እነ ወይንሸት የአጤ ቴዎድሮስን ልደት ሲያከብሩ ተይዘው ታሰሩ

Source: http://welkait.com/?p=11535
Print Friendly, PDF & Email

ወይንሸት ሞላ እና …

ነገ የሚከበረውን የአጤ ቴዎድሮስ ልደት በደመቀ ሁኔታ ለማክበር በማሰብ በዛሬው እለት አዲስ አበባ ላይ ፋሲል ከነማ ከመቀሌ ከነማ ያደረጉትን የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ለመታደም ወደስታዲየም ገብተው የነበሩት

1. ወይንሸት ሞላ (Woyinshet Molla)
2. ይድነቃቸው አዲስ መኮንን
3. አዲሱ ጌታነህ (Addisu Getaneh)

ስታዲየም ውስጥ በፖሊስ ተይዘው የታሰሩ ሲሆን የት በስፍራው የነበሩ ግለሰቦች እነወይንሸት ወደማእከላዊ መወሰዳቸውን ገልፀው የነበረ ሲሆን ከደቂቃዎች በፊት ኢንጂነር Yilkal Getnet በፌስቡክ ገፃቸው ላይ እንደገለፁት እነአዲሱ ታስረው የሚገኙት ጣይቱ ሆቴል ፊት ለፊት የሚገኘው እስር ቤት ነው።

*************

By Amanuel Abinet

“ሠላም አማኑኤል

ዛሬ ፋሢል ከናማን ከመቀሌ ከነማ ጨዋታ ለመታደም ቀኃሥ ኳሥ ሜዳ ተከስተናል። ኳሥ ሜዳ ውስጥ ለመግባት ከደጋፊው መብዛት አንፃር አስቸጋሪ ቢሆንም ቅሉ ትኬቶችን በብዙ እጥፍ በመጨመር ገዝተን ገባን። ስታዲዬሙ ሙሉ ነበር። በተለይ የፋሢል ከነማ ቦታዎች ክቡር ትሪቡን ግማሹ፣ ዳፍ ትራክና ካታንጋ መተንፈሻ አልነበረውም።

ጨዋታው ምንም አይነ ግቡ ሳይሆን በባዶ አቻ ውጤት ተጠናቅቋል። በመሃከል ሁለተኛው ክፍለ ጊዜ ሊጀመር ትንሽዬ ደቂቃዎች ሲቀሩት ግን አዲሥ ክስተት ተፈጠረ። ኳሥ ሜዳው በፋሲልና በመቀሌ ደጋፊዎች ተከፋፍሏል። ፌዴራል ፖሊሥ እጅግ በብዛት ገባ፤ በሁለቱም በኩል ሳይሆን በፋሲል ከነማ ደጋፊዎች መገኛ ሁሉ። ይሄኔ ደጋፊው የተወሰነ ተቃውሞውን አሰማ።

ከተወሰነ ደቂቃ በኃላ ጨዋታ ተጀመረ፤ ያለምንም ግብ መስተናገድም ተቋጨ። እኛ በካታንጋ በኩል የነበርን ደጋፊዎች ወጣን። ከስታዲዬም ጀምሮ እስከ አምባሳደር ድረስ በተለያዩ አቅጣጫዎች የተጓዙ ደጋፊዎች መገናኛቸውን ከላይ በ አምባሳደር፣ በምእራብ ከኢትዮጵያ ሆቴል በኩል የመጡ፣ ከታቸ የመጣው ቡድን መስቀለኛዋ መንደግ ላይ ተገናኝዐ ጭፈራው ደራ።

አማራነትን ከፍ አድርገው በመሥበክ ከሸገር ሰማይ ሥር ድምጻቸውን ከፍ አድርገው አስተጋቡ። በዚህ መሃል ከደቂቃዎች በፊት ካንድ ፌዴራል ጋር ተነጋግሬ ነበር፤ እናም እኔ አላየኃቸውም ጓደኞቼ ግን በደንብ እየተከታተሏቸው ነበር። ይሄኔ ታዲያ እኔን ለመያዝ እየተዶለተ ኖሯል። እናም ወደ እኛ ሲያመሩ ወደ ጭፈራው መሃል እንድገባና እንድንገባ ጓደኞቼ ነገሩኝ። ምንም ጊዜ ባለመግደል ከፌዴራሎች አመለጥን።

አሁን ዋናና ፋሢል ደጋፊዎችንና ፌዴራል ፖሊሶችን ያጋቸው ኩነት ሊከሰት ነው። ጭፈራው ደርቷል፤ ጉዞ ወደላይ ወደ ፖስታ ቤት እያልን ነው። ከ አምባሳደር ፊት ለፊትና ከመከላከያ ሚንስቴር ፊት ለፊት ወያኔ ሕወሓት ሥማቸው እየተነሣ ሌባነታቸው እንደጉድ ተነገራቸው፣ አፓርታይድነታቸው ተነገራቸው፣ አማራነትን ሥማ ተባሉ፣ ወያኔ በቃን የሚሉና ተንገሽጋሽነት የበዛባቸው እሮሮዎች ከመከላከያ ሚንስትር ፊት እንደጉድ ወረዱ። በዚህ መሃል የተወሰኑ ፌዴራሎች የተወሰኑ ልጆችን ያዟቸውና ወደዳር ይዘው ሲያንገሏቷቸው ፌዴራሎቹንም ሆነ ልጆቹን ያልለዬ የድንጋይ ዶፍ እንደበረዶ ፌዴራሎቹ ላይ ወረደ።

አሁን የጨበጣ ድንጋይ ውርዋሮሽ ፌዴራል ፖሊስ ከፋሲል ደጋፊዎች ሆኗል። እናም ምንም ቢሆን ፌዴራል ፖሊሶች የያዙት መሳርያም፣ ዱላምና ብዛትነታቸው ታክሎ ደጋፊዎችን ወኣአደ ተለያዬ አቅጣጫ ማሯሯጡን ተያይዘውታል፤ አንዳንዱ አልሞት ባይ ተጋዳይነቱን በተግባር አሳይቷል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በብዙ ሽህ የሚቆጠሩ ፋሲላዊያን ወደ ቸርችል ወይንም ወደ ጥቁር አንበሳ ትምህርት ቤት አባሮሹን ተባራሪነቱን ተያይዘውታል።

ጉድ ነው ኢትዮጵያዊ በኢትዮጵያዊ እንዲህ አይነት ጭካኔ ታይቶ ተሰምቶም አይታወቅ። እየሮጥን ነው ከጀርባ በዱላ የሚመቱ ልጆች በፊት ሰውነታቸው ካስፓልቱ ጋር ይገናኛል፤ በዚህ መሃል ፌዴራሉም ሆኑ ፖሊሶቹ ምን እንደሚፈጽሙ እናንተው ተፋረዱት። አሁን እኛ ከታች እንደመጣን ወደ ኢሚግሬሽን ወይንም ወደ ተክለሃይማኖት ለማምለጥ ነፍስ ውጭ ነፍስ ግቢ እያልን ነው፤ ይገርማል መቶዎች ፌደራል ቦታውን ቀድመው በመያዝ በፍቅር እየጠበቁ ነበር።

እኔና ጓደኞቼ በብርሃን ፍጥነት ወደ ተክለሃይማኖትም ሆነ ወደ ቸርችል ጎዳና ማምራታችን በመግታት ወደ ፍልውሃ ወይንም ኦርማ ጋራጅ በኩል ሾለክን። በኦርማ ጋራጅ በኩል ወደ ሎኣይ ታጥፈን ጉዞ ወደ አራት ኪሎ የሚይዘውን ጎዳና እየሸከሸክን ሳንባችንን ታቅፈን ጦሣ ሆቴልን ትንሽ መቶ ኪሎ ሜትሮች እንዳለፍን ከሰይጣን ቤት በኩልና ከላይ ካራት ኪሎ በኩል የሚመጣውን መንገድ በማቋረጥ ወደ ፒያሳ ልናመልጥ ትንሽ ኪሎ ሜትር እንደተጓዝን የፋሲል ደጋፊዎች የሆኑ በፌዴራል እየተሯሯጡ እንደሆነነ የፋሲልን ማሊያ የለበሰ እየተመረጠ በፌዴአራሎች ፒካፕና በፖሊሶች ፒካፕ በትብብር እየጫኑ እንደሆነ ይነግሩንና እንዳጋጣሚ ሁላችንም ሸሚዝ ኮት ቢጤ ይዘናል። በሉ ሁላች ሁም ከላይ የፋሲልን ማሊያ ሸፍኑት ደርቡት አሉንና ቶሎ እንድናመልጥ መረጃው ደረሰንር።

በብርሃን ፍጥነት ምክሩ ወደ ተግባር ተቀየረ።ጉዞ ወደ ኃላ አልንና አስፓልት እንደደረስን ወደ እሪ በከንቱ ውስጥ ለውስጥ ሩጫችንን በመሸምጠጥ ዋናው አስፓልት ጋር ስንደርስ ወደ ፒያሳ ማሳለጫ ውስጥ ውስጡን አፈላለግንና ፒያሳ ጣይቱ ሆቴል ከትመናል። አሁን ሌላኛው ትኩረት ሳቢ ኩነት ፊታችን ላይ ቆሟል።

ከጣይቱ ሆቴል በር ላይ ብዙ ፌዴራሎች አሉ፣ ጎንደር ሆቴል ላይም በተመሳሳይ ፌዴራሎች ሰፍረዋል። ይህ አካባቢ በብዙ ፒካፖችና ዶልፊኖች ተሞልቷል፤ ውስጣቸውን የሞላው ደግሞ የፋሲልን ማሊያ የለበሰ ደጋፊ ነው። አሁን ሁሉንም እያንገላቱ የትግሬዎች ከሆነው ጎንደር ሆቴል ፊትለፊት ካለው ፖሊስ ጣቢያ አስገቧቸው። አሁንም እንዳበደ ውሻ በመቅበዝበዝ ሌሎችን ለማፈን ከወዲያ ወዲህ እየተሯሯጡ ነው። እንዳጋጣሚ ሆኖ ይህንን ትእይንት የሚመለከቱ የጣይቱ ሆቴል ቤተኞች ጣይቱ በር ላይ ተኮልኩለዋል።

እኛም የጣይቱ ተጠቃሚ እንደመሆናችን መጠን ከሰዎቹ ጋር እንተዋወቃለንና ማሊያ እንደለበስን ሥለሚያውቁና ከስታዲዬም እንዳመለጥን ሥላወቁ እናንተን ሊይዟች ሁ ነው አምልጡ አሉን። በዚህ መካከል ማምለጫው መከራ ነው፤ መንገዱ ሁሉ ፌዴራልና ወጥመድ ነው። ይሁንና ደፋርና ጭስ መውጫ አያጣም ይላልና ብሂሉ እኛም ከሆነም ይሁን በማለት ጉዞ ወደ አራዳ ተመረሸ።

አሁንም አራዳ መስቀለኛ መንገድ በሰው በላዎች ተሞልቷል። ሆኖም ግን ማንን ከማን መለየት ስለማይችሉ አባሮሹ ረብ ብሏል። እናም በፍጥነት ወደ አራዳ ህንጻ በመዝለቅ ወደ አንደኛው ግሮሰሪ ጎራ በማለት በረንዳ ላይ ሆነን ኩነት ውጩን መከታተል ጀመርን። አንድ አንድ እንዳልን ወደ ጓደኞቻችን ደውለን መኪና እንዲያመጡልንና እንዲወስዱን በማናገር ከቆይታ በኃላ በፈጣሪ ቸርነት ከሰው በላ አውሬዎች በመትረፍ አሁን ከምሽቱ ሶስት ተኩል በየቤታችን ከተምን። ሆኖም ግን ብዙ ውድ ወገኖቻችን በየፖሊስ ጣቢያው እንደታጎሩ፣ በየመንገዱ እንደተቀጠቀጡ፣ በየቁራንጉሩ እንደተሳደዱ፣ የፋኢል ማሊያና ኃላ ላይ አማራ የሚል መታወቂያ የያዙ ውድ ወገኖቻችን ባውሬዎች እጅ ወድቀዋል።”
.
አማራ ከሆንክ እንዲህ ትንከራተታለህ!!

ግዮናዊት መዳኛችን!!

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.