ኢትዮጵያዊነት በዴሞክራሲያዊ ብሔርተኝነት ያብባል ይዘምናልም | አበበ ተክለሃይማኖት (ጆቤ) (ሜጄር ጄኔራል)

Source: http://www.zehabesha.com/amharic/?p=83265

* አገሮች በውዴታ ብቻ ቢመሰረቱ ኖሮ የማንነት ጉዳይ በተለይ የብሔር ማንነት ጉዳይ በላላ ነበር የመደብ እና ሌሎች ማንነቶች ጎልተው ይታዩ ነበር፡፡ ነገር ግን አብዛኛው አገሮች የግዴታ በኃይል የተመሰረቱ በመሆናቸው የተለያዩ ብሄሮችን አጭቀው ይገኛሉ፡፡ በአገር ግንባታ አንፃር ረጅም ርቀት ተጉዘዋል የሚባሉት የአውሮፓ አገሮች እንኳን የብሄር ጥያቄ በበርካታ አገራት በ21ኛ ክፍለ ዘመን ጎልቶ እየታየ ነው፡፡ በስፔን፣ ጣሊያን፣ […]

Share this post

One thought on “ኢትዮጵያዊነት በዴሞክራሲያዊ ብሔርተኝነት ያብባል ይዘምናልም | አበበ ተክለሃይማኖት (ጆቤ) (ሜጄር ጄኔራል)

 1. ሞት ለጎሣ /የቋንቋ/ ፌደራሊዝም (በሃያሬ ተንለሱ)
  ሰሞነኛው የፖለቲካ ቁማር የሚያጠነጥነው የኢትዮጵያን ፖለቲካዊ ችግር ለመፍታት በጎሣ /የቋንቋ/ ፌደራሊዝም አስፈላጊነትና መግባባት ላይ ትኩረት በመስጠት ጉዳይ ላይ ነው። የዚህም ጥረት ዋነኛ ቀመር አክራሪ የጎሣ ፖለቲከኞችን ቀልብ ለመግዛትና እነርሱን የመገንጠል ህልማቸውን ትተው ወደ አንድነት ጎራ ለማምጣት ሲባል የሚደረግ እሹሩሩና በአዲስ መልክ የተቃኘ ወግም ነው። በዚህ ጉዳይ ላይ ከማተኮሬ በፊት ስለ ጎሣ /የቋንቋ/ ፌደራሊዝም አንዳንድ ነገሮችን ማንሳቱ ጠቃሚ ይመስለኛል።

  ጎሣ/የቋንቋ/ ፌደራሊዝም
  የጎሣ /የቋንቋ/ ፌደራሊዝም እንደ መፍትሄ የሚቀርበው በአንድ ሃገር ውስጥ በሚኖሩ ጎሣዎች መሃከል ቅራኔና ውጥረት ሲሰፍንና ሲባባስ /Inter-Ethnic Tensions/ ይህንን ችግር የዚሁ ሃገር ሉዓላዊነት ሣይናጋ ለጎሣዎቹ የራስ-ገዝ አስተዳደርና መልካዐ-ምድራዊ ክልል በማበጀትና በመስጠት ሁኒታውን ለማርገብ ሲባል ነው።

  የጎሣ /የቋንቋ/ፌደራሊዝም ከተሞከረባቸው ሃገሮች ደቡብ ሱዳን፣ኔፓል፣ዩጎስላቪያ፣ፓኪስታንና የኛው ኢትዮጵያ ቀዳሚዎቹ ናችው። ነገር ግን ይህ የተተገበረው የጎሣ/የቋንቋ/ ፌደራሊዝም በአንፃሩ ችግርን ሲፈታ ሣይሆን ችግርን ሲባብስ ይስተዋላል። በደቡብ ሱዳን የሚታየው የርስ በርስ ፍጅት፤የዩጎስላቪያ መበታተን፤በፓኪስታን ያለው የጎሣ ግጭትና በሃገራችን ኢትዮጵያ የተከሠተው ውጥረት ምንም እንኳ ይህ የሚቀነባበረው በገዢው ወያኔ ቢሆንም ለህወሃት አፓርታይዳዊ ስራዓት መፈጠር ምክንያቱ የጎሣ /የቋንቋ/ፌደራሊዝም ብቻ ነው። የጎሣ/የቋንቋ/ ፌደራሊዝም የተደራጁ ጎሣዎች የራሳቸውን ጥሬ ሃብት መቆጣጠር ሲጀምሩ፣እውቅናን እያገኙ ሲመጡና ነፃ የሆነ የስልጣን መሠረት ሲያደላድሉ የመገንጠል ስሜትን እያዳበሩ ይመጣሉ።

  በዚህም ሣቢያ የጎሣ /የቋንቋ/ ፌደራሊዝም አንድም ለመገንጠል ሌላም ለለየለት የጭቆና ስርዓት መከሰት አይነተኛ ምክንያት ይሆናል። የጎሣ /የቋንቋ/ፌደራሊዝም ማንኛውንም ሃገራዊ ጉዳዮች በጎሣ ዓይን መመልከቱን ስለሚያዳብርና ሁሉንም ክስተቶች ጎሣ ተኮር ብቻ የማድረግ አባዜ ሰለሚጠናወተው ከቸግር ፈችነቱ ይልቅ በችግር ፈጣሪነቱ ይታወቃል።

  ሌላው የጎሣ /የቋንቋ/ፌደራሊዝም ገፅታ የስርዐቱ አወቃቀር ነው። ለምሳሌ በሃገራችን ኢትዮጵያ የጎሣ /የቋንቋ/ፌደራሊዝም የተዋቀረው ቋንቋን መሰረት አድርጎ ነው። ትርክቱም የሚጀምረው በዘመነ ሶሻሊዝም በተነደፍውና በጊዜ በከሰመው የጆሴፍ ስታሊን መጣጥፍና በ1960ዎቹ የኢትዮጵያ ተማሪዎች በተቃረመው “የብሔሮች ጭቆና” አስተሳሰብ ዙሪያ በተንከባለለ ንድፈ ሃሳብ ነው። የጆሴፍ ስታሊን መጣጥፍ መነሻ ሃሳብ በተለይ በሶቪዬት ህብረት ግዛት አስተዳደር ስር የነበሩትን ላቲቪያ፣አኢስቶኒያ፤ጆርጂያ፤ስላቭ ወ.ዘ.ተ. መብትን አስመልክቶ ነበር። ጆሴፍ ስታሊን ብሔርን “ብሔር በታሪክ ሂደት የተዋቀረ ተመሳሳይ ማህበረ ህዝብ ነው።ብሔር ዘር ወይም ጎሣ አይደለም። ብሔር በአንድ አይነት ባህል የሚገለፅ የስነልቦና አመለካከት፣ከብሄራዊ መለያ ጋር የተቆራኘ የጋራ ድንበርና ቋንቋ እንዲሁም በኢኮኖሚ መተሳሰርና መጣበቅ ያለው ህዝብ ነው”ሲል የገልፀዋል። ጆሴፍ ስታሊን ጨቋኝ ብሔር የሚለውም የሌሎቹን በመጨፍለቅ የራሱን ባህሉን፣ቋንቋውን፣የስነልቦና አመለካከቱን በሌሎች ላይ ጥሎ ኢኮኖሚውንና ፖለቲካውን የሚቆጣጠረውን ብሔር ነው። እስኪ በዚህ ንፅፅር የሃገራችንን ሁኔታ ዕንቃኝ።

  Reply

Post Comment