ኦፌኮ በነቀምት ከተማ አባላቱን ጨምሮ 2ሺ የሚደርሱ ሰዎች መታሰራቸውን አመለከተ።

Source: https://mereja.com/amharic/v2/131454

DW : የኦሮሞ ፈደራሊስት ኮንግረስ ኦፌኮ ካለፈው ሰኔ ወር ጀምሮ በነቀምት ከተማ አባላቱን ጨምሮ 2ሺ የሚደርሱ ሰዎች መታሰራቸውን አመለከተ። የኦፌኮ የምስራቅ ወለጋ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፈቃዱ አያናን ጨምሮ ታሳሪዎቹ በከተማዋ ኩምሳ ሞሮዳ ቤተመንግሥት ግቢ እንደሚገኙ ተገልጿል።
በምሥራቅ ወለጋ የኦፌኮ ጽሕፈት ቤት ፀሐፊ አቶ ዓለሙ ኦሉማ የፓርቲያቸው አመራሮችም ሆኑ አባላት ሕጋዊ መስፈር በሌላቸው በተለያዩ ሰበቦች በመታሰራቸው መንግሥት ተግቢውን ማስተካካያ ማድረግ እንዳለበትም ተናግረዋል፡፡ «ምሥራቅ ወለጋ ነቀምቴ ከተማ የኦፌኮ ሊቀመንበር አቶ ፍቃዱ አያና የሚባል አሁን ሦስት ሳምንቱ ጨርሷል ከታሰረ ያለምንም ጥያቄ የኩምሳ ሞሮዳ ውስጥ ነው ያለው።
ሌሎች ደግሞ እዚያ ቴረሞ የሚባል አለ አሎረሞ የሚባል አለ እዚያ ደግሞ ሰባት ሰዎች ናቸው የታሠሩት እነሱ ደግሞ ወደ ጦላይ ነው የሄዱት።»ከታሰሩት መካከልም ሃኪሞች፣ ሌሎች የመንግሥት ሠራተኞች እንዲሁም በግል ሥራ የሚተዳደሩ ዜጎች መኖራቸውንም ለአሶሳው ዘጋቢያችን ነጋሳ ደሳለኝ ገልጸዋል። የኦፌኮ አባላት ስለመታሰራቸው እንደማያውቁ የተናገሩት የኦሮሚያ ክልል ፀጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ኮሎኔል አበበ ገረሱ በበኩላቸው የታሰሩት በጦርነት የተማረኩ እና ወንጀል የሰሩ ናቸው ብለዋል። «እኛ የምናውቀው ሽፍቶች ነው እየተያዙ ያለው የሚታሰረውም።
እነኚያን ሽፍታ ከያዝክ ወደማዕከል ታስገባለህ ወይ ደግሞ ምርኮኛ ነው፤ ምርኮ ማዕከል ገብቶ ተሀድሶ ወስዶ ወንጀል ካለበት ይጣራል። ወንጀል ከሌለበት እንደማንኛውም ተሀድሶ ወስዶ ወደማኅበረሰቡ ይቀላቀላል የሚያዙት ያሉት ከእነዚህ ጋር ተያያዥነት ያላቸው እና በቀጥታ የተሳተፉ ናቸው እንጂ ከሕግ ውጪ ያሰረ ሰው የለም።» በተመሳሳይ በምዕራብ ወለጋ በጊምቢ ከተማ በርካታ ሰዎች ከታጣቂዎች ጋር

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.