ኤርሚያስ እኛኮ አንተ የምትሰራውን ነገር በደንብ ስለማናውቀው፣ በጣም እንፈራሃለን !

Source: https://mereja.com/amharic/v2/174601

“የዶሮ ሻኛ አምጣ” የሚባለው ኤርሚያስ አመልጋ ( መስከረም አበራ )
ኢትዮጵያችን በፖለቲካ ጣሯ ላይ የኢኮኖሚ ደዌ የደረበች ጎስቋላ ሃገር ነች፡፡ “አፍርሻት ልፍረስ” የሚለው የፖለቲካ ዛሯ ተሻለው ሲባል የሚብስበት መሆኑ ብቻ አይደለም ክፋቱ፣ ኢኮኖሚዋንም ይዤ ልሙት ማለቱ እንጂ፡፡ ፖለቲካና ኢኮኖሚ ሲጠፉም ሲለሙም አብረው የሆኑ መንትያዎች በመሆናቸው፣ አንዱን ለይቶ ጤናማ ማድረግ አይቻልም። ፖለቲካው ካለመፈወሱ የተነሳ ኢኮኖሚውም እንዲሁ በህመም ላይ ይገኛል፡፡ ፖለቲካውን የተጣባው ዘረኝነት፣ ኢ-ፍትሃዊነት፣ ሴረኝነት፣ ማስሰመሰል፣ እውቀት አልቦነት ሁሉ በኢኮኖሚው ላይም ይንፀባረቃል። ነግዶ ለማትረፍ፣ ተናግሮ ለመሰማት፣ ወጥቶ ለመመግባት ወሳኙ ነገር መርጠን ያልተገኘንበት ዘር፣ መቼ መናገር እንደጀመርን እንኳን የማናውቀው ቋንቋ ሆኗል፡፡
እንዲህ ባለው እጅግ ኋላቀር የፖለቲካ ከባቢ ውስጥ የኢኮኖሚ እድገት ከማምጣት ግመል በመርፌ ቀዳዳ ብትሾልክ ይቀላል፡፡ በውስብስቡ ድህረ-ዘመናዊ ዘመን እየኖርን፣ በቅድመ-የድንጋይ ዘመን ነጠላ የኑሮ ዘይቤ መኖር መርጠናል፤ የሰው ነጠላ ማንነቱ የሚናገረው ቋንቋ ብቻ ይመስለናል። ስለዚህ አሁን ያለንበትን ውስብስብ ዘመን የሚመጥን ፖለቲካና ኢኮኖሚ እንዲኖር የሚፈልጉ ሰዎችን እስከ አድማስ ዳርቻ እናሳድዳለን። ህልማቸውን፣ አበርክቷቸውን፣ ወደፊት ደግሞ ሊጠቅሙ የሚችሉትን አስበን፣ መንገዳቸውን ከማቅናት ይልቅ ትንሳኤ የሌለው ሞት እንዲሞቱ እንሰራለን። ይህን ለማድረግ ደንባደንቦችን፣ መመሪያዎችን እንደገፋለን። ፖሊሲዎቻችን ህጎቻችን እንዴት እንደሚሳካ ሳይሆን እንዴት እንደማይሳካ ይደነግጋሉ። አለማስቻልን በህግ ደንግገን እንኖራለን። ይህን ጉዳይ በተግባር የሚያሳይ አንድ ገጠመኜን ላጋራ፡፡
በቅርቡ ቪዥን ኢትዮጵያ በአዲስ አበባ ባዘጋጀው የጥናት መድረክ ተገኝቼ ነበር፡፡ የአዲስ አበባን የትራንስፖርት ችግር ለማቃለል ስራ ለመስራት ከአሜሪካን ሃገር የመጣ አንድ ወጣት፣ በዚሁ ጉዳይ ላይ

Share this post

One thought on “ኤርሚያስ እኛኮ አንተ የምትሰራውን ነገር በደንብ ስለማናውቀው፣ በጣም እንፈራሃለን !

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.