ኢትዮጵያ፣ «የጠረቁ ሹማምንት የተጎሳቆለ ሕዝብ ሐገር» – ውይይት

Source: https://mereja.com/amharic/v2/139264

https://radiodownloaddw-a.akamaihd.net/Events/dwelle/dira/mp3/amh/052A3B51_2_dwdownload.mp3

DW : ባለሙያዎች እንደሚሉት ግድያ፣ግጭት፣ ዉዝግቡ በፊት ከነበረዉ የተዛባ የምጣኔ ሐብት መርሕ ወይም የአፈፃፀም ጉድለት፣ሙስና፣የወጪና ገቢ ንግድ ተባለጥ፣ የዉጪ ምንዛሪ እጥረት፣ የመሰረተ ልማት አዉታር ችግር፣የምርት መሳት፣ ምናልባትም ከሕዝብ ቁጥር ማደግ ጋር ተዳምሮ ዛሬ ጤፍን ለጤፍ አምራቹ ምጃሬ ሳይቀር «ከቁመቱ በላይ የተሰቀለ ቋንጧ» አድርጎበታል።
ድሕነት፣አለማወቅ፣ ድርቅ፣ሥራ አጥነት፣ጦርነት፣ የገዢዎች ጭቆና በየዘመኑ ለከፋ ረሐብና በሽታ የሚያጋልጠዉ ኢትዮጵያዊ ባለፉት 3እና 4 ዓመታት ደግሞ ሐገሪቱን የሚያብጠዉ ፖለቲካዊ፣ጎሳዊና አስተዳደራዊ ቀዉስ ፍዳዉን እያየ ነዉ።
የገዢዎች የከፋ ጭቆናን በመቃወም የተቀጣጠለዉ ሕዝባዊ ተቃዉሞ፣ በተቃዉሞዉ መሐልና ማግሥት የቀጠለዉ የጎሳና የፖለቲካ ግጭት፣ ሥርዓተ አልበኝነት፤ በየአካባቢዉ ሺዎችን ገድለዋል።ብዙ ሺዎችን ጎድተዋል።ሚሊዮኖችን አፈናቅለዋልም።በቢሊዮን ብር የሚገመት የድሐይቱን ሐገር ጥሪት ወድሟልም።አሁንም ድረስ ሚሊዮኖች በስጋትና ፍርሐት እያሸማቀቀ ነዉ።
ከቀጥታዉ ጥፋት በተጨማሪ ገበሬዉ በእርሻዉ፤ነጋዴዉ በመሸጥ መለወጡ፣ተቀጣሪዉ በመደበኛ ሥራና ኃላፊነቱ ላይ እንዳያተኮር ትልቅ እንቅፋት በመሆኑ ምርታማነት እንዲያሽቆለቁል ተጨማሪ ምክንያት ሆኗል።የፀጥታዉ ችግር፣ በተለይ ዘርና ጎሳን የተላበሰዉ ግጭትና ዉዝግብ የሰዎችንና የሸቀጦችን ዝዉዉር በመገደቡ ወትሮም ኑሮዉ «ከእጅ ወደ አፍ» የሆነዉን ሕዝብ ለሸቀጦች ዋጋ ንረት አጋልጦታል።
የምጣኔ ሐብት ባለሙያዎች እንደሚሉት ግድያ፣ግጭት፣ ዉዝግቡ በፊት ከነበረዉ የተዛባ የምጣኔ ሐብት መርሕ ወይም የአፈፃፀም ጉድለት፣ሙስና፣የወጪና ገቢ ንግድ ተባለጥ፣ የዉጪ ምንዛሪ እጥረት፣ የመሰረተ ልማት አዉታር ችግር፣ የምርት መሳት፣ ምናልባትም ከሕዝብ ቁጥር ማደግ ጋር ተዳምሮ ዛሬ ጤፍን ለጤፍ አምራቹ ምጃሬ ሳይቀር «ከቁመቱ በላይ የተሰቀለ ቋንጧ» አድርጎበታል።
የሸቀጦች በተለይም የመሠረታዊ ሸቀጦች ዋጋ ንረት መሠረታዊ ምክንያቶች፤ ንረቱ የደረሰበት ደረጃና መፍትሔዉ የዛሬዉ

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.