ኦሮሞኛ ቋንቋ በኢትዮጵያ ምድር እንዳይነጋገርበት ተከልክሎ አያውቅም!

Source: http://welkait.com/?p=8749

የኢትዮጵያወርቅ (የሐረርወርቅ) ጋሻው

የኢትዮጵያ ሕዝብ ሊያውቅ የሚገባ፣ ዛሬ ለመጻፍ ያነሳሳኝ ዋናው፡-

በኦሮሞው ስደተኛ ስም የሚፈጸም ግፍ የኦሮሞን ብሔር በኢትዮጵያ ምድር ብቻ ያለውን ሳይሆን ከኢትዮጵያም ውጪ የጎረቤት አገሮች አገሩ በመሆኑ በሕዝባቸው ቆጠራ በሚታወቅበት ጭምር አደጋ ላይ ጥለውት ይገኛል፣ ከወለጋ የወጡት ጥቂት እንክርዳዶች ኦነጎች። ይሄንን ጉዳይ አስመልክቶ እና ሌላውን ኦሮሞ እነዚህ የወለጋ ኦነጎች እንዴት እንደሚያዩት እንደሚርቁት በቅርብ በሰፊው እመለስበታለሁ።

አንደኛ፡-

“ኦሮሞኛ መነጋገር በደርግ ጊዜ ክልክል ነበር፣ በንጉሱም ጊዜ እንዲሁ፣ ማንም ከቤቱ ውጪ በይፋ እንዳይነጋገርበት ይከለከል ነበር።” ይላል።

አይ ውሸት! እንደው ለካስ የአጎቴ የእናቴ ታላቅ ወንድም ሃደኛቱ የሚለው እውነቱን ነበር ማለትም እናት በሊታ። ኢትዮጵያን እናቱን በሊታ ለማለት ነው።

ሁለተኛ፡-

ባለፈው አመት እንደጻፉት አሁንም “በደርግ ግዜ መንግስቱ ኃይለማርያም ስልጣኑን ተጠቅሞ ኦሮሞኛን በአማርኛ፣ በትግሪኛ እና በጉራጌኛ ቀይሮት ነበር። በሃሉም የእነዚህ የሶስት ብሄሮች ብቻ እንዲሆን ኦሮሞውን ሲያስገድደው ኖርዋል ይላል።”

አቤት ቆርጦ ቀጥልነት፣ ሕሌና ማጣት። እውነት እነዚህ የኢትዮጵያ ኦሮሞች ናቸው ወይስ የሶማሌ፣ የኬኒያ፣ የዩጋንዳ ወይስ የሱዳን እራሳቸውን እነሱ እያስቀመጡ እንዳሉት። የኢትዮጵያ ኦሮሞዎች እንዴት እንደሚያስቡ ከዚህ በታች ባጭሩ አስቀምጠዋለሁ ከሃቅ በመነሳት በተለመደው።

በኦሮሙኛ ሳምንታዊ የሬዲዮ ስርጭት በደርግ ጊዜ ተጀምሮ ይተላለፍ ነበር እንኳን ሊከለከል!

ሃቁ በማስታወቅያ ሚንስትር መስሪያ ቤት በጊዜው የነበራችሁ ጋዜጠኞች ለሃቅ የምትመሰክሩ እና ቴፑ እራሱ በኦሮሙኛ ይተላለፍ የነበረው ስርጭት በኢትዮጵያ ሬድዮ ምስክር ነው። ኦነገ እና ጉፋያዎቹ ወዴት ሊገቡ ነው። ዜናውን እና ፕሮግራሞቹን ሲያዘጋጁ እና ሲያቀርቡ የነበሩት ጋዜጠኞች በሕይወት አሉ እኮ።

ጥቂት ልበል ለመነሻ፡-

እንደሚታወሰው ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማሪያምን በስልጣን ላይ እያሉ እና ከስልጣንም ከወረዱ በኋላ ማግኘቴ ግልጽ ነው። ከስልጣን ሳይወርዱ ከአንድ አመት በፊት፡ በአገራችን በአዲስ አበባ ጽሕፈት ቤታቸው በይፋ በኢትዮጵያ፡ በሕዝቧ እና መከላከያ ሰራዊቷን እና ሰላም እና እርቅ ከገንጣዮች ጋር እንዲደረግ ጭምር በማስብ የኢትዮጵያ ጉዳይ እጅ አሳስቦኝ ላለፈው 26 አመት እየሄድነው ያለንው አሳዛኝ ሁኔታ በወያኔ እየተፈጸመ ያለው እንዳይፈጠር በማሰብ፡ ከኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማሪያም ጋር ሃሳብ መለዋወጤ አይረሳም።

ታዲያ በዚያን ጊዜ በኢትዮጵያ ሚዲያ የተመለከቱት ጉዳዩን፡ ለእኛም ድምጻችንን ታሰማለን በለው፡ የሸዋ ኦሮሞዎች በጊዜው እርዳታ ማስተባበሪያ ይሰሩ በነበሩ እኔን በቅርብ የሚያገኙ ኦሮሙኛ ተናጋሪ የአቃቂ ኗሪ በሆኑት ወንድም አማካኝነት፡ እሳቸውን የሚያውቁ ባስተባበሩት ፡ የአቃቂ እና የአዲስ አበባ፣ የሰላሌ፣ የሸኖ፣ የአንቦ እናም የሰንዳፋ ሰዎችን ያካተተ ኮሚቲ ቀደም ብሎ የነበረ ተሰሚነት አጥቶ በተስፋ ይጠባበቅ የነበረ ጥሪ ባደረገልኝ መሰረት እርዳታ ማስተባበሪያው ውስጥ በነበሩት ወንድም አማካኝነት ተነግሮኝ አብረን በመሄድ በስብሰባው በመገኘት ሃሳባቸውን እና ኮሚቲውን ወክዬ በእየሳምንቱ የሚተላለፈው ኦሮሞኛ ለወለጋዎች ብቻ እንጂ ለእኛ ስለማይገባን ይቀየርል ብለው የጻፉትን እና እኔንም እንድትወክለን ሃላፊነት ውክልና ሰጥተናታል የሚል ጽፈው ፈርመው የሰጡኝን አምኘበት፡ ሰፋ ካለ ሃሳብ መለዋወጥ በኋላ ጠያቂዎቹ የሚሉትን ይዤ ወደ ሚመለከተው ማስታወቂያ ሚንስትር አቅርቤ በመጨረሻም ለኮሎኔል መንግስቱጋ ጉዳዩን ከሚንስትሩ ጋር በመተባበር አቅርበን ጉዳዩ ተቀባይነት አግኝቶ ነበረ።  ይሄውም የወለጋውን ኦሮሙኛ ስርጭት እንዳለ ሆኖ ብዙሃኑ በሚሰሙት ኦሮሙኛ እራሱን የቻለ ሌላ የሬዲዮ ስርጭ ቅዳሜ ቀን እንዲቀርብ ተወሰነ ማለት ነው።

እስከዚህ ነው እንግዲህ ኦሮሙኛ በህግ ክልክል ነበር በሚል ዛሬ ኦነጎች እያስተጋቡ ያሉት። በጊዜው የነበራችሁ ጋዜጠኞች በሳምንት አንዴ እሁድ እሁድ ኦሮሙኛ ይቀርብ እንደነበረ የምታውቁ ኦነግን ቶሽ! ልትሉት ይገባል። ገነጣጣዮች ከወለጋ የወጡት ጥቂት እንክርዳዶች የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪን እና የኤርትራን ሕዝብ ነፃ አውጪን የኦሮሞ ነፃ አውጪ በሚለው ስማቸው እየመሩ የኢትዮጵያ በኢተመንግስት አስገብተው ትልቁን የኦሮሞ ሕዝብ ቲንሽ አድርገው በጉልበት ቁጭ አሉ እንደነሱ አይምሮ በክልል አስቀመጠው። ከዛም አሳልፈው በክልል ሸጠውት ወጡ እነዚህ ወንጀለኞች። አሁንም መኖሪያቸው “ኦሮሞ” ነው።

በመጨረሻም ፡ እንደሚታወቀው አንድም ቀን አንድም የኢትዮጵያ መንግስት ወይም መሪ እራሱ ኦሮሙኛውን ወደ ቤተመንግስት በጎንደር አስገብቶ የቤተመንግስቱ ቋንቋ ከማድረግ ውጪ፡ ኦሮሙኛ በህግ ይቅር እና በድብቅም ክልክል እንዳልነበረ በሚገባ ከኦሮሞው የተወለደው ቤተሰብ ጭምር የሚያውቀው ነው። የከለከለ መንግስት የለም። ለኢትዮጵያ የቆምነው ማስረጃ በሚሊዮን የሚቆጠር አለን አገራችንን ኢትዮጵያን ለሕዝቧ የኢትዮጵያ ባለቤትነቱን ለማስከበር።

ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!

የኢትዮጵያወርቅ (የሐረርወርቅ) ጋሻው
ዘብሄረ አንዲት ኢትዮጵያ!
Yehar9@aol.com

Share this post

One thought on “ኦሮሞኛ ቋንቋ በኢትዮጵያ ምድር እንዳይነጋገርበት ተከልክሎ አያውቅም!

Post Comment