ኢትዮጵያ ነፍሰ ገዳዮች እንጂ ንጹሕ ፖለቲከኞች የላትም

በገ/ክርስቶስ ዓባይ ነሐሴ 3 ቀን 2012 ዓ/ም በውጭ ዓለም ያሉ ፖለቲከኞች ገና ከልጅነታቸው ጀምሮ ማለትም ከ17-18 ዓመት ዕድሜ ጀምሮ በተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች ስብሰባዎች እየተገኙ፤ ጥያቄ በመጠየቅ፤ በምርጫ ጊዜም የተለያዩ በራሪ ወረቀቶችና የቅስቀሳ ጽሑፎችን ለብዙኃኑ ሕዝብ በማደል ድርጅታቸውን እያስተዋወቁ ይሳተፋሉ። ከዚያም በየጊዜው በሚያደርጉት እንቅስቃሴና ከሕዝብ ጋር ያላቸው ግንኙነት እየጎላ ስለሚሔድ፤ በዕድሜያቸውም ሆነ በአእምሮአቸው እየተቡ ስለሚመጡ ቀስ በቀስ ከተራ ዓባልነት ወደ ከፍተኛ የኃላፊነት ደረጃ ይደርሳሉ። በመቀጠልም ያከናወኑትን የሥራ ውጤትና ከሕዝብ ጋር ያላቸውን ተሰሚነትና ክብር ከግምት ውስጥ በማስገባት ፓርቲያቸውን ወክለው ለወረዳ፤ለአውራጃ፤ ለክልል ወይም ለፌድራል ምርጫ እንዲወዳደሩ ይታጫሉ። እንዲህ ያሉ ፖለቲከኞች ዕድሜ ልካቸውን ያደጉበት ስለሆነ በተግባርም ሆነ በቲዮሪ ጥልቅ የሆነ ዕውቀትና ግንዛቤ ይዘው ያድጋሉ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply