ኢንጂነር ታከለ ኡማ በፍሬህወት አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመገኘት ጉብኝት አደረጉ

Source: https://fanabc.com/2019/11/%E1%8A%A2%E1%8A%95%E1%8C%82%E1%8A%90%E1%88%AD-%E1%89%B3%E1%8A%A8%E1%88%88-%E1%8A%A1%E1%88%9B-%E1%89%A0%E1%8D%8D%E1%88%AC%E1%88%85%E1%8B%88%E1%89%B5-%E1%8A%A0%E1%8A%95%E1%8B%B0%E1%8A%9B-%E1%8B%B0/

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 18 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በፍሬህወት አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመገኘት ጉብኝት አድርገዋል።

ኢንጂነር ታከለ በስፍራው የተገኙት በትናንትናው እለት በተማሪዎች ላይ የማስመለስና የሳል ምልክት ታይቷል መባሉን ተከትሎ ነው።

በምልከታቸውም የሆስፒታል የምርመራ ውጤትን ጠቅሰው በተማሪዎች ላይ ከምግብ ጋር የተያያዘ ችግር አለመከሰቱን አስታውቀዋል።

የምግብ መመረዝ አለመከሰቱን ያነሱት ከንቲባው በትምህርት ቤቶች የሚደረገው የምገባ ፕሮግራም በተጠናከረና ተቋማዊ በሆነ መልኩ ይቀጥላል ብለዋል።

አያይዘውም ፕሮግራሙ በሕግ ደረጃ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አዋጅ ሆኖ ይፀድቃል ማለታቸውን ከምክትል ከንቲባው የፌስ ቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

 

Share this post

One thought on “ኢንጂነር ታከለ ኡማ በፍሬህወት አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመገኘት ጉብኝት አደረጉ

  1. No K9 no safety. Belgian Malinois need to be used in police works of Ethiopia ,Meles Zenawi kept his personal partner as his best kept secret that’s why till this day Belgian Malinois are not allowed for the security apparatus’s daily activities. Meles made sure he himself directly ordered the Belgian Malinois with he himself leading the mission personally meaning Belgian Malinois were not to be used without him being physically present.

    Reply

Leave a Reply to Adane Cancel reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.