ኢዜማ ከአዲስ አበባና ከባሕር ዳር ከተማ ነዋሪዎች ጋር ተወያይቷል።

Source: https://mereja.com/amharic/v2/190521
https://radiodownloaddw-a.akamaihd.net/Events/dwelle/dira/mp3/amh/C0F6583B_2_dwdownload.mp3

ኢዜማ ከአዲስ አበባና ከባሕር ዳር ከተማ ነዋሪዎች ጋር ተወያይቷል።
አዲስ አበባ
ኢዜማ በአዲስ አበባ ሜክሲኮ በሚገኘው የመብራት ሐይል አዳራሽ ከከተማዋ ነዋሪዎች ጋር መወያየቱ ታውቋል። የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በዚሁ ውይይት ላይ ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያ ተሰጥቷል።
Image may contain: 14 people, crowd«ከኢትዮጵያዊነት ከፍታ ፈፅሞ አንወርድም፤ አንፈጠፈጥም!»
«ከሕልማችን አናፈገፍግም፤ ሕልማችን እስኪወለድ ትግላችን ይቀጥላል፤ ሕልማችንን እናዋልዳለን!»
ብልፅግና ፓርቲን እንዳት ትመለከቱታላችሁ? በሚል ከስብሰባው ታዳሚ ለተነሳው ጥያቄ አንዷለም አራጌ የሰጡት ምላሽ።
«በፕላስቲክ ቀዶጥገና ማንም ተስፋ አያደርግም። ትላንት ልማታዊ ዛሬ ብልፅግና ማለት መልከጥፉን በስም ይደግፉ እንደማለት ነው። ለመታለል ፈፅሞ ዝግጁ አይደለንም።»
አንዱዓለም አራጌ
የ ኢዜማ ምክትል መሪ የመክፈቻ ንግግር

ብልፅግና ፓርቲ ምርጫውን ለማሸነፍ ከፍተኛ ገንዘብ መድቧል። እናንተ እንዴት በገንዘብ ብልፅግናና ተገዳድራችሁ እንመረጣለን ትላላችሁ? በሚል ከስብሰባው ተካፋይ ለተነሳ ጥያቄ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) የሰጡት ምላሽ።Image may contain: 10 people, crowd
«በኢትዮጵያ ውስጥ ትክክለኛ ምርጫ ተደርጎ ገንዘብ አሸንፎ አያውቅም። የኢትዮጵያ ሕዝብ 10 ጊዜ ገንዘብ ቢበተንበት ገንዘብ አያሸንፈውም። የኢትዮጵያን ሕዝብ ገንዘብ ይገዛዋል ብዬ አላስብም ።»
«ዓይናችሁን ከኳሱ ላይ እንዳታነሱ፤ ኳሱ ያለው ራስን በራስ የማስተዳደር መብት ላይ ነው።»
«የአዲስአበባ ሕዝብን ማስተዳደር ያለበት የአዲስ አበባ ከተማ ሕዝብ የመረጠው ሰው ነው። ባሕርዳን ማን ያስተዳድር ብትሉኝ የባሕርዳር ሕዝብ የመረጠው ነው። የአዳማን ከተማ ማን ያስተዳድር ቢባልም የአዳም ከተማ ሕዝብ የመረጠው ነው። የእኛ (ኢዜማ) የአዲስ አበባ ፖሊሲ የአዳማ፣ የባሕርዳር፣ የመቀሌ፣ የድሬዳዋ፣ የአሶሳ…. ፖሊሲ ነው»
ብርሃኑ ነጋ የኢዜማ መሪ

«የአዲስአበባ ሕዝብ ራሱን በራሱ ማስተዳደር ይችላል። የአዲስ

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.