‘ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሟን አሳልፎ የሚሰጥ ውይይት ፈጽሞ አላደረገችም፣ ወደፊትም አታደርግም’ – አቶ ገዱ አንዳርጋቸው

Source: https://mereja.com/amharic/v2/201638

የኢትዮጵያ፣ የግብጽ እና የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች፣ የውሃ ሃብት ሚኒስትሮች እና የልዑካን ቡድኖቻቸው በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ እ.ኤ.አ ከጃንዋሪ 13 እስከ 15 ቀን 2020 በዋሽንግተን ዲሲ ሲያካሂዱት የነበረው ውይይት ከተጠናቀቀ በኋላ የኢትዮጵያን አቋም አስመልክቶ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው እና የውሃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶ/ር ስለሺ በቀለ ዛሬ በዋሽንግተን ዲሲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መግለጫ ሰጥተዋል።
Image may contain: 5 people, people sitting
በመግለጫቸው የተነሱ አንኳር ነጥቦች:-
• ኢትዮጵያ ከህዳሴ ግድቡ ጋር በተያያዘ ትናንት በተደረገው የመግባቢያ ነጥብ ብሔራዊ ጥቅሟን አሳልፎ የሚሰጥ አንዳችም ውይይት ፈጽሞ አላደረገችም፣ ይሄ ወደፊትም የኢትዮጵያ ቀዳሚው መርህ ሆኖ ይቀጥላል።

• ከግድቡ ጋር የሚደረጉ ድርድሮች እና ውይይቶች ኢትዮጵያ ሌሎች ግድቦችን የመገንባት መብቷን የማይጋፋ ነው።
• ከዚህ ቀደም ለውይይቱ መጓተት እንደ ምክንያት ሲነሳ የነበረውን የህዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌት ከታችኛው ተፋሰስ አገራት ግድቦች የማያያዝ ሁኔታ እንዲቀር ማድረግ ተችሏል።
• የግድቡ ግንባታ በአሁኑ ወቅት በተጠናከረ ሆኔታ ቀጥሏል፣ ግድቡ በፍጥነት እንዲጠናቀቅ በመንግስት በኩል ከፍተኛ ፖለቲካዊ ቁርጠኝነት እየተደገፈ ነው።
• ግድቡ ሲጠናቀቅ ከኃይል ማመንጨት ባሻገር የቱሪዝምና የአሳ እርባታ ልማቶችን ይኖሩታል።
• የቴክኒክ ውይይቱ ብሎም ከህግ ጋር የሚያያዙት ጉዳዮች አሁንም በዘርፉ ልምድና ክህሎቱ ባላቸው፣ በሐገር ፍቅር እንዲሁም በከፍተኛ ኃላፊነት ብቁ በሆኑ ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች እየተመራ ነው።
• ግድቡ ሲጠናቀቅ የኢትዮጵያ ስም በከፍተኛ ደረጃ በበጎ የሚያሳድግ፣ የመደራደር አቅም እና ተደማጭነትን ያጎለብታል።
• ኢትዮጵያ ትክክለኛና በመርህ ላይ የተመሰረተ አቋም እስካላት ድረስ የውይይት ቦታው

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.