ከሺዎች ንፁህ ውሃ አቅርቦት ጀርባ ያለች ኢትዮጵያዊት ወጣት

Source: https://amharic.voanews.com/a/young-ethiopian-provides-clean-water-for-thousands/5431864.html
https://gdb.voanews.com/3E8CD0BE-4B2D-4C29-8C09-0E6673CE19AA_w800_h450.jpg

በንፁህ ውሃ አቅርቦት ችግር ዜጎቿ ለተለያዩ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ከሚጋለጡ ሃገሮች መካከል ኢትዮጵያ አንዷ ናት። ውሃ ለመቅዳት ለሰአታት በእግር ከመጓዝ ጀምሮ በንፁህ ውሃ እጦት ለበሽታ የሚዳረጉ ሰዎች ብዙ ናቸው። ሄርሜላ ወንድሙ በወጣትነት ዕድሜዋ ይህንን ተረድታ በመላው ኢትዮጵያ በዚህ ችግር የሚሰቃዩ ዜጎችን በንፁህ ውሃ ተደራሽ ለማድረግ ‘ጠበታ ውሀ’ የተሰኘ ግብረ-ሰናይ ድርጅት መስርታ፣ በአምስት የተለያዩ ክልሎች 70 የውሃ ጉድጓዶችን አስቆፍራለች።

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.