እእ እንደንታለል፣ እንዳንደለል፣ እንዳንዘናጋ እንጠንቀቅ!!

Source: https://kalitipost.com/%E1%8A%A5%E1%8A%A5-%E1%8A%A5%E1%8A%95%E1%8B%B0%E1%8A%95%E1%89%B3%E1%88%88%E1%88%8D%E1%8D%A3-%E1%8A%A5%E1%8A%95%E1%8B%B3%E1%8A%95%E1%8B%B0%E1%88%88%E1%88%8D%E1%8D%A3-%E1%8A%A5%E1%8A%95%E1%8B%B3/

ወያኔ የፖለቲካ እስረኛ ወገኖቻችንን ሊፈታ እንደሆነ ዛሬ አስታውቋል፡፡ ሁሉንም ሊፈታ ይሆን ወይም በከፊል የታወቀ ነገር የለም፡፡ እነማንን ፈትቶ እነማንን ሊያስቀር እንደሆነም እንዲሁ የታወቀ ነገር የለም፡፡ ሁሉንም ማለትም አማራነታቸው ኃጢአት ሆኖባቸው በመንግሥት ግልበጣ ስም ወኅኒ ተወርውረው እየማቀቁ ያሉ የጦር መኮንኖች ወገኖቻችንን ጨምሮ ይፍታ አይፍታ የታወቀ ነገር የለም፡፡

በግሌ ሁሉንም ይፈታል የሚል እምነት የለኝም፡፡ ሁሉንም የሚፈታ ከሆነ መልካም ነው፡፡ በዚህ ብደሰትም ግን አልፈነጥዝም! እንደ ሕፃን ደረኔን እየመታሁ የምፈነትዘው ሀገሬና ሕዝቧ ከወያኔ አስከፊ እስራት በተፈቱ፣ ነጻ በወጡ ጊዜ ነው፡፡ ይሄ እስኪሆን ድረስ ከመቸውም ጊዜ በላይ ልንበረታ እንጅ በመጭዎቹ ቀናት ወያኔ ሕዝብን ለመደለል፣ ለማዘናጋት፣ ለማታለል በሚወስዳቸው የማዘናጊያ፣ የማታለያ እርምጃዎች ተደልለን ተዘናግተን ልንቀመጥ፣ ሀገርንና ሕዝቧን ከአስከፊ እስራትና አገዛዝ ከማስፈታት፣ ነጻ ከማውጣት ለቅጽበት እንኳ ልንታቀብ ፈጽሞ አይገባንምና እንዳንዘናጋ እንጠንቀቅ!

በተረፈ ለተፈች እኅት ወንድሞቻችን ሁሉ እንኳን እግዚአብሔር አስፈታቹህ! ከትግሌ በተጨማሪ የዘወትር ጸሎቴም ነበርና፡፡

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪያን አርጋው
amsalugkidan@gmail.com

 

Share this post

One thought on “እእ እንደንታለል፣ እንዳንደለል፣ እንዳንዘናጋ እንጠንቀቅ!!

  1. gobez weyane birr selechegerat yehenen tera zede ametach. mefetatachew des yilal. medeleya selehone weyanen kenezermanzerachew maswegedachen ayseram. yane Ethiopia nesa tewetalech.

    Reply

Post Comment