ኦነግ ሰላማዊነቱን በተግባር ማረጋጋጥ ይኖርበታል ተባለ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/77625


. በህግ ማስከበር ሂደቱም ህዝቡ ከጎናችን ሊቆም ያስፈልጋል

. ኦነግም ሰላማዊነቱን በተግባር ማረጋጋት ይኖርበታል
አዲስ አበባ፡- በኦሮሚያ ክልል በተለይም በምዕራብ ኦሮሚያ አካባቢ ተባብሶ የቀጠለውን ችግር ከመፍታት አኳያ የክልሉ መንግሥት ማንኛውንም ዕርምጃ በመውሰድ በክልሉ የህግ ማስከበር ሥራ እንደሚያከናውን ገለጸ፡፡ በሂደቱም የክልሉ ህዝብ ከመንግሥት ጎን እንዲቆም የተጠየቀ ሲሆን፤ ኦነግም አሁን ያለው የትጥቅ እንቅስቃሴ ለሰላም ያለውን አቋም ጥያቄ ውስጥ የሚከት እንደመሆኑ ሰላማዊነቱን በተግባር ማረጋገጥ እንዳለበት ተጠቁሟል፡፡
የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ዶክተር ዓለሙ ስሜ፣ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ በለውጥ ሂደቱ ጉልህ ድርሻ የነበራቸውን አካባቢዎች በተለይም የኦሮሚያ ክልልን የግጭት ማዕከል ለማድረግ እየተሠራ ነው፡፡ ይህ ሂደትም በተለይ በክልሉ ምዕራባዊ አካባቢዎች ላይ የዜጎችን ህልውና አደጋ ላይ ጥሏል፡፡ የሕይወት መጥፋት፣ ንብረት መውደምና ሌሎችም ሕገ ወጥ ተግባራትን አበራክቷል፡፡ በመሆኑም የክልሉ መንግሥትም ሆነ ክልሉን የሚመራው ፓርቲ በማንኛውም መልኩ የሕግ የበላይነትን ማስከበር እንደሚገባ ወስኖ ወደተግባር ገብቷል፡፡ የክልሉ ህዝብም ይሄን ተገንዝቦ ድጋፉን ሊያደርግ ይገባል፡፡ ኦነግም ሰላማዊነቱን በተግባር ማረጋገጥ ይኖርበታል፡፡
ዶክተር ዓለሙ እንዳሉት፤ ባለፉት ሦስትና አራት ዓመታት የኢትዮጵያ ህዝቦች በስርዓቱ ላይ የሚታየውን ችግር በመቃወም የተለያየ ትግል ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡ በዚህ ውስጥ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጉልህ ድርሻ ያለው ቢሆንም፤ የዚህ ትግል እንብርትና ማዕከል የሆነውና ትልቅ መስዋዕትነትም የከፈለው የኦሮሞ ህዝብ በተለይም የኦሮሞ ወጣት ወይም ቄሮ ለለውጡ ትልቅ አስተዋጽዖ ያደረገ ኃይል ነው፡፡ እንደ ድርጅትም ክልሉን የሚመራው ድርጅት ኦዴፓ ለውጡን እውን ለማድረግ ከሌሎች እህት

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.