ኢሕአዴግ ከ30 ገደማ የሥልጣን አመታት በኋላ ፈረሰ።

Source: https://mereja.com/amharic/v2/196144
https://radiodownloaddw-a.akamaihd.net/Events/dwelle/dira/mp3/amh/24C31175_2_dwdownload.mp3

DW — ህወሓት በ45 አመታት ታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የጠራው አስቸኳይ የጠቅላላ ጉባኤ መቐለ በሚገኘው ሐውልቲ አዳራሽ ሲካሔድ መሰብሰቢያው በቀይ ቀለም ደምቆ ነበር። የአዳራሹ ወንበሮች ቀይ ናቸው። የጉባኤው ተሳታፊዎች ከአንገታቸው ጣል ያደረጓቸው ስካርፎች ቀይ ናቸው። “ውግንናችን ለህዝባችን እና መስመራችን” እንዲሁም “ሁሉ ተግባራችን ለህዝባችን ደህንነት እና ህልውና” የሚሉትን ጨምሮ በርከት ያሉ መፈክሮች በአዳራሹ ግድግዳዎች ይታያሉ። ከመድረኩ ጀርባ ህወሓት ደርግን ለመጣል ለአስራ ሰባት አመታት ባደረገው ትግል ሕይወታቸውን የገበሩ ታጋዮች ፎቶ ግራፎች ይታያሉ።
አንድ ሺሕ ስልሳ ስድስት ድምፅ የመስጠት መብት ያላቸው የህወሓት አባላት የተሳተፉበት ጠቅላላ ጉባኤ ሲጠናቀቅ ያወጣው መግለጫ ግንባሩ ኢሕአዴግ ፈርሶ ከተቋቋመው ብልፅግና ፓርቲ እንደማይቀላቀል አስታውቋል። ያለ ምንም ተቃውሞ እና ያለ አንዳች ድምጸ-ተዓቅቦ በጉባኤው የጸደቀው የውሳኔ ሐሳብ ኢሕአዴግን አፍርሶ አዲስ ፓርቲ መመሥረት “ታሪክ የማይረሳው ስህተት” ነው ብሏል። ውሳኔው ከዚህ ቀደም በህወሓት ሥራ አስፈጻሚና ማዕከላዊ ኮሚቴ ከተላለፈው የተስማማ ነው።
በጉባኤው ጅማሮ ንግግር ያደረጉት የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ-መስተዳድር ደብረጺዮን ገብረ-ሚካኤል ከህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ጋር በመሆን ኢሕአዴግን የመሠረተው የቀድሞው ብአዴን ወይም የኋላው የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ በማፍረሱ ሒደትም እጁን ማስገባቱን ጠቅሰው ወቅሰዋል።
Meles Zenawi Ministerpräsident Äthiopien (AP)
ኢሕአዴግ የተመሠረተው በህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) እና በቀድሞው የኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ኢሕዴን) ጥምረት በግንቦት ወር 1981 ዓ.ም.  ነበር። መጋቢት 17 ቀን 1982 ዓ.ም. የተመሠረተው የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦሕዴድ) እና በመስከረም 1985 ዓ.ም. የ«አስራ ስድስት የብሔረሰብ የፖለቲካ ድርጅቶች» ጥምረት የሆነው ደኢሕዴን ግንባሩን

Share this post

One thought on “ኢሕአዴግ ከ30 ገደማ የሥልጣን አመታት በኋላ ፈረሰ።

 1. To Sidama: 01/06/2020

  -Wait for your turn .
  For all we know so far at the next national elections in allover the country, Sidama might be the only one voted for with all others across the whole country getting boycotted not getting a single vote at the next national elections except for Sidama , if this happens every body in federal government and in all regional gvernments have to relinquishh all government to Sidama .

  Then Sidama will have to administer the whole not only Sidama, so for now we advise Sidama to wait for your turn by in the meantime spending the next six months time wisely by preparing for the scenario we just told you above starting from nowon that is just in case if you didn’t start already, so that if it happens you can confidently be able to do the work of transitioning into such a huge responsibility .

  http://ayyaantuu.org/የሲዳማ-ዳያስፖራ-ማህበር-በወቅታዊ-ጉዳዮ/

  Re: የሲዳማ ዳያስፖራ ማህበር በወቅታዊ የሽግግር ጉዳዮች ላይ የሰጠው መግለጫ

  Reply

Leave a Reply to Woliso Cancel reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.