ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ዛሬ በፖላንድ ጊዲኒያ የዓለም ግማሽ ማራቶን ይጠበቃሉ

ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ዛሬ በፖላንድ ጊዲኒያ የዓለም ግማሽ ማራቶን ይጠበቃሉ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 7 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ዛሬ በፖላንድ ጊዲኒያ የዓለም ግማሽ ማራቶን ሻምፒዮና ላይ ይጠበቃሉ፡፡

ለ24ኛ ጊዜ በሚካሄደው የዓለም ግማሽ ማራቶን ሻምፒዮና ላይ ለመሳተፍ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከኬንያ እና ዩጋንዳ አትሌቶች ጋር ከባድ ፉክክር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ኢትዮጵያን የሚወክሉ አትሌቶች በሴቶች

ያለምዘርፍ የኋላው ደንሳ፣ ነፃነት ጉደታ ከበደ፣ ዘይነባ ይመር ወርቁ፣ አባበል የሻነህ ብርሃኔ እና መሰረት ጎላ ሲሳይ ተመርጠዋል።

በወንዶች ደግሞ

ሀይለማርያም ኪሮስ ከበደው፣ አንዱዓምላክ በልሁ በርታ፣ አምደወርቅ ዋለልኝ ታደሰ፣ ጉዬ አዶላ ኢዳሞ እንዲሁም ልኡል ገብረስላሴ አለሜ መሆናቸውን ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

The post ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ዛሬ በፖላንድ ጊዲኒያ የዓለም ግማሽ ማራቶን ይጠበቃሉ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply