ኢትዮጵያውያን ከሊባኖስ ወደ ሃገራቸው ተመለሱ

Source: https://amharic.voanews.com/a/domestic-workers-Lebanon-5-28-2020/5439678.html
https://gdb.voanews.com/A023A85F-24EE-4FCE-AC08-5FA48360C495_cx0_cy2_cw0_w800_h450.jpg

ሊባኖስ ውስጥ የነበሩ 337 ኢትዮጵያዊያን የሚያስፈልጋቸው የጉዞ ሰነድና ማስረጃዎች ተመቻችተውላቸው ወደ ሃገራቸው እንዲመለሱ ተደረገ።

ዛሬ ከቤይሩት የወጡት ኢትዮጵያዊያን ወደ ሃገር ቤት ለመጓዝ ቀደም ሲል 550 ዶላር ከፍለው የነበረ ሲሆን ገንዘባቸው ሙሉ በሙሉ የተመለሰላቸው መሆኑን በሊባኖስ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት ለአሜሪካ ድምፅ ገልጿል።

በሌላ በኩል ደግሞ የዛሬው እንስቃሴ በተለያዩ ሁኔታዎች ችግር ውስጥ የሚገኙ እና ወደ ሃገራቸው መግባት ለሚፈልጉ ዜጎች ተስፋ ሰጭ መሆኑን በሊባኖስ የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ አንድ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ገልፀዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

 

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.