ኢሳት የሚዲያ አፈና ሊፈጽም ቀርቶ አፈናን ማሰብ እንኳን አይችልም! – ከኢሳት የኢዲቶሪያል ቦርድ የተሰጠ መግለጫ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/112079

ሚያዚያ 17 ቀን 2011 ዓም
ከኢሳት የኢዲቶሪያል ቦርድ የተሰጠ መግለጫ
ኢሳት የሚዲያ አፈና ሊፈጽም ቀርቶ አፈናን ማሰብ እንኳን አይችልም!

No photo description available.ሰሞኑን ጋዜጠኛና አክቲቪስት ርዮት አለሙ ከቴዎድሮስ ጸጋዬ ጋር ያደረገችው ሙሉ ቃለ ምልልስ ታርሞ እንዲተላለፍ መወሰኑን ተከትሎ ድርጊቱ “አፈና ነው” የሚል እንደምታ ያለው መልክት በማህበራዊ ሚዲያ ሲሰራጭ ተመለክተናል፡፡ መልዕክቱ ኢሳት ከቆመለት አላማ ጋር የሚጻረር በመሆኑ የኢሳት ኤዲቶሪያል ቦርድ ጉዳዩን ትኩረት ሰጥቶ ተወያትቶበታል።
ኢሳት የአቅም ውስንነት፣ የቦታ ርቀት እንዲሁም ተደጋጋሚ የአፈና ሙከራዎች ሳይበግሩት የኢትዮጵያን አየር ሞገድ እየሰነጠቀ በመላው አገሪቷ ጨለማን የገፈፈ ፈርቀዳጅ የሚድያ ተቋም መሆኑ የአደባባይ ሚስጥር ነው። በዚህ እልህ አስጨራሽ ትግልም ላለፉት 9 ዓመታት በኢሳት ዙሪያ የተሰባሰቡ ጋዜጠኞች፣ የመብት ተሟጋቾች፣ የለውጥ አቀንቃኞች ብቻ ሳይሆኑ በአለም ዙሪያ የተደራጁ ደጋፊዎች ለኢሳት ስኬት ጉልህ ሚና ተጫውተዋል።
ዛሬ በአገራችን ያለው ሁኔታ በአንድ በኩል ተስፋና እድል የያዘ፣ በሌላ በኩል ደግሞ ስጋትና ጭንቀትን እያስከተለ በመሆኑ ኢትዮጵያ መስቀለኛ መንገድ ላይ ትገኛለች ብሎ መናገር ይቻላል። መስቀለኛ መንገድ ላይ የምትገኝ አገር፣ ወደ ተሻለ ጎዳና ትሄድ ዘንድ ኢሳትን የመሳሰሉ ሃላፊነት የሚሰማቸው የሚዲያ ተቋማት ልዩ ጥንቃቄ በማድረግ አገራዊ ሃላፊነታቸውን መወጣት እንዳለባቸው ኢሳት ከልብ ያምናል።
ኢሳት ተቺና ሞጋች ሚድያ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ የሚያቀርባቸው ዘገባዎች በተቻለ አቅም ሚዛናዊና ከስሜት የጸዱ እንዲሁም የሚተላለፉ ዘገባዎችም ሆኑ የሚቀርቡ ዝግጅቶች ከግል አመለካከት እና ከግል ሃሳቦች ይልቅ የነጠሩ ሃቆች (facts) ላይ መሰረት ማድረጋቸውን ማረጋገጥ እንደሚያስፈልግ ኢሳት ላለፉት 9 ዓመታት ሲመራበት

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.