ኤርትራ አንድ የሳውዲ ባለስልጣን በኢትዮ-ኤርትራ የእርቅ ሂደት ላይ የሰጡትን አስተያየት አጣጣለች!

Source: https://mereja.com/amharic/v2/200498

ኤርትራ አንድ የሳውዲ ባለስልጣን በኢትዮ-ኤርትራ የእርቅ ሂደት ላይ የሰጡትን አስተያየት አጣጥላለች!
የሳውዲ አረቢያ የአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር አህመድ ቢን አብዱል አዚዝ ካታን ከአሽራቅ አል-አስዋት ሚድያ ጋር በነበራቸው ቆይታ “ሳውዲ አረቢያ በአፍሪካ ቀንድ ያደረገችው ተሳትፎ ውጤት እያመጣ ነው። የመጀመርያው ውጤት ደግሞ በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መሀል የተደረገው ታሪካዊ ስምምነት ነበር” ብለው ነበር።
የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስቴር በሰጠው መልስ “ይህ አገላለፅ ታሪካዊው የሰላም ስምምነት ሂደትን እና እውነቶችን ያላገናዘበ ነው። የአለም አቀፍ ተባባሪዎቻችንን በጎነት ብናደንቅም እንዲህ አይነት የበላይነት አገላለፅ የአፍሪካን ገፅታ አሳንሶ የሚያሳይ ብቻ ሳይሆን የሳውዲንም ገፅታ የሚያበላሽ ነው” ብሏል።
http://www.shabait.com/news/local-news/29956-press-release
Via Elias Meseret
Image may contain: 1 person, hat, closeup and indoor

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.