ኢትዮጵያዊው የባህል አምባሳደር መላኩ በላይ ተሸለመ።

Source: https://mereja.com/amharic/v2/173668

ኢትዮጵያዊው የባህል አምባሳደር ተሸለመ።
በየዓመቱ በሞሮኮ ራባት ከተማ በሚካሄደው ቪዛ ፎር ሚውዚክ ፌስቲቫል (visa for Music ) ኢትዮጵያዊው የባህል አምባሳደር መላኩ በላይ ተሸለመ።
እ.ኤ.አ. በ2013 የተጀመረው ይህ የሙዚቃ ፌስቲቫል በአፍሪካና በመካከለኛው ምስራቅ በሙዚቃ ዘርፍ ተጽኖ የፈጠሩ ሰዎችን ይሸልማል።
ዘንድሮም ለ6ኛ ጊዜ በተዘጋጀው በዚህ ፌስቲቫል የፈንድቃ ጥበባ ባህል ማዕከል ባለቤትና “የኢትዮ ከለር “የባህል ሙዚቃ ባንድ መስራች አርቲስት መላኩ በላይ ተሸላሚ ሆኗል።
የፓን አፍሪካኒዝም ሀሳብ አቀንቃኝ እንደሆነ የሚነገርለት ሞሮኳዊው ኢብራሒም ኤል ማዝነድ / Brahim El Mazned /የሽልማት ድርጅቱ መስራች ሲሆን “የየሀገሩ ሙዚቃን በማወቅና በመረዳት ሰብአዊነትን ማዳበር ይቻላል።” ብሎ ያምናል ።

ምንጭ፦Visa For Music

Share this post

One thought on “ኢትዮጵያዊው የባህል አምባሳደር መላኩ በላይ ተሸለመ።

  1. እንኳን ደስ አለህ አለን !
    ሁላችንም በሞያችንን እንዳንተ ጠንክረን በመስራት ተሸላሚ እንድንሆን እንዲሁም ከድህነት እና ኃላ ቀርነት እንላቀቅ ዘንድ ምኞቴ ነው !!

    Reply

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.