ከመጋቢት እስከ መጋቢት’ የፎቶ ዐውደ ርዕይ መጋቢት 22 ቀን ይከፈታል

Source: https://fanabc.com/2019/03/%E1%8A%A8%E1%88%98%E1%8C%8B%E1%89%A2%E1%89%B5-%E1%8A%A5%E1%88%B5%E1%8A%A8-%E1%88%98%E1%8C%8B%E1%89%A2%E1%89%B5-%E1%8B%A8%E1%8D%8E%E1%89%B6-%E1%8B%90%E1%8B%8D%E1%8B%B0-%E1%88%AD%E1%8B%95%E1%8B%AD/

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ‘ከመጋቢት እስከ መጋቢት’ የፎቶ ዐውደ ርእይ መጋቢት 22 ቀን 2011 ዓ.ም እንደሚጀመር የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

ይህ የፎቶ አውደ ርዕይ በሚሊኒየም አዳራሽ ላሊበላ ክፍል እንደሚካሄድም ነው የተነገረው፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድን የአንድ አመት ቆይታ የሚያሳየው የፎቶ አውደ ርዕይ ከመጋቢት 22 ቀን ጀምሮ እስከ መጋቢት 26 ቀን 2011 ዓ.ም ባሉት አራት ቀናት ለጎብኝዎች ይከፈታል ተብሏል፡፡

የፎቶ አውደ ርዕዩ በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት የተዘጋጀ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

Share this post

One thought on “ከመጋቢት እስከ መጋቢት’ የፎቶ ዐውደ ርዕይ መጋቢት 22 ቀን ይከፈታል

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.