ኢ/ር ታከለ ኡማ የህንፃ ተቋራጭ ባለቤቶች እና አማካሪዎችን አስጠነቀቁ

Source: https://fanabc.com/2019/01/%E1%8A%A2-%E1%88%AD-%E1%89%B3%E1%8A%A8%E1%88%88-%E1%8A%A1%E1%88%9B-%E1%8B%A8%E1%88%85%E1%8A%95%E1%8D%83-%E1%89%B0%E1%89%8B%E1%88%AB%E1%8C%AD-%E1%89%A3%E1%88%88%E1%89%A4%E1%89%B6%E1%89%BD-%E1%8A%A5/

አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2011(ኤፍ.ቢ.ሲ) ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሚያከናውናቸው ፕሮጀክቶች ላይ ለሚሳተፉ የህንፃ ተቋራጭ ባለቤቶች እና አማካሪዎች አስጠነቀቁ።

ኢንጅነር ታከለ በተለያየ ምክንያት ግንባታዎችን የሚያጓትቱ ኮንትራክተሮች እና አማካሪዎችን የከተማ አስተዳደሩ ከዚህ በኃላ አይታገስም ብለዋል።

እንዲሁም በግንባታ ላይ የሚገኙ ነባር ፕሮጀክቶች በተቀመጠላቸው ጊዜ ውስጥ የማይጠናቀቁ ከሆነ ውላቸው እንደሚቋረጥ አስታውቀዋል ።

በተጨማሪም በተያዘላቸው ጊዜ የተሰጣቸውን ፕሮጀክት ማጠናቀቅ ያልቻሉ እና የህዝብን ሃብት ለከፍተኛ ብክነት እየዳረጉ ያሉ ኮንትራክተሮች እና አማካሪዎች በቀጣይነትም የከተማ አስተዳደሩ በሚያወጣቸው ፕሮጀክቶች ላይ እንዳይሳተፉ እንደሚያደረግም አንስተዋል።

በመጨረሻም በከተማ አስተዳደሩ የሚገነቡት ግንባታዎች ሁሉ በአስቸኳይ ኦዲት ተደርገው ለከተማ አስተዳደሩ ኮንስትራክሽን ቢሮ ሪፖርት እንዲያደርጉ እና ኮንትክተሮች እና አማካሪዎች ፕሮጀክቶችን ኃላፊነት በተሞላበት መንገድ አጠናቅቀው እንዲያስረክቡ ማሳሰባቸውን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገነነው መረጃ ያመለክታል።

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.