ኢትዮ-ቴሌኮም በአጭር ጽሁፍ መልዕክት የተሰበሰበ ከ74 ሚሊየን ብር በላይ ለሜቄዶንያ አስረከበ

Source: https://fanabc.com/2018/12/%E1%8A%A2%E1%89%B5%E1%8B%AE-%E1%89%B4%E1%88%8C%E1%8A%AE%E1%88%9D-%E1%89%A0%E1%8A%A0%E1%8C%AD%E1%88%AD-%E1%8C%BD%E1%88%81%E1%8D%8D-%E1%88%98%E1%88%8D%E1%8B%95%E1%8A%AD%E1%89%B5-%E1%8B%A8%E1%89%B0/

አዲስ አበባ፣ ህዳር 23፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮ-ቴሌኮም በአጭር ጽሁፍ መልዕክት የተሰበሰበ ከ74 ሚሊየን ብር በላይ ለሜቄዶንያ የአረጋውያን እና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል አስረከበ፡፡

ኢትዮቴሌኮም ገንዘቡን ለማዕከሉ ገቢ ማድረጉን ዛሬ በላከው መልእክት አስታውቋል፡፡

በጥቅሉ ባለፉት ሦስት ዓመታት ለማዕከሉ 74 ሚሊየን 718 ሺህ 165 ብር በአጭር ጽሁፍ መልዕክት መሰብሰብ መቻሉ ተገልጿል፡፡

ከአንድ ወራት በፊት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክትር አብይ አህመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው ማዕከሉን ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝቱ ላይም ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው 15 ዘመናዊ ዊልቸር ለማዕከሉ ማበርከታቸው ይታወሳል፡፡

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.