ኢሕአዴግ መስራቾች መወነጃጀልና የግንባሩ አንድነት፣ የኢትዮጵያ ሕልዉና

Source: https://mereja.com/amharic/v2/131443
https://radiodownloaddw-a.akamaihd.net/Events/dwelle/dira/mp3/amh/C442F543_2_dwdownload.mp3

DW : አምና መጋቢት አዲስ አበባ ላይ የተደረገዉ የመሪዎች ለዉጥ ለኢትዮጵያ ሕዝብ የዘመናት ትግሉ ዉጤት፣ የሰላም፣ የፍትሕ፣ የነፃነት የልማት ዕድገቱም ተስፋ ነበር።የቦምብ ሽብር፣የጎሳ ግጭት፣ ግድያ፣የሚሊዮኖች መፈናቀል ቅራ ቀኝ ሲያዳፈዉ ዓመት የዘለቀዉ ተስፋ፣ ዘንድሮ ሰኔ አጋማሽ የተፈፀመዉ የባለስልጣናት ግድያ ጨርሶ እንዳይድጠዉ ብዙዎችን አስግቷል።የሕዝብን ተስፋ ሲሆን የማዳን፣ ይሕ ቢቀር ስጋቱን የማቃለል ኃላፊነት የተጣለባቸዉ የገዢ ፓርቲ መስራቾች ከመቀሌና ባሕርዳር የገጠሙት መወነጃጀል ታዛቢዎች እንዳሉት 27 ዓመት አፈሙዝ የጋረደዉን «ድንቁርና» ገሐድ አፍግቶታል።ደቡብ ላይ የሚሰበከበዉ የራስ አስተዳደርም ገዢዉን ግንባር የሚያፍረከርክ፣ የሚንጠራወዘዉን ተስፋ ሕልቅት የሚፈጠርቅ መስሏል። ከዚሕ በኋላስ?
ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ይመሩት የነበረዉ መንግስት ግንቦት 2001 በመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ወንጅሎ ካሰራቸዉ የጦር መኮንኖች አብዛኞቹ አማሮች ነበሩ።የኢሕአዴግን መርሕና የመሪዎቹን አሰራር እናዉቃለን የሚሉ፣ ያኔ እንደተናገሩት ብዙዎቹ የፓርቲና የመንግስት ሹማምታት እርምጃዉን የሰሙት እንደአብዛኛዉ ህዝብ ከመንግስት መገናኛ ዘዴዎች ነበር።
እርምጃዉን ዘግይተዉ መስማታቸዉ፣ ተጠርጣሪዎቹ የጦር መኮንኖች «የቀድሞ» የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) ታጋዮች መሆናቸዉ ያበሳጫቸዉ የንቅናቄዉ መሪ አቶ አዲሱ ለገሰ በዚያዉ ሰሞን በተደረገ የባለስልጣናት ስብሰባ ላይ፣ «ጠቅላይ ሚንስትሩ ማብራሪያ እንዲሰጧቸዉ ጠየቁ» ይላሉ-ሰምተናል ባዮች።
«የተወሰደዉ እርምጃ አስተዳደራዊ በመሆኑ—-መንግሥትን እንጂ ፓርቲዎችን—-ደግሞም አንዳዶቻችሁ ሰምታችኋል——» እያሉ ትልቁ አለቃ ሲያብራሩ፣ አገጫቸዉን መዳፋቸዉ ላይ ተክለዉ ሲያዳምጡ የነበሩ አንድ የብአዴን ከፍተኛ ሹም፣-
«አዲሱ—- እንዴ—-እኔናተ አይደለንም እንዴ ኢሕድንን እጁን ጠምዝዘን ለሕወሓት ያስረከብነዉ—-» አሉና ጠያቂዉም፣ መላሹም፣ ሌሎቹም «ሆድ ሲያዉቅ» ዓይነት ለዓመታት የሚደባብቁትን ሐቅ ተነፈሱ።«ተፈወሱ» ብንልም ያስኬድ ይሆናል።
ትረካዉ እዉነት፣
Emblem der Tigray People's Libration Font (TPLF)
ሐሰት፣

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.