባ ተቃዋሚ/ተቋቋሚ ካለ የጉድ ነው። ገዢው ፓርቲ፡አውራው ፓርቲ፡ መንግስት፡ህወሓት/ኢህአዴግ የገበሬው ነው፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ፹ ከመቶ ገበሬ ነው፡ ፷፭ ከመቶ ዕድሜው ከ፴ ዓመት ብታች ነው፡ስለዚህ “ሕዝቡ ምን ምርጫ አለው ይመርጠናል።” ያሉትም ንቀትን እንደ ዕውቀት ተጠቅመው እንደሆነ ልብ ይሏል።
  ግን ይህ ፹ ከመቶ ገበሬ የየት ሀገር ገበሬ ነው?
  ይህ መንገድ ላይ ወጥቶ የሚጮኽው ወጣት የየትኛው ሀገር የገበሬ ልጆች ናቸው?
  ለመሆኑ ፖለቲከኛው፡ ምሁሩ፡ ሠራተኛው፡ ተማሪው፡ ወታደሩ፡ ከገበሬው የተለየ ልዩ ፍላጎትና ጥቅም አለውን?
  ከሌለው እንዴት አላመፀም? ከአመፀስ ኢህአዴግን ለምን ጠላው?
  የገበሬውን ፍላጎት አሟልቻለሁ ያለው አውራው መንግስት ደጋፊ/ተደጋፊ፡ ካድሬ፡ በማብዛት ልዩ ጥቅማጥቅመኞችን በሙስና መር ኢኮኖሚ ጠርንፎ ለምን ለውጥ አላመጣም!?
  የግለሰብ የዜግነት መብት እየጨፈለቁ ይልቁንም የቡድን መብት መፍቀድ ተቧድኖ ዙሪያውን ሲጠዘጥዙት ለምን ያለቅሳል? በፈጣን አዋጅ እራሱን ለምን ያስራል? ተከለልና ብላ/አባላ ያለውን ራስ ገዝ መሬት(ክልል) አትደረስብኝ ሲባል ለምን ደፍሮ ገብቶ በእሳት ይለበለባል? ህወሓት አባታቸው ያልታወቀ እህቴ የሚላቸው ብአዴን፡ደህዴን፡ኦህዴድን ግንባራቸውን አቀልሞ ለምን የቁም እስረኛ አደረገ? አጋሮቼ የሚላቸውን የእንጀራ ልጆች እንዴት ከዘበኝነት አንስቶ መኝታ ቤቴ ይግቡ አልጋ ይነጠፍላቸው ለማለት ፈለገ? ነገር አለ በለው!

  አዎን! መለስ ሞተ አልሞተ፡ ፋጡማ(አዜብ) ኖረት አልኖረች፡ ዘርይሁን መጣ ቀረ፡ ህወሓት መሠረቱን ጥሎባቸዋልና የሰሩት አሻጥር ሁሉ ተመዝግቧልና ካርዱ ከመመዘዙ በፊት “በእኛ የተፈጠራችሁ፡ለእኛ የምትኖሩ፡ያለ እኛ የምትበታተኑና የምትጠፉ ብርቅዬ እንሣዎች(ሰቦች)ተብለው አማራ፡ አማርኛንና ኦርቶዶክስ ዕምነትን ከእነ ሰንደቅ ዓላማው ለማጥፋት ተስማምተው በመፈቃቀድና በመፈቃቀር ተረግጠው ሊገዙም ህወሓት ለሚነድፈው አንድ የፖለቲካል ኢኮኖሚ(ሞኖፓል)ሥር ሊገዙ ወደው በጫካው ማኒፌስቶ በከተማው ሕገመንግስት ተማምለዋል።
  አራት ነጥብ።
  ከዚች ብታፈነግጥ ወይም ቃልኪዳን ብታፈርስ ትፈርሳለህ!ስለዚህ የሚመጣው ተቀጣሪ አገልጋይ ተጠቅላይ ሚ/ር ዕጣ ፈንታ ጭራሽም በአስቸኳይ አዋጅ ላይ የሚሾም ዕዳው ገብስ አደለም። ከአጋም የተጠጋ ቁልቁል ይልዎታል እራሱ እሱ ነው።
  እራስህን ዝቅ አድርግና (ክብርና ሞገስ ለታላቁ መሪ)ብለህ”ሥራው ከባድ ነው፡ከፊትም፡ ከኋላም፡ ከጎንም፡ ሆናችሁ እርዱኝ” ሶስት ም/ተጠቅላይ ጨመረው ባጃጁ ኅይለመለስ ደስአለኝ አሉት አሉ። ዘይገርም

  Reply

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.