እስክንድር ነጋ ‘ሁከትና ግጭት ለመቀስቀስ በመሞከር’ ተጠርጥሮ መያዙ ተነገረ

Source: https://www.zehabesha.com/amharic/archives/107194

የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ፕሬዚደንት እስክንድር ነጋ በአዲስ አበባ ውስጥ ሁከት ለመቀስቀስ በመሞከር ተጠርጥሮ እንደታሰረ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ገለጸ። የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ምሽት ላይ የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የድንበር ተሻጋሪ ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ፈቃዱ ጸጋ እንዳሉት በአዲስ አበባ ሁከትና ግጭት እንዲፈጠር በመቀስቀስ ተጠርጥሮ በሕግ ቁጥጥር ስር መዋሉን ተናግረዋል። ኃላፊው እንዳሉት አቶ እስክንድር በአዲስ አበባ ውስጥ ቡድን በማደራጀት ወጣቶችን በተለያዩ ቦታዎች ላይ በመመደብ ሁከትን የሚያነሳሱ ቅስቀሳዎች ሲደረግ እንደነበር ጠቅሰዋል። በዚህም በሕዝቡ መካከል ግጭትን ለመፍጠር በሚችሉ ድርጊቶች ተጠርጥሮ በሕግ ቁጥጥር ሰር መዋሉን አቶ ፈቃዱ ጸጋ ተናግረዋል። የባልደራስ ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ናትናኤል ያለምዘውድ ዛሬ [ረቡዕ] ከሰዓት በኋላ አቶ እስክንድር ነጋ በፖሊስ

The post እስክንድር ነጋ ‘ሁከትና ግጭት ለመቀስቀስ በመሞከር’ ተጠርጥሮ መያዙ ተነገረ appeared first on ዘ-ሐበሻ: ZeHabesha Latest Ethiopian News Provider.

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.