ኢራን በሳምንት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ የተቃጣባትን የበይነ መረብ ጥቃት ማክሸፏን አስታወቀች

Source: https://fanabc.com/2019/12/%E1%8A%A2%E1%88%AB%E1%8A%95-%E1%89%A0%E1%88%B3%E1%88%9D%E1%8A%95%E1%89%B5-%E1%8B%8D%E1%88%B5%E1%8C%A5-%E1%88%88%E1%88%81%E1%88%88%E1%89%B0%E1%8A%9B-%E1%8C%8A%E1%8B%9C-%E1%8B%A8%E1%89%B0%E1%89%83/

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 5 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢራን በሳምንት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ የተቃጣባትን የበይነ መረብ ጥቃት ማክሸፏን አስታወቀች።

የሃገሪቱ ቴሌኮሙዩኒኬሽን ሚኒስትር እንዳስታወቀው የተቃጣውን የበይነ መረብ ጥቃት ማክሸፍ ተችሏል።

ጥቃቱ በቻይንኛ ተናጋሪ የበይነ መረብ ጠላፊዎች አማካኝነት የተቃጣ መሆኑንም ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

ባለፈው ረቡዕ በኢርና የዜና ወኪል ላይ ሊፈጸም የነበረ ተመሳሳይ ጥቃት ማክሸፉንም ሚኒስቴሩ ገልጿል።

ከሽፏል ከተባለው የበይነ መረብ ጥቃት ጋር በተያያዘ ግን ዝርዝር መረጃ አልሰጠም።

ባለፈው ሰኔ ወር ላይ የሃገሪቱን የኒውክሌር ሲስተም ኢላማ ያደረገ የበይነ መረብ ጥቃት መፈጸሙ ይታወሳል።

 

 

ምንጭ፦ ቢቢሲ

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.