እንኳን መሞት አለ ማርጀት (ዘ-ጌርሣም)

Source: https://www.zehabesha.com/amharic/archives/107130

  አያ እርጅና ተደብቀህ ትከርምና ሰዎችን አዘናግተህ ትመጣለህ ዕድሜ ቆጥረህ ቀርቷል ተብለህ ስትታማ ከች ትላለህ ሳታቅማማ እንኳን መሞት አለ ማርጀት ብሎ ነበር የኔ አባት ስለገባው መዳከሙ እጅና እግሩ መዛሉ አያ እርጅና እንዴት ከረምክ ዕድሜ አስልተህ ከየት ብቅ አልክ ማሸበቱ ሳይበቃህ የራስ ፀጉር መጨረስህ ፊትን አጨማዶ መጅራትን ጨምድዶ ዓይኖችን አሞጭሙጨህ ወገብን አሽመድምደህ ጉልበተን በማንበርከክ ህዝበ አዳምን ጉድ አረክ ትልቁን ትንሽ አርገህ ነበርኩ እንዲል አሰኝተህ በጫማህ ስር አዋልከው የሰው እጅ አሳየኽው ሴት ወንዱን ስታስፈራራ ዕድሜን በውል እንዳይጠራ ሽማግሌ ላለመባል ራሱን እንዲሸነግል ድንገት ብቅ ትልና ትለዋለህ ወደኔ ና ማን አለብኝ ብሎ ሲኩራራ ትቢት ይዞት ሲንጠራራ ሁብታም ነኝ ብሎ ሲደነፋ በአፍ በጢሙ ሰው ሲያዳፋ

The post እንኳን መሞት አለ ማርጀት (ዘ-ጌርሣም) appeared first on ዘ-ሐበሻ: ZeHabesha Latest Ethiopian News Provider.

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.