ኢትዮጵያውያን አዲስ ለተገኘ ግዙፍ የህዋ አካል ስያሜ እንዲያወጡ ጥሪ ቀረበ

Source: https://fanabc.com/2019/05/%E1%8A%A2%E1%89%B5%E1%8B%AE%E1%8C%B5%E1%8B%AB%E1%8B%8D%E1%8B%AB%E1%8A%95-%E1%8A%A0%E1%8B%B2%E1%88%B5-%E1%88%88%E1%89%B0%E1%8C%88%E1%8A%98-%E1%8C%8D%E1%8B%99%E1%8D%8D-%E1%8B%A8%E1%88%85%E1%8B%8B/

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2011 (ኤፍቢሲ) አዲስ ለተገኘ ግዙፍ የህዋ አካል ዜጎች ስያሜ እንዲያወጡ የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት ጥሪ አቀረበ።

ጥሪው የቀረበው የዓለም አቀፉ የህዋ ህብረት ለኢትዮጵያ አዲስ ለተግኘ ግዙፍ የህዋ አካል ስም እንድታውጣ እድሉ ከሰጣት በኋላ መሆኑ ተግልጿል።

የህዋ አካሉ ሳይንሳዊ መለያ ቁጥሩ ኤችዲ 16175 ና ኤችዲ 15175ቢ የተሰኘው የኮከብና ኮኮቧን የምትዞር ፕላኔት የያዘ ስርዓት ነው ተብሏል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ዜጎች 920 ላይ ስያሜውን በጽሑፍ በመላክ የዚህ ዕድል ተሳታፊ ይሆኑ ዘንድ ጥሪውን አቅርቧል።

ኢትዮጵያ ስያሜውን እንድትሰይም ዕድሉ የሰጣት ዓለም አቀፉ የህዋ ህብረት አባል የሆነቸው በቅርቡ መሆኑም ተገልጿል።

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.