ኢጋድ በቅርቡ ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ቃል የገባውን የ100 ሺህ ዶላር ግዢ ሊፈጽም ነው

Source: https://fanabc.com/2019/03/%E1%8A%A2%E1%8C%8B%E1%8B%B5-%E1%89%A0%E1%89%85%E1%88%AD%E1%89%A1-%E1%88%88%E1%89%B3%E1%88%8B%E1%89%81-%E1%8B%A8%E1%8A%A2%E1%89%B5%E1%8B%AE%E1%8C%B5%E1%8B%AB-%E1%88%85%E1%8B%B3%E1%88%B4-%E1%8C%8D/

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2011(ኤፍ.ቢ.ሲ) የምስራቅ አፍሪካ የልማት በየነ መንግስታት/ኢጋድ/ ከዚህ ቀደም ቃል የገባውን የ100 ሺህ የአሜሪካን ዶላር የታላቁ ህዳሴ ግድብ ቦንግ ግዢ በቅርቡ እንደሚፈጽም አስታወቀ።

ኢጋድ ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከዚህ ቀደም የ250 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ቦንድ ለመግዛት ቃል መግባቱ ይታወሳል።

የድርጅቱ ዋና ጸሃፊ አምባሳደር ማህቡብ ሟሊም እንደገለጹት በኢጋድና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን ጠንካራ መስተጋበር አጠናክሮ እንደሚቀጥል ነው የገለጹት።

በጅቡቲ የኢፌዴሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው በቅርቡ የተሾሙት አምባሳደር አብዱልአዚዝ መሃመድ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለኢጋድ ዋና ጸሃፊ አምባሳደር ማህቡብ ሟሊም አቅርበዋል።

በዚሁ ወቅት ባደረጉት ውይይትም በቀጣናው እየታየ ስላለው አንጻራዊ ሰላም እና የፖለቲካ መነሳሳት እንዲሁም በኢኮኖሚ ውህደት ረገድ ስለሚደረጉ ጥረቶችም ሃሳብ ተለዋውጠዋል።

በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች ኢጋድ ድጋፍ ማድረግ በሚችልባቸው ጉዳዮች ዙሪያም መመክራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

Share this post

One thought on “ኢጋድ በቅርቡ ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ቃል የገባውን የ100 ሺህ ዶላር ግዢ ሊፈጽም ነው

  1. @Solution

    መች ገዢ ጠፋና ነው ለኢጋድ የሚሸጠው። አይናችን እያየ አንዱን ብርቅዬ ሀብታችንን አሳልፈን መስጠት አይሆንብንም?!

    Reply

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.