ኦሮሚያ የአዲስ አበባ ጐረቤት እንጂ ባለቤት አይደለችም – ጋዜጠኛና አክቲቪስት እስክንድር ነጋ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/105297

ቃለ ምልልስ – አዲስ አድማስ ጋዜጣ
“ኦሮሚያ የአዲስ አበባ ጐረቤት እንጂ ባለቤት አይደለችም” – ጋዜጠኛና አክቲቪስት እስክንድር ነጋ
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የአዲስ አበባ የባለቤትነት ጥያቄ በእጅጉ እያወዛገበ ይገኛል፡፡ የኦሮሞ አክራሪ ብሔርተኛ ፖለቲከኞችና አክቲቪስቶች ብቻ ሳይሆኑ የኦሮሚያ ክልልን የሚመራው ኦዴፓ በድፍረት ሲያቀነቅነው ነበር፡፡ የአማራ ክልልን የሚመራው አዴፓም አልቀረለትም፡፡ ከአዲስ አበባ የባለቤትነት ጥያቄ ውዝግብ ጋር ተያይዞ በቅርቡ በባልደራስ የመዲናዋን ነዋሪዎች ስብሰባ የጠራው ጋዜጠኛና አክቲቪስት እስክንድር ነጋ፤ “የአዲስ አበባ ባለአደራ ም/ቤት”
ማቋቋሙ ይታወቃል፡፡ ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ሰሞኑን በሰጡት መግለጫ፤ የባለአደራ ም/ቤት የሚባለው “አገር ስለሚያፈርስ ተገቢ ያልሆነ እንቅስቃሴ ነው” ብለዋል፡፡ “የባለ አደራ ም/ቤት” ሰብሳቢው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በጉዳዩ ላይ ምላሽ እንዲሰጠን አጭር ቃለ ምልልስ አድርገንለታል፡፡ እነሆ፡-

ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ፣ ሰሞኑን በአዲስ አበባ ጉዳ ይ ላይ ሲናገሩ “ባለአደራ ማቋቋም ጨዋታ ነው” ብለዋል፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ምን አስተያየት አለህ?
ጠ/ሚኒስትሩ ብዙ ነገሮች ተናግረዋል፤ አንዱ ባለአደራ ማቋቋምን በተመለከተ ነው። ባለአደራ በየቦታው ተቋቁሞ የኢትዮጵያ አንድነትን አደጋ ውስጥ ይጥላል ያሉትን ነገር እኛም እንቀበለዋለን፤ ምክንያቱም የእኛም እንቅስቃሴ ገዢ ሃሳብ ስለሆነ። እኛ በሁለት ነገሮች አንደራደርም እንላለን፤ አንዱ የኢትዮጵያ አንድነት ነው፡፡ ይሄም ማለት የኢትዮጵያ አንድነትን የሚያናጉ ማናቸውንም አይነት እንቅስቃሴዎች አናደርግም፡፡ ጥያቄያችን ውስጥ የኢትዮጵያን አንድነት ማስጠበቅ የሚል ሃሳብ ስላለ የጠ/ሚኒስትሩን ንግግር እንቀበለዋለን፡፡
ባለአደራ እየተባለ በየቦታው ሲቋቋም፣ ለኢትዮጵያ አንድነት ስጋት መሆን የለበትም ማለታቸውን እንቀበላለን ስንል፤ ኢትዮጵያ ውስጥ በህዝብ የተመረጠ መንግስት የለም ተብሎ፣ በየቦታው

Share this post

2 thoughts on “ኦሮሚያ የአዲስ አበባ ጐረቤት እንጂ ባለቤት አይደለችም – ጋዜጠኛና አክቲቪስት እስክንድር ነጋ

 1. I WOULD LIKE TI INVITE ESKENDIR TO READ THID PROFESIONAL ARTICLE

  Zehabesha Amharic
  ETHflag_1__1_

  HOME
  MAIN PAGE
  የዕለቱ ዜናዎች
  ነፃ አስተያየቶች
  ጤና
  ስፖርት
  ኪነ-ጥበባዊ ዜና
  ህብር ሬዲዮ
  ETHIO NEWSLINK
  ENGLISH
  መነሻ ገጽ
  About Us
  Contact Us
  Ads Rate
  Legal Statements
  Ethio Newslink

  Search in site…
  Search in site…
  አዲስ አበባ ከአቡጃ እና ከብራሰልስ ልትማር የሚገባት ተሞክሮ – ይርጋለም (PhD.)
  March 24, 2019 | Filed under: ነፃ አስተያየቶች | Posted by: ዘ-ሐበሻ
  331
  SHARES
  FacebookTwitter
  x
  ይርጋለም (PhD.)

  በኢትዮጲያ ውስጥ ለተከሰተው ለውጥ የአዲስ አበባ ጉዳይ እንደ አንድ የለውጡ አቀጣጣይ ነዳጅ ቢሆንም ከተማዋ የለውጡን ትግል በመምራትም ሆነ በመሳተፍ የጎላ ሚና አልነበራትም። በዚህ ምክንያት አዲስ አበባ መቼነው ከእንቅልፏ የምትነቃው እየተባለች ስትወቀስ ቆይታለች። በእኔ እይታ አዲስ አበባ ለለውጡ ጉልህ ሚና ያልተጫወተችው አንቀላፍታ ሳይሆን ለዘመናት መፍትሄ ባላገኘው የማህበራዊ፤ ምጣኔ ሀብታዊ እና ፖለቲካዊ ችግር የተነሳ በስጋት ደመና ስለተከበበች ነው። የዚህ ጽሁፍ አላማ አሁን አዲስ አበባ ያለችበትን ሁኔታ ከከተማዋ ታሪክ ጋር በማገናዘብ መዳሰስ እና አዲስ አበባ ከተከበበችበት ዘርፈ ብዙ ችገሮች የመውጫ በሮችን ለመጠቆም ነው። ይህ ጽሁፍ የግል ሙያዊ አስተያየት ሲሆን በአዲስ አበባ ላይ አሁን እየተንጸባረቀ ያለውን የማንንም አጀንዳ በመደገፍ ወይም በመቃወም ላይ የተመሰረተ አይደለም።

  አዲስ አበባ የማናት?

  ይህ ጥያቄ የሰሞኑ የአገሪቱ የፖለቲካ ትኩሳት፤ የማህበራዊ መድረክ የንትርክ አጀንዳ፤ የአደባባይ ተቃውሞ እና የከተማዋ የስጋት ምንጭ ሆኖ ሰንብቷል። ጥያቄውም ሆነ የሚሰነዘረው መልስ ስሜታዊ እና ቁጣ አዘል ከመሆኑ የተነሳ ለችግሩ መፍትሄ ከመስጠት ይልቅ ነገሩን ወደ ግጭት ሊያመራው ይችላል። ብዙ ሰው አዲስ አበባ የማናት የሚለውን ጥያቄ የጎሳ ፌድራሊዝም ያመጣው ጣጣ ነው ብሎ ያምናል። በመሰረቱ የጎሳ ፌድራሊዝም ኖረም አልኖረም ይህ ጥያቄ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በብዙ አግሮች የሚነሳ ጥያቄ ነው። በርሊን (ከጀርመን)፤ ብራሰልስ (ቤልጂየም) ዴልሂ (ህንድ)፤ እንዲሁም አቡጃ (ናይጄሪያ)ከአዲስ አበባ ጋር የሚያመሳስላቸው ጉዳይ ስላለ ከእነሱ ልምድ መቅሰም ይቻላል። ይህንን በሚመለከት ወደፊት ጊዜ ሳገኝ በሰፊው እመለስበታለሁ። ወደ ዋናው ጉዳይ ስመለስ፤ አዲስ አበባ የማናት የሚለው ጥያቄ በእኔ እይታ ምንጩ አዲስ አበባን የራስ ከማድረግ ፍላጎት የመነጨ ሳይሆን ከፍትሃዊ ተጠቃሚነት እና ከስጋት የመነጨ ጥያቄ ነው። ይህንን የፍትህ እና የስጋት ችግር መፍታት የሚቻለው ለአዲስ አበባ ባለቤት በማፈላለግ ሳይሆን ስጋትን አስወግዶ ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን በማስፈን ብቻ ነው። ስለዚህ አዲስ አበባ የማናት የሚለው ክርክር ጉንጭ ከማልፋት የዘለለ ፋይዳ የለውም።

  አከራካሪው “ልዩ ጥቅም”

  የኢትዮጵያ ህገመንግስት በአንቀጽ 49 ቁጥር 5 እንዲህ ይላል “የኦሮሚያ ክልል፤ የአገልግሎት አቅርቦት ወይም የተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀምንና የመሳሰሉትን ጉዳዮች በተመለከተ፣ እንዲሁም አዲስ አበባ በኦሮሚያ ክልል መሐል የሚገኝ በመሆኑ የሚነሱ ሁለቱን የሚያስተሳስሩ አስተዳደራዊ ጉዳዮች በተመለከተ ያለው ልዩ ጥቅም ይጠበቅለታል፡፡ ዝርዝሩ በሕግ ይወሰናል፡፡” ይህ አንቀጽ የአዲስ አበባ አስተዳደር ከኦሮሚያ ክልል ጋር ለሚኖራት ዘርፈ ብዙ ግንኙነቶች ጥሩ መነሻ ቢሆንም ዝርዝር ጉዳዮቹ በወቅቱ በህግ ባለመወሰናቸው እና “ልዩ ጥቅም” የሚለው ሃረግ ስላልተብራራ ለአሻሚ ትርጉም በር ከመክፈቱም በላይ በአዲስ አበባ ጉዳይ “ልዩ ጥቅም ማለት የባለቤትነት ማረጋገጫ ነው” በሚሉ እና “ልዩ ጥቅም የሚባል ነገር የለም” በሚሉ ሁለት ጫፍ የረገጡ ቡድኖችን ፈጥሮ የአዲስ አበባን ችግር እያወሳሰበው ይገኛል።

  ልዩ ጥቅም ማለት ምን ማለት ነው?

  በህገመንግስቱ ውስጥ ልዩ ጥቅም የሚለው ሐረግ ከኢንግሊዝኛው “እስፔሻል ኢንተረስት” በቀጥታ የተወሰደ ሲሆን የአማርኛው ትርጉም ሙሉ በሙሉ የኢንግሊዝኛውን ሃሳብ አይገልጸውም። ህገመንግስቱ በተጻፈበት አውድ መሰረት እስፔሻል ኢንተረስት ማለት ሁለት ወገኖች ወይም ቡድኖች ተደራድረው አንዱ የሌላውን ጥቅም በማይጎዳ መልኩ የድርድሩ ውጤት ተጠቃሚ የሚሆኑበት አሰራር ማለት ነው። ይህ አሰራር ደግሞ በየትኛውም ፌድራሊዝምን በሚከተሉ አገሮች የሚሰራበት መንገድ ነው። አዲስ አበባ ላይ ችግር የፈጠረው ልዩ ጥቅም የሚለው ስላልተብራራ እና የፌደራሉ መንግስት በጊዜው የህግ ማሰሪያ ሳያዘጋጅ ከተማዋ “በመመሪያ ቁጥር አንድ እና ሁለት” እንድትመራ ስለፈቀደ ነው።

  ልዩ ጥቅም ማለት የጉዳት ማካካሻ ነው

  የአዲስ አበባን ከተማ ወደ የትኛውም ክልል ብንወስዳት በዙሪያዋ ለሚገኝ ክልል የምታመጣው ጥቅም እና ጉዳት አለ። ይህ ደግሞ የማናስቀረው የማንኛውም ከተማ ተፍጥሮዊ ባህሪ ነው። ከሌሎች አገሮች ልምድ ስንነሳ የልዩ ጥቅም መሰረታዊ ሃሳብ በፌድራል ከተማ ዙሪያ የሚገኝ ክልል ለከተማዋ ካለው ቅርበት አንጻር የሚፈጠረውን ማህበራዊ እና ምጣኔ ሀብታዊ ጥቅም በማጎልበት የፌደራል ከተማዋ በክልሉ ላይ ለምታሳድረው ተጽዕኖ ተገቢ እና ፍትሃዊ ማካካሻ ክልሉ እንዲያገኝ የህግ አሰራር መዝርጋት ማለት ነው።

  አዲስ አባባ ለጎረቤት ከልል የምትስጠው ጥቅም

  በየትኛውም ሃገር የፌድራል ከተማ ከሌሎች ከተሞች የተሻለ የማህበራዊ፤ የምጣኔ ሃብታዊ፤ የጤና እና የመሰረተ-ልማት አገልግሎቶች ያገኛሉ። ከፌድራል ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ የሚገኙ የክልል አስተዳደሮችም የዚሁ እድል ተጠቃሚ ናቸው። አዲስ አበባም እነዚህ ከላይ የተጠቀሱትን ግልጋሎቶች ስትሰጥ ኖራለች ወደፊትም ትሰጣለች። ሌሎች ከልሎች ከአዲስ አበባ ርቀው ስለሚገኙ የዚህ እድል ተጠቃሚ አይሆኑም። ይህ ደግሞ አዲስ አበባ ለጎረቤት ከልል ከምትሰጠው ልዩ ጥቅም አንዱ ነው። ሌሎችንም ብዙ መዘርዘር ይቻላል።

  አዲስ አበባ በጎረቤት ከልል ላይ የምታሳድረው አሉታዊ ተፅዕኖ

  ማንኛውም ከተማ ይወለዳል፤ ያድጋል፤ እንዲሁም ይሞታል። በዚህ ሂደት ውስጥ ከተማ ለእድገቱ የሚሆን ግብአትን በአብዛኛው የሚያገኘው ከጎረቤት ክልል ነው። በተጨማሪም በከተማው ውስጥ የሚፈጠረው ደረቅ እና ፈሳሽ ቆሻሻ የሚወገደው በጎረቤት ክልል በሚገኝ መሬት ላይ ነው። አዲስ አበባ ለእድገቷ እና መስፋፋቷ የሚያስፈልጋትን የግንባታ እና ሌሎች ግብአቷን በብዛት የምታገኘው ከኦሮሚያ ክልል ነው። እንዲሁም ከተማዋ ደረቅ እና ፈሳሽ ቆሻሻዎችን ለማስወገድ የሚያስፈልጋትን መሬት የምታገኘው ከዚሁ ክልል ነው። የአዲስ አበባ ከተማ በኦሮምያ ክልል መንግስት እና በአዲስ አበባ ዙሪያ ባሉ መስተዳድሮች ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እንዳላት የማይካድ ሃቅ ነው። ይህንን አሉታዊ ተፅዕኖ አዲስ አበባ ለጎረቤቷ በምትፈጥረው መልካም አጋጣሚ ማካካስ ሲቻል በአስተዳደራዊ ድክመት እና የተሳሳተ ፖሊሲ ምክንያት ይህ ባለመደረጉ በአዲስ አበባ እና በጎረቤት ክልል መካከል ያለው ግኑኝነት መርህ አልባ እና አወዛጋቢ ሆኖ ቆይቷል። ይህ ውዝግብ አድጎ መንግስትን ዋጋ እያስከፈለ ሲገኝ የአዲስ አበባን ነዋሪዎች ስጋት ላይ ሲጥል እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል “የልዩ ጥቅም” ጥያቄን አስከትሏል። ይህንን ችግር ለመፍታት ከስሜት የጸዳ የሰከነ ውይይት፤ ሃገራዊ ሃላፊነት፤ የፖለቲካ ቁርጠኝነት፤የህግ የበላይነት እና የሌሎች ሀገሮችንም ልምድ መቅሰም ግድ ይላል።

  ከአቡጃ (ናይጄሪያ) ምን እንማራለን?

  አቡጃ የናይጄሪያ የፌድራል ከተማ ስትሆን ከተመሰረተች ሃምሳ አመት አይሞላትም። ከአቡጃ በፊት የናጄሪያ ዋና ከተማ ሌጎስ ስትሆን አቡጃ አዲሷ የናይጄሪያ ፌድራል ከተማ ሆና የተመረጠችበትን ምክንያት የወቅቱ የናጄሪያ መሪ እንዲህ በማለት ነበር ያስረዱት “አዲሲቷ ከተማ ሁሉንም የናይጄሪያ ጎሳዎች በእኩል የምታገለግል የአንድነት ተምሳሌት ናት” በማለት ነበር። ምንም እንኳን አቡጃ የተመሰረተችበት ቦታ የብዙ ብሄረሰቦች መኖሪያ ቢሆንም ዋና ከተማዋ ከተመሰረተች በኋላ የየትኛውም ብሄር ሳትሆን የናይጄሪያውያን የአንድነት ተምሳሌት ሆና እያገለገለች ትገኛለች። አቡጃን ለመመስረት ናጄሪያውያን ከዋሽንግተን ዲሲ (ዩናይትድ ስቴትስ)፤ ከብራዚልያ (ብራዚል)ከኢዝላማባድ (ፓክስቲያን)፤ ከፒተርስበርግ (ሩሲያ)እና ከፓሪስ (ፈረንሳይ) በቂ ልምድ ቀስመዋል። ከእነዚህ ሃገሮች በወሰዱት ልምድ መሰረት የአቡጃ ከተማ ምስረታ ሰነድ ላይ የሚከተሉትን ጠቃሚ ነጥቦችን አካተዋል።

  የአቡጃ ከተማ ህጋዊ ድንበር እና የወደፊት የመስፋፊያ መሬት ባንክ በግልፅ እና በዝርዝር ተቀምጧል።
  አቡጃ ስትመሰረት ከመሬት ይዞታቸው ለሚፈናቀሉ ዜጎች የካሳ ክፍያ እና መልሶ ማቋቋሚያ ዝርዝር መመሪያ ተካቷል።
  የመሬት ወረራን እና ሌብነትን የሚከላከል ጠንካራ ተቋም ተፈጥሯል።
  የአቡጃ ምስረታ ለናይጄሪያውያን አዲስ የፍትህ፤የሰላም እና የአንድነት ዘመን ብስራት መሆኑ ታውጇል።
  አቡጃን የአንድነት ማእክል ብሎ ሰይሟል።
  ዛሬ እያንዳንዱ ናይጄሪያዊ አቡጃ የማነች ለሚለው ጥያቄ አጥጋቢ መልስ ስላለው አቡጃ የማነች ብሎ አይወዛገብም። ለዚህ ምክኒያቱ ደግሞ የአቡጃ ከተማ የእያንዳንዱ ናይጄሪያዊ እንደሆነች የምስረታ ሰነዱ ስለ ሚናገር ነው። እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት የአቡጃ ተሞክሮ ዛሬ አዲስ አበባ ካለችበት አጣብቂኝ እና ስጋት ውስጥ ለማውጣት በብዙ ሊጠቅመን ይችላል።

  ከብራሰልስ (ቤልጂዬም)ምን እንማራለን?

  ኢትዮጵያ እና ቤልጂዬም በብዙ ነገር ቢለያዩም የፌድራል አመሰራረታቸው የመመሳሰል ባህሪ አለው። የትኛውም የፌድራሊዝም አስተዳደር መነሻ ሃሳቡ ሁለት ነው። የተለያዩ ራሳቸውን የቻሉ ግዛቶች ለመተባበር እና አንድ ላይ ለማደግ በመስማማት የሚጣመሩበት የፌድራል አስተዳደር የመጀመሪያው ሲሆን ለዚህም ጥሩ ምሳሌ የሚሆኑት ጀርመን እና ዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ ናችው። ሁለተኛው የፌድራል መነሻ ሃስብ በአሃዳዊ አስተዳደር የሚተዳደሩ ግዛቶች እራስን በራስ ለማስተዳደር ከመነጨ ፍላጎት ወደ ፌድራል አስተዳደር የሚሸጋገሩበት ሂደት ነው። ኢትዮጵያ እና ቤልጅዬም ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ናቸው። ኢትዮጵያ እና ቤልጅዬም በፌድራል አወቃቀርም የመመሳሰል ባህሪ ይታይባቸዋል። የቤልጅዬም ፊድራሊዝም የተዋቀረው ማህበረሰብን፤ ቋንቋን እና ከልልን አንድ ላይ በማጣመር የተዋቀር ሲሆን የኢትዮጵያ ደግሞ ቋንቋን እና ብሄርን መሰረት ያደረገ ነው። የቤልጅዬም የፌድራሊዝም አውቃቀር በሶስት ክልል የተክፈለ ሲሆን፤ የፍሌሚሽ ክልል (የፍሌሚሽ ማህበረስብ በብዛት ይሚኖርበት)፤ የዋሉን ክልል (የፈረንሳይ ማህበረሰብ በብዛት ይሚኖርብት) እና የብራስለስ ክልል (የፌድራሉ ዋና ከተማ) ተብለው ይጠራሉ። ብራስልስ እንደ አዲስ አበባ ዋና ከተማነቱን ከአሃዳዊ አስተዳደር ወደ ፌድራሊዝም ይዞ የተሸጋገረ ከተማ ነው። ይሁን እንጂ የፌድራል ስርዓቱ ሲዋቀር ብራሰልስ በአዲስ መልክ በአስራ ዘጠኝ የመዘጋጃ አስተዳደር ተዋቅሯል። ከዚህ ውስጥ አንዱ መዘጋጃ ብራስልስ ሲሆን ሌሎቹ አስራ ስምንቱ የመዘጋጃ አስተዳደሮች የብራስልስ የመስፋፊያ ዞኖች ተብለው የተዋቀሩ ናቸው። ብራሰልስ በፍሌሚሽ ማህበረሰብ ክልል ተከቦ ያለ ክልል በመሆኑ ፍሌሚሾች በየጊዜው መሬታችን ተወሰደ የሚል ቅሬታ ያቀርባሉ። ይሁን እንጅ ይህ ቅሬታ በፌድራል መንግስት እና በክልሉ መንግስት መካክለ በተደረገ ድርድር መሰረት ብራስልስ ከአስራ ዘጠኙ መዘጋጃ ውጭ እንዳትስፋፋ በመገደብ የመሬት እጥረት ሲፈጠር በፌድራል እና በከልሉ መንግስት መካካል በሚደረግ ድርድር ይወሰናል በሚል ሃሳብ በመስማማት ቅሬታውን ማስወገድ ተችሏል። እንደ አለመታደል ሆኖ ኢትዮጵያ ከአሃዳዊ አስተዳደር ወደ ፌድራሊዝም ስትቀየር አዲስ አበባ ላይ መሰራት የነበረበት ስራ አልተሰራም። አሁንም ዋጋ ቢያስከፍልም ከአቡጃ እና ብራሰልስ ልምድ ወስዶ የተበላሸውን ለማስተካከል እድል አለ።

  ከአዲስ አበባ ታሪክ ምን እንማራለን?

  የዚህ ጽሁፍ አቅራቢ አዲስ አበባን በሚመለከት ሰፊ ጥናት አድርጎ ከአራት በላይ ጥናታዊ ጽሁፎችን አሳትሟል። በዚህ ሂደት ውስት ጸሃፊው ያስተዋለው ነገር ቢኖር አዲስ አበባ ማንነቷን የተቀማች የመሪ እቅድ መሞከሪያ ቤተ-ሙክራ እንደሆነች ነው። በእኔ እምነት የአዲስ አበባ ህጋዊ እና ፖለቲካዊ ማንነት በህግ ካልተረጋገጠ የአዲስ አበባን የባለቤትነት ጥያቄ መመለስ አይቻልም። በመጀመሪያ አዲስ አበባ እንዴት የመሪ እቅድ ወይም ማስተር ፕላን ቤተ-ሙከራ እንደሆነች ላስረዳ እና ከዛ ወደ ማንነት ጥያቄ እመለሳለሁ።

  አዲስ አበባ ስትቆረቆር የኢትዮጵያውያንን የቦታ አጠቃቀም እና የማህበረሰብ አሰፋፈር ፍልስፍና የተከተለ ነበር። ይህም የመኖሪያ ሰፈርን፤ የእምነት ማዕከልን፤ የገበያን እና የፖለቲካ ማዕከልን ለይቶ በማስቀመጥ ነው። አዲስ አበባ ስትመሰረት ስዕል-1 ላይ የተቀመጠውን ገጽታ ይዛ ሲሆን ይህንን አገር በቀል መሪ እቅድ (ማስተር ፕላን) ወደ ዘመናዊ የከተማ መሪ እቅድ ማሸጋገር ተስኗት የሌላ አገር መሪ እቅድ ፍልስፍና እና ርዕዮተ-አለም በግድ ሲጫንባት ቆይቷል።

  ጣልያን አዲስ አበባን ከተቆጣጠረች ሶስት ወር በኋላ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር 1936 ሊ-ኮርቤዥር የተባለ ፈረንሳዊ እና የሲዊዘርላንድ ዜጋ ያለው ታዋቂ የስነ-ህንጻ ባለሙያ ለሞሶሎኒ የአዲስ አበባን መሪ እቅድ በማዘጋጀት እንደሚረዳው በመግለጽ ደብዳቤ ይጽፍለታል። ሞሶሎኒም በሃሳቡ ተደስቶ በምስራቅ አፍሪካ የታላቋን ጣሊያን የቅኝ ግዛት ከተማ ማየት እንደሚፈልግ ህልሙን ነገረው። ሊ-ኮርቤዥርም የሞሶሎኒን ህልም ከራሱ ፍልስፍና ጋር በማዋሃድ በአካል አይቷት ለማያውቀው ከተማ እና ለማያውቀው የኢትዮጵያ ህዝብ በሰዕል-፪ የተቀመጠውን መሪ እቅድ አዘጋጀ። ይህ ግዴለሽነት እና ቅዠት የተቀላቀለበት መሪ እቅድ ከአዲስ አበባ ውጭ በአለም ላይ የትም ሃገር ተሞክሮ አያውቅም። አዲስ አበባ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ እራሷን ሳትሆን የባእድ የመሪ እቅድ መጫወቻ ሜዳ ሆና ረጅም ዘመን ተጉዛለች።

  በስዕል-2 ላይ የተቀመጠው የአዲስ አበባ መሪ እቅድ ከዚህ በፊት አዲስ አበባ የምትባል ከተማ እንደሌለች በመቁጠር በባዶ ሜዳ ላይ ተግባራዊ እንዲሆን ታቅዶ የተዘጋጀ መሪ ዕቅድ ነበር። ይሁን እንጂ በዚያን ወቅት አዲስ አበባ ከአየር ላይ ስትታይ ባዶ መሬት ሳትሆን በስዕል-3 ላይ የተቀመጠው ገጽታ ነበራት።

  ከሁለተኛው የአለም ጦርነት በኋላም አዲስ አበባ የመሪ ዕቅድ መሞከሪያ ሜዳ ሆና የእንግሊዝ እና የፈረንሳይ ታዋቂ የከተማ መሪ እቅድ ባለሙያዎች የአዲስ አበባ ከተማ መሪ እቅድ በማዘጋጀት ላይ በዋናነት ተሳትፈዋል። ለምሳሌ፤ ታዋቂው የሎንዶን መሪ እቅድ አዘጋጅ አቤርክሮምባይ እንዲሁም የፓሪስ ከተማ መሪ እቅድ አዘጋጅ ዲማራይን አዲስ አበባ ሎንዶንን እና ፓሪስን እድትመስል መሪ እቅድ አዘጋጅተውላት ነበር። በደርግ ዘመን ደግሞ አዲስ አበባ የሶሻሊስት ከተማ እንድትመስል ተፈርዶባት ነበር። በዚህም መሰረት የደርግ መንግስት ፊቱን ወደ ሶሻሊስት አገር በማዞር ፕሮፌሰር ፖሎኒን ከሃንጋሪ በማስመጣት አዲስ አበባ ቡዳፔስትን እድትመስል መሪ እቅድ አዘጋጅቶላት ነበር። ፕሮፌሰር ፖሎኒ በይበልጥ የሚታወቀው የአብዮት አደባባይን በመስራት ስለነበር የአሁኑን መስቀል አደባባይ በዘመናዊ መልክ ያዘጋጀ ሰው ነው። ፕሮፌሰር ፖሎኒ የአዲስ አበባ ክልል እስክ አዳማ እንዲደርስ ለደርግ ሃሳብ አቅርቦ እንደነበር ይታወቃል።

  እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር እስክ 1986 ድረስ የአዲስ አበባ መሪ እቅድ ሲዘጋጅ የነበረው ለአዲስ አበባ ባእድ በሆኑ ባለሙያዎች እና በባዕድ ፍልስፍና ስለነበር አዲስ አበባ መምሰል እና መሆን የሚገባትን ከተማ ሳትመስል የመቶ አመት ጉዞዋን ጨረሰች። ኢትዮጵያዎያን ባለሙያዎች የተሳተፉበት የመጀመሪያው መሪ ዕቅድ የተዘጋጀው እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ 1986 ነበር። ይህ አጋጣሚ አዲስ አበባ ታሪካዊ ማንነቷን መልሳ እንድታገኝ መንገድ ቢከፍትም ህጋዊ እና ፖለቲካዊ ማንነቷ እስከዛሬም ድረስ አወዛጋቢ ሆኖ ቆይቷል። እንግዲህ ከላይ እንደ ተመለከትነው አዲስ አበባ በኢትዮጵያውያን ብትቆረቆርም በታሪኳ ውስጥ የብዙ አገሮችን ከተማ አሻራ ይዛ ነው ያደገችው። በባእዳን ይዘጋጅላት የነበረው መሪ እቅድም ማህበራዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ ችግሯን የሚፈታ ሳይሆን የጊዜውን ፍልስፍና እና ርዕዮተ ዓለም እንዲያንጸባርቅ ተደርጎ ነበር። በዚህ ምክንያት አዲስ አበባ ታሪካዊ ማንነቷን ያጣች ሲሆን የከተማዋ ህጋዊ ወሰንም በትክክል ተከልሎ ስለማያውቅ ህጋዊ መንነቷም ጥያቄ ውስጥ ገብቷል። ከዚህም በተጨማሪ አዲስ አበባ ካላት ክልላዊ፤ አገራዊ፤ አህጉራዊ እና አለም አቀፋዊ ሚና አንጻር የሚመጥናትን የፖለቲካ አመራር ስላላገኝች እንደ መንደር በመመሪያ ቁጥር አንድ እና ሁለት ስትመራ ቆይታለች። እንግዲህ ከአዲስ አበባ ታሪክ የምንማረው ቁምነገር አዲስ አበባ ህጋዊ፣ ታሪካዊ እና ፖለቲካዊ ማንነቷን በማጣቷ ዛሬ ለምናየው ችግር መፈጠር ዋነኛው ምክኒያት ነው።

  የመፍትሄ ሃሳቦች

  አዲስ አበባ የሌሎችን በፌድራል የሚተዳደሩ ሃገሮችን ዋና ከተማ በተለይም ከአቡጃ እና ከብራሰልስ ልምድ በመውሰድ የአዲስ አበባን አስተዳደር በአዲስ መልክ ማዋቀር ዘላቂ መፍትሄ ሊያመጣ ይችላል።
  ከተማዋ ስትዋቀር የከተማ ክልል እና የመስፋፊያ ከልል ተብሎ በህግ የተወሰነ ግለጽ ወሰን ማበጀት አሁን ያለውን ውዝግብ ሊያስቀር ይችላል።
  አዲስ አበባ ዛሬ ያለባትን ችግር ብቻ ሳይሆን በሃያ እና ሰላሳ አመት ውስጥ ሊገጥማት የሚችለውን ችግር በማሰብ መሪ እቅድ ሊኖራት ይገባል።
  አዲስ አበባ ለነዋሪዎቿ፤ በዙሪያዋ ላሉ አስተዳደሮች እና ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ህጋዊ እና ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ ስርዓት እንዲኖራት ፖለቲካዊ እና ህጋዊ ስርዓት መዘርጋት።
  የከተሞችን መስፋፋት በፖለቲካ ድንበር ማቆም ስለማይቻል ከተሞችን በፌድራል እና በክልል በጋራ የማስተዳደር ህግ እና ስርዓት መዘርጋት። ይህ ወደፊት በክልል እና በፌድራል ከተሞች መካከል ሊፈጠር የሚችለውን አላስፈላጊ ውዝግብ ሊያስቀር ይችላል።
  የኦሮሚያ እና የፌድራል መንግስት ከስሜት ነጻ በሆነ፤ በሃገራዊ ሃላፊነት እና በፖለቲካ ቁርጠኝነት ተቀራርበው ከሰሩ አዲስ አበባን የሁሉም ኢትዮጵያዊ የአንድነት እና የብዝሃነት መገለጫ ማድረግ ይቻላል።
  መልካም ንባብ!

  331
  SHARES
  FacebookTwitter
  Leave a Reply
  Your email address will not be published. Required fields are marked *

  Comment

  Name *

  Email *

  Website

  This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

  GDPR – Request personal data Legal Statements መነሻ ገጽ About Us Contact Us Ads Rate Ethio Newslink
  ↑ Zehabesha Amharic Log in –

  Reply
 2. I WOULD LIKE TI INVITE ESKENDIR TO READ THID PROFESIONAL ARTICLE

  Zehabesha Amharic
  ETHflag_
  1__1_

Post Comment