ኦሮሞ የሞተላትን ሃገር ጥሎ ወዴትም አይገነጠልም – ኦሮሞ ከኢትዮጵያ ውጭ ሃገር የለውም አይኖረውም። ( ጠ/ሚር አብይ አህመድ )

Source: https://mereja.com/amharic/v2/52828

የኢሳት ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን።
የኦህዴድ ድርጅታዊ ጉባዔ በጂማ እየተካሄደ ነው። ጠ/ሚር አብይ አህመድ አስደናቂ የሆነ ንግግር ማድረጋቸውን ትርጉሙን ካካፈሉኝ ወዳጆቼ ተረድቼአለሁ። ቀሲስ ኤፍሬም በፌስ ቡክ ገጻቸው የዶ/ር አብይን የዛሬ ንግግር እንዲህ ቀንጭበውታል

«እሳት ውስጥ ቆመን፣ ስድቡን ሁሉ ችለን፣ ትግሉን ከዳር አድርሰነዋል። ኦሮሞ ከለቅሶ መውጣት አለበት። …. ይህ አገር ያለ ኦሮሞ አገር መሆን አይችልም። ለኦሮሞ ኢትዮጵያ ብቻ ትጠበዋለች። አፍሪካንም መገንባት ይችላል ብለን ተነሥተናል። … ረጅም መንግድ እንድንሄድ ከፈለጋችሁ ይቺን አገር የመገንባት ኃለፊነት እንዳለብን እንወቅ። …. አድዋ ላይ ማን ነው ያሸነፈው? … ይህንን አገር ለማን ትተን ነው የምንመለሰው? አንመለስም»
“ከዚህ በኃላ በኦሮሞ ህዝብ ስም መነገድ የለም። ኦሮሞ የሞተላትን ሃገር ጥሎ ወዴትም አይገነጠልም።

Share this post

One thought on “ኦሮሞ የሞተላትን ሃገር ጥሎ ወዴትም አይገነጠልም – ኦሮሞ ከኢትዮጵያ ውጭ ሃገር የለውም አይኖረውም። ( ጠ/ሚር አብይ አህመድ )

 1. “ከዚህ በኃላ በኦሮሞ ህዝብ ስም መነገድ የለም። ኦሮሞ የሞተላትን ሃገር ጥሎ ወዴትም አይገነጠልም።”
  +++++++++++++++++++++++++++++++++++
  **መቼም ኮ/ል ዓብይ አህመድ ዓሊ ይህንን ኮስታራ ፊት ሊያሳይ ይህንን መፈከር ሊያሰማ ያደፋፈረና ያስቆጣው በይቅርታና መደመር እሳቤ ያለ ቅድመሁኔታ ፈቶ የለቀቃቸው የውጭ ዜጎች እንጂ አማራና ትግሬ አደለም።
  ይህ ሰውዬ አምባገነን ሲሆን ታየኝ !
  ” በምሕረት በይቅርታና በመደመር መልካም ምኞት ለመግለፅ የመጣችሁ እንግዶቻችን ሆይ፤
  አሁን የጭፈራና የፈንጠዝያው ግዜ ስላለቀ ላደረጋችሁልን ትብብር እያመሰገንን ከድሃው ጉሮሮ *ተቀንሶ ለጤነነታችሁና ለደህንነታችሁ ያወጣነው ወጪ ሁሉ በይቅርታና በእንግዳ ተቀባይነታችን ኢትዮጵያዊ ባሕልና ጨዋነት ሂሳቡ በእኛ *ተደምሮ ለሕዝብ *ተካፍሎ ከዚህ በላይ የድሃ ገንዝብ ማባከንም ሆነ ጭፈራ ድህነት *ማብዛት ሆነብን። የእናንተም የሻንጣ ገንዘብ በጥቁር ገበያ ተለወጦ ለሀገር ምንም ያተረፈ ስላልሆነ፡ ለነበረን መልካም የፌሽታ ግዜ ከልብ ደስትኞች ነን ወደፊት በራሳችሁ ወጪ እየመጣችሁ የዲሞክራሲ ተቋዳሽ፡ የምሕዳሩ ተሽከካሪ እንድትሆኑ እየተመኘን ከሚቀጥሉት ቀናት በኋላ ምንም ስብሰባና የመንገድ ላይ ጭፋሮ አክሳሪ እንጂ አዋጪ ሆኖ ስላላገኘነው ቢቻል የውጭ ዜግነታችሁን በኢትዮጵያዊነት ለውጣችሁ በሰላምና በደስታ በእናት ሀገራችሁ ኢትዮጵያ ላይ በሰላም የጡረታ ዘመናችሁን እንድትገፉ፡ አለዚያም በጎብኝነት ወጥታችሁ ከሀገር ውጭ በመቆየት የውጭ ዜግነትና የጡረታ መብታችሁ፡ ከመሰርዙና የጤና የነጻ ሕክምና ካርዳችሁ ግዜው አልፎ ያለ ጧሪ ቀባሪ ያለ ዕድር በፓርቲ ምሥረታ ብቻ መንገድ ከምትወድቁ አማራጩን ትመረጡ ዘንድ ከወዲሁ እናሳስባለን!! ዲሞክራሲ ሂደት እንጂ በሻንጣ የሚመጣ ቁሳቁስ ስላልሆነ እኛው ባለን የተማረ ኅይልና ኅብረተሰብ ተሳትፎ እንድናዳብረው የወሰነን ስልሆነ እንደተለመደው የውጭ ሀገር ልምድ ሐሳብ ስንፈለግ እኛው በመልዕክተኛ ወይንም የእውቀት ሽግግር በሬዲዮና በቲሌቪዥን ጣቢያችሁ የቀጥታ ስርጭት የዲሞክራሲ ግንባታ ትምህርት እንድትሰጡ በማሰብ ወደመጣችሁበት ሀገር ትመለሱ ዘንድ የሰጠናችሁ የጥበቃ ዋስትና ብዙ ሂሳብ ስልጠየቀና የሀገራችን ጸጥታ መደፈረስ የፍቅርና የመደመር ምኖታችን የረስ በረስ ፊክክር ቁርሾና የዘር መተላለቅ ተከስቶ በዓለም ደረጃ ከርሃብተኝነትና ደንቁርና ተጭማሪ እሴት በዘር ማጥፋት ማፈናቀል ሀፍረትና ውርደትን ደምረናል!! ስለሆነም ከፖለቲካ ግርግር ይልቅ ቅድሚያ የምንሰጠው ለሀገሩ ዜጋ ሰላምና ደህንነት በመሆኑ ከይቅርታ ጋር በሰላም ልንሸኛችሁ ወሰንን ይህም ሲባል ከመጣችሁበት ሀገር ተመልሳችሁ መንግስትን ማሳጣት፡ መወንጀል፡ ወይም ከሀገር ውስጥ በደል አለ የሚለው ጩኸት መሰማት አይኖርበትም!፡ ምክንያቱም እናንተው እዚህ ሆናችሁ ሀገር ሲረበሽ፡ የመጣችሁባቸው ሀገራት ኤምባሲ ወኪሎች የዓለም አቀፉ ማኅበራት ሁሉ ዕለት ከዕለት እንቅስቃሴአችሁንና የሕዝቡን ተቃውሞ ያለውን የፀጥታ መደፈረስ መንስኤ ምን እና ማን እንደሆነ የዓይን ምስክር ሆነዋል።
  ስለሆነም በሕዝብ ወጪ በኢሕአዴግ ቤተመንግስት በነበራችሁ ልዩ መንስተንግዶና ሰላማዊ እንቀስቃሴያችሁ ደጋፊና ተደጋፊዎቻችሁን አግኝታችሁ ያሳላፋችሁት የተንፈላሰሰ ግዜ አጭር ቢሆንም በዘመነ የዲሞክራሲ የኢትዮጵያ ንጹሕ አየር እንዳስደሰታችሁ ከመግለጫና ከፎተግራፋችሁ፡ ከተለያዩ ባሕላዊ ልብስ ሽልማቶች፡ ጭፈራዎች ከምትወክሉት ባንዲራ ጋር ልዩ ደታና ፍቅር ትዝታ የሚያጭር ለትውልድ የሚተላለፍ ቅርስ እንደሆነ የመጣችሁባቸው ዲፕሎማት ሀገሮች ሁሉ ደስተኛነታቸውን በመካከላችሁ ተገኝተው አረጋግጠውልናል። ስለዚህ ቀሪው ዘመን ዜግነት ቀይራችሁ ኢሃዴግ ላይ ተደመሮ በሶስተኛ አማራጭነት ለመኖር ከሆነ ሀገራችሁ ነው….አትሂዱ አትገንጠሉ ተደመሩ….እኛ እንደፈለግነውና እንደመረጥነው ሥልጣን ተካፍለን ወይም ክልል ተቆርሶ ተሰጥቶን ካላስተዳደርን ዋ ! እናፈርሳለን! የሚሉ አስገዳጅ ሁኔታዎች ግን ቅድሚያ ለነዋሪው ኢትዮጵያዊ ዜጋ ፍላጎትና ምርጫ ስለምንሰጥ፡ ዓላማና ፍላጎታችሁን በምርጫ ባገኛችሁት ዜግነት ሀገር ላይ መተገበርን አንከለክልም! ሀገሩ የፖለቲካ ፓርቲ ግለሰቦች ሳይሆን ኢትዮጵያ የ ፻፭ ሚሊየን ሕዝብ ሀገር (እ)ናት ።አራት ነጥብ።”
  የመደመር ጽ/ቤት ዋና ኅላፊ ሌ/ኮ ዓብይ አህመድ አሊ
  ….ቢልና ይህንን ዲያስፐር ሁሉ በወታደር መኪኒና ጭኖ ቦሌ አየር ማረፊያ ቢያጉራቸውስ?
  የመጡበት ሀገር በረራ ሰዓት እስኪደረስ ቃለመጠይቅ ሲደረጉ፡ ወንበር ላይ ተጋድመው ማየት በራሱ ዲሞክራሲ ነው።ሰወዬው በገዛ እግሩ ሄዶ መዘዝ ይዞ ይመጣል? አደለም እንዴ? ዋሸሁ እንዴ፧ ነን ሶቤ?

  Reply

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.